Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የህንጻ ማቆሚያ ስፍራን(ፓርኪንግ )ለሌላ አገልግሎት ሲጠቀሙ የነበሩ 55 የህንጻ ባለ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

በአዲስ አበባ የህንጻ ማቆሚያ ስፍራን(ፓርኪንግ )ለሌላ አገልግሎት ሲጠቀሙ የነበሩ 55 የህንጻ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ከተሸከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ  ጋር በተያያዘ አዲስ የፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ ለሚያወጡ የህንጻ ባለሀብቶች በዲዛይኑ መሰረት አገልግሎት መስጠታቸዉን መፈተሸና ማረጋገጥ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡በተጨማሪም የተሸከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ ብቃት ማረጋገጫና እድሳት ለሚያደርጉ የህንጻ ስር ፓርኪንግ በዲዛይን መሰረት አገልግሎት መሰጠቱን መፈተሽ እና የቁጥጥር ስራ መሰራቱን በአዲስ አበባ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ  የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርሃኑ ኩማ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል

በዚህም መሰረት በ2015 ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የህንፃ ስር የተሸከርካሪዎች ቦታ አጠቃቀም ስርዓት ለማስያዝ ሰማንያ ስምንት ህንፃዎች ላይ ፍተሻ ተደርጎ የመኪና ማቆሚያ ስፍራን ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ሃምሳ አምስት ህንፃዎች ላይ ተገቢ የሆነ  ህጋዊ  እርምጃ  መወሰዱ ተነግሯል ፡፡

በተጨማሪም  ሰላሳ አራት የሚሆኑ በመንገድ ላይ የተዘጋጁ የተሸከርካሪ ማቆሚያ ስፍራዎች አዲስ ተደራጅተው ለሚመጡ ማህበራት የመስክ ምልከታ በማድረግ እና ማህበራት የሚደራጁበትን  ቦታዎችን መለየት ተችሏል፡፡ ከመንገድ ዳር እና ከመንገድ ውጭ ላሉ ማህበራት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ፣ ህገ-ወጥ የፓርኪንግ ማህበራትን የመለየት ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አቶ ብርሃኑ ኩማ ጨምረውም ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet