Get Mystery Box with random crypto!

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደረሰበት ግፍ ጥቅምት 24 ቀን ታስቦ እንደሚውል ተገለፀ ጥቅምት 24 | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደረሰበት ግፍ ጥቅምት 24 ቀን ታስቦ እንደሚውል ተገለፀ

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመው ጥቃት ታስቦ እንደሚውል የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል ።

ዕለቱ በኢትዮጵያ ክህደት እና ባንዳነት እንዳይደገም ለማስገንዘብ ታስቦ የሚከበር እንደሆነ ተገልጿል ። ቀኑ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ታስቦ እንደሚውል የተገለፀ ሲሆን ሁሉም የመንግሥት እና የግል ተቋማት ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ተገልጿል ።

ዕለቱ ጥቅምት 24  መቼም አልረሳም በሚል መሪ ቃል አራት ሰዓት ሲሆን ሁሉም በየአለበት በመሆን እንደሚከበር ተነግሯል ።
@Ezmerejaet
@Ezmerejaet