Get Mystery Box with random crypto!

የሰላም ስምምነቱ ከግብ እንዲደርስ መንግስት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል - ዶ/ር ለገሰ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የሰላም ስምምነቱ ከግብ እንዲደርስ መንግስት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የሰላም ስምምነቱ ከግብ እንዲደርስ መንግስት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑት÷ የጦርነትና ግጭቶች መቋጫው ዘላቂ ሰላምን ያረጋገጠ እንዲሆን ለማድረግ መስዋዕትነትን የሚከፍሉ ሃይሎች ትናንትም ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ነገም ይኖራሉ ብለዋል፡፡

እነዚህ ጀግኖች በሽግግር ፍትህና በፅኑ መሰረት ላይ በተገነባ ማንነትና ድርጊት ይታነፃሉ ያሉት አቶ ለገሰ÷ የጀግኖች ወሮታ ጠንካራ ሀገርና የሀገረ-መንግስት ግንባታ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ይህን ሃቅ የብዙ ሀገራትን ታሪክ መለስ ብሎ የቃኘ ሰው ሊረዳው ይችላል፤በእኛም ሀገር የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲሳካ ብዙዎች መስዋዕትነትን ከፍለዋል ብለዋል፡፡

የሰላም ጥረቱ ከዳር እንዲደርስ፣ የህዝባችን መሻት እውን እንዲሆን እና ያስቀመጥናቸው ሀገራዊ ግቦች እንዲሳኩ ሁላችንም የሰላም ስምምነቱን መርሆዎች ማክበር ይገባናል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
Fbc

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet