Get Mystery Box with random crypto!

240 ኩንታል ቡና በመዝረፍ በአዳማ ከተማ መጋዘን ውስጥ የደበቁ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

240 ኩንታል ቡና በመዝረፍ በአዳማ ከተማ መጋዘን ውስጥ የደበቁ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ተጠርጣሪዎቹ የእርዳታ ድርጅት ሙሉ ዱቄት ከነተሳቢው ከአዳማና ሻሸመኔ ዘርፈዋል

በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ንብረቶችን ሲዘርፉ የነበሩ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።የተለያዩ የግል እና የመንግስት ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ከሻሸመኔ ከተማ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ የእርዳታ ድርጅት ሙሉ ዱቄት የጫነ ተሽከርካሪ ከነ ተሳቢው የዘረፉ መሆናቸውም ተገልጿል።

ግለሰቦቹ በተመሳሳይ በአዳማ ከተማ ሙሉ የእርዳታ ዱቄት የጫነ ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ሰርቀው ሊሰወሩ ሲሉ ነው በቁጥጥር ስር ውለዋል።በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ በባሌ ዞን ከሚገኘው ትራኮ ጣኢር ጅብሪል ከተባለ የቡና አምራች ድርጅት 240 ኩንታል ቡና ዘርፈው አዳማ ከተማ ባለ መጋዘን ውስጥ ደብቀው የተያዙ መሆናቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር ብርሃኑ ጫላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የተዘረፈው 240 ኩንታል ቡና ግምቱ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ነው።12ቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች የግለሰብ እና የመንግስት ተሽከርካሪዎችን የሰሌዳ ቁጥር እየቀያቀሩ የሚዘርፉ ሲሆን በግለሰቦቹ እጅ ከ20 በላይ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ተይዟል።

በቁጥጥር ስር በዋሉት ተጠርጣሪዎች ላይ በበቂ ሁኔታ በመረጃ የተጠናከረ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ መዝገቡ ለአቃቤ ህግ መላኩን ዋና ኢንስፔክተር ብርሃኑ ጫላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet