Get Mystery Box with random crypto!

ሞቃዲሾ አልሸባብ ቅዳሜ'ለት በሞቃዲሾ ባደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ የፈንጂ ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

ሞቃዲሾ
አልሸባብ ቅዳሜ'ለት በሞቃዲሾ ባደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ የፈንጂ ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ እና ሌሎች ከ100 በላይ የሚገመቱ ሰዎች እንደቆሰሉ የሱማሊያ ዜና ምንጮች ፖሊስን ጠቅሰው ዘግበዋል። አልሸባብ ጥቃቱን የፈጸመው በትምህርት ሚንስቴር ቅጥር ግቢ ውስጥ እና አቅራቢያ ባፈነዳቸው መኪና ላይ የተጠመዱ ፈንጂዎች ነው። የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልጸው፣ ፕሬዝዳንቱ መንግሥታቸው በአልሸባብ ላይ የሚያደርገውን ውጊያ ግን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet