Get Mystery Box with random crypto!

የሚኒሊክ ጀብድ የአድዋው ድል የፈረሰኛው ጊዮርጊስ እርዳታ እና ያልተነገረለት ታላቅ ሀያል ያለው ሞ | የሬጌው👑 ንጉስ🇪🇹™

የሚኒሊክ ጀብድ የአድዋው ድል የፈረሰኛው ጊዮርጊስ እርዳታ እና ያልተነገረለት ታላቅ ሀያል ያለው ሞኦ መንግስት የተሰኘው መጻህፍ !

ለዛሬቱ የድል በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡

የዛሬ 125 አመት እለተ ቅዳሜ ማታ በአድዋ አቅራቢያ በሚገኘው እምየ ምኒሊክ ባከበሩት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ታላቅ ሱባኤ ተይዟል ::
ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ሚኒልክ ማለትም ከ 3ሺ አመት በፊት ከ እስራኤል ከሌላውያኑ ጋ በሚስጥር የገቡ ታቦተ ጽዮንን ጨምሮ አምስት መለኮታዊ ሀብታት አሏት።
ለዛሬ አንድን ልግለ ጥላችሁ።
በአድዋ ላይ ድል ስላደረገው የጊዮርግስ መገለጥ ሃይሉ ምንጭ ምክኒያት ከዚህው ቅዱስ መጻህፍ የሚቀዳ ታሪክ አለው።
ብዙ ጊዜ በአድዋ ታቦት አብሮ መዝመቲ ቅዱስ ጊዮርጊስም መዋጋቱ ይገለጣል ነገር ግን ዋናው ሚስጥር ሲነገር አይስተዋልም።
''ሞኣ መንግስት'' ይባላል ከታቦተ ጸዮን ጋ ለሙሴ ከተሰጡት መለኮታዊ ስጦታወች ዋናው ነው።
ይህ ቅዱስ እቃ ሀገር ስትጨነቅ መከራ ሲመጣ ቸነፈር ሲፈጠር ክፉ እና ወራሪ ሲመጣ ጠበበት አባቶቻችን ከመንበሩ ያወጡታል ጸሎቱ የሚፈጸምበት የራሱ የሆነ ስርአትን ይፈጸማሉ በሀገር ላይ ፍጹም ሰላም ይመጣል ይህ መፈንቅለ መንግስት እንደ ማለት ነው ሲገለጥ ሲነበብ ስርአቱም ሲፈጸም ሃይሉ ይገለጣል ሚኒሊክም ብልህ ነበርና ሚስጥሩንም ያወቅ ነበር እና ካለበት አስፈልጎ ከመንበሩ አስወጥቶ ስርአቱን እንዲፈጸም አድርጓል ሃይሉም በምድሪቱ ላይ ተገለጠ ያነገሱት ጊዮርጊስም ሊረዳ ከራማ መጣ።

ካህናት በግራና በቀኝ
"ነዓ ነዓ ነዓ ጊዮርጊስ እንዘ ትፄአን በፈረስ ወነዓ ፍቁርየ ዘልዳ እነዘ ትፄአን በፈረስ ወነዓ ፍቁርየ ዘልዳ ንጉስ ......እያሉ ያነ ቫሉ፡፡

ሊቃውንቱ ይዘምራሉ" ጊዮርጊስ ረባን ዘሀገረ ኢትዮጰያ ስህን
ንስእለከ በብርሀን ከመ ትናዝዘነ ነዓ እምክቡደ ሀዘን" ይላሉ..
እምየ ሚኒሊክ የንግስና ልብሳቸውን አውልቀዉ ቃልኪዳናቸውን ከጊዮርጊስ ጋር ሊያደርጉ '' ጊዮርጊስ ሆይ ተራዳን'' እያሉ ከቤተመቅደሱ ፊት ለፊት ታጥቀው ተምበርክከው ይማፀናሉ::
ጀግኒት ጣሂቱ
"አድህነኒ እግዚኦ እምፃርየ
ወአንግፈኒ እም እለ ቆሙ ላእልየ
አቤቱ ከጠላቶቻችን አድነን
በላያችንም ከቆሙት አስጥለን "
እያለች ፈጣሪን ትማፀናለች


እንዳይነጋ የለም ነጋ እምየ ሰራዊታቸውን ሰበሰቡ በአረጋዊው ካህን አሰባረኩ ፤ከሰራዊቱ ጋር በማርያም ስም ተማማሉ፡፡
አድዋ ላይ የዘመተው አሁን አዲስአበባ ያለው የፒያሳውን ጊዮርጊስ በመምህሬ ካሳሁን አስከብረው(አስይዘው ) በጀብድ እና በጀግንነት የልዳውን ጊዮርጊስን ይዘው ወረዱ፡፡
ጦርነቱ ተጀመረ፡



… የአድዋ ጦርነት በ1888 ዓመተ ምሕረት በየካቲት 23 ቀን እሑድ ጦርነት ተዠመረ፡፡ ወዲያው የኢጣሊያ የጦር አዛዥ ያገር ተወላጅን ጦር እፊት አስቀድሞ ሲዋጋ በኋላ የራስ መንገሻና የራስ ሚካኤል የዋግ ሥዩም ጓንጉል ወታደሮች ከበው በጥይት ስለ ቆሏቸው ይበልጦቹ እጦርነቱ ላይ ሞቱ፡፡ ገሚሶቹ ዐውቀው እጃቸውን ሲሰጡ የቀሩት ደግሞ ወዳልተነካው ጦር ወደ ጄኔራል አርሞንዲ ሠራዊት በሽሽት እየሄዱ ተደባለቁ፡፡1050 ኪሎሜትሮችን በባዶ እግራቸው ተጉዘው የጊዮርጊስን ታቦት አክብረው ጣሊያንን ሲዋጉ የነበሩት ካህኑ ካሳሁን የተሸከሙት የልዳው ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተቀምጦ የጣሊያንን መድፍ ያኮላሻል ፣ታንክ ያከሽፍል የጦር ጀቶችን ከሰማይ ወደምድር ዶጋ አመድ ያደርጋል ፤ በዛን ጊዜ ከአለም የጦር ሜካናይዝ ከፍተኛ የነበሩትን የጣሊያንን ጦር በ 4 ሰአት ውስጥ መድረሻውን አሳጣው፡፡
የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊትም እያቅራራና እየፎከረ ወደ ፊት አልፎ ገስሶ ከሚባለው ጉብታ ላይ ደርሶ እንደ ገና ተጋጠማቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ዠግናው ፊታውራሪ ገበየሁ ከሠራዊታቸው ተለይተው ጠላት መካከል ገብተው ከቀኛዝማች ታፈሰ ጋራ እየፎከሩ የጠላትን አንገት በጎራዴ ሲቆርጡ በጥይት ተመተው ወደቁ፡፡
ንጉሠ ነገሥቱ ዐፄ ምኒልክ የጦር ወታደራቸውን በሚያበረታታ ቃል ሲያደፋፍሩ እንዲሁም እቴጌ ጣይቱ እንደ ወንድ በጦርነቱ መካከል እየተላለፉ የቆሰለውን ሲያነሱ ለተጠማው መጠጥ ለተራበው ምግብ ሲያሰጡ ዋሉ፡፡ እነሊቀ መኳስ አባተ እነራስ አሉላ እነበጅሮንድ ባልቻ እነደጃች በሻኽ አቦዬና የቀሩትም የጥንት ወታደሮች በመድፍና በጠመንዣ በዠግንነት ሲዋጉ የጠመንዣውና የመድፉ ጩኸት ከልክ ያለፈ ነበር ይላል ታሪክ፡፡
የኢጣሊያንንም ወታደር ከበው እየተፏከሩ በጥይትና በጎራዴ ሲደበድቡት የኢጣሊያ ጦር በዠግንነት አራት ሰዓት ከተዋጋ በኋላ ሽሽት ዠመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያውያን እየተከተተሉ ሲወጉት አዝማቹ ጄኔራል አልቤርቶኒ ተቀምጦበት የነበረው በቅሎ ተመቶ ወደቀ፡፡ ኢትዮጵያውያን ደርሰውም ጄኔራሉን ማረኩት፡፡
የአንደኛው ክፍል ጦር አዛዡ ተማርኮ ሠራዊቱ በጭራሽ ከጠፋ በኋላ ሁለተኛው ክፍል የጦር ሠራዊት ራአዮ ከሚባለው ስፍራ ላይ ሆኖ ካራት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ የሦስተኛውን ክፍል የጄኔራል ኤሌናን ጦር ጨምሮ ተዋግቶ በመጨረሻ የጦር አዛዡ ጄኔራል አሪሞንዲ እዚያው እጦርነቱ ላይ ሞቶ ተገኘ፡፡
ከዚህም በኋላ በመጨረሻ ያለው የኢጣሊያ ጦር በተለይ ማርያም ሸዊቶ ከሚባለው ስፍራ ላይ ተጋጥሞ ከቀድሞው የበለጠ ጦርነት ተደረገ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻው ድል የሚፈጸምበት ለመሆኑ የሁለቱም የጦር ሠራዊት ተደባልቆ በጨበጣ በሚዋጉበት ጊዜ በጨበጣ በሚደረገው ዘመቻ ከኢጣሊያኖች ይልቅ ኢትዮጵያውያን በጎራዴ አነዛዘር የቀለጠፉ ነበሩ፡፡
በዚህ ጊዜ ኢጣሊያኖች ገሚሶቹ ሲሞቱ የቀሩት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያውያን ደግነው ይተኩሱበት የነበረውን ብረት አፈሙዙን ጨብጠው ሰደፉን ወደ ሰማይ እየሰቀሉ ተማረኩ፡፡ ድሉም በማያወላውል አኳኋን የኢትዮጵያ ሆኖ ጦርነቱ በ1888 ዓመተ ምሕረት በዚህ በየካቲት 23 ቀን ተጀምሮ በዚሁ እለት በታላቅ ጀግንነት ተፈጸመ፡፡አለምንም ጉድ አሰኘ ለመላው የነጭ ህዝቦች አሁን ሊቀበሉት የሚከብዳቸው ዉረደትን አከናነበ፡፡ እንዴት ሆነ ብለው ዛሬም ድረስ ይገረማሉ ??? የጀርመኑ ፀሀፊ ራይመድ በመገረም ታምር ነው በማለት ፅፎታል፤ አውን ታምር ነው፤በ 1970ወቹ አንድ የጣሊያን ፀሀፊ እንዲህ አለ የሀገሬን የጣሊያንን ወታደር የፈጀው በሚበር በነጭ ፈረስ የሆነ አንድ ሃያል ነው ይህንንም በአይናችን አይተናል ሀይሉም እጅግ ከባድ ነበር ይላል፡፡

እውነትም ለማመን የሚከብድ ታምር በባዶ እግር የተሰራ የሀገር ፍቅር ጀብድ ነው፡፡
አወን አ ድ ዋ፡
፡ የሚኒሊክ የመሪነት ጥበብ ነው፤
የራስ መኮነን ራስነት የተገለጠበት፤
የባልቻ አባ ነብሶ ወኔ የተመ ሰከረበት ፤ ያሉላ አባ ነጋ ጀግንነት የታየበት ፤ የአያቶቻችን የመንፈስና የእምነት ልእልና የተገለጠበት
የጣይቱ የሴትነት እልህ ጥጉ የታየበት፤ የኢትዮያውያን የማንነት አሻራችን በአባቶቻችን ደም ና አጥንት በማይጠፋ የደም ቀለም ተፃፎ በአለም ህዝብ ዘንድ የሚነበብበት ፤የክብርና የጀግንነት ወኔ እና አልደፈር ባይነት የተገለጠበት፤ የድል አጥቢያ የብርሀን ጮራ የታየበት አሁን ላለንበት አንፃራዊ ያልተመረዘ ማንነት ምክኒያት ያ የአድዋ ገድል ነው፡፡
አውን አባቶቻችን አኩረተውናል እኛስ እንዳባቶቻችን በዘመናችን ድል አድርገን ልጆቻችን እናኮራ ይሆን ?????

ይህ ታሪካዊት ኢትዮጵያ ነው ያላችሁን አስተያየት @Abelbalehager ላይ አድርሱኝ።
@ethioabesha
@ethioabesha
@ethioabesha