Get Mystery Box with random crypto!

#አትወድህም ቢሉህ ውሸታም በላቸው መዉደድ ማለት ልኩ ፈፅሞአልገባቸው ግን መውደድ ምንድን ነው? ፍ | የሬጌው👑 ንጉስ🇪🇹™

#አትወድህም ቢሉህ ውሸታም በላቸው
መዉደድ ማለት ልኩ ፈፅሞአልገባቸው
ግን መውደድ ምንድን ነው?
ፍቅር የሚሉት ጉድ መኖርያው ከየት ነው?
እኔ ምለዉ ዓለሜ
ግን የምር ሲታሰብ ፍቅር እዉነት ጉድ ነው?
እንጃ!
ብቻ የማያቁት አለም ያላዩት ገፅታ
ሲታገሉት ቢውሉ ፍፁም ማይረታ
በልባችን ሀገር ከትሞ የሚኖር
ከራስ ግዞት ዓለም ፈፅሞ ሚያቃቅር
ፍቅር።
#እና እንደነገርኩ
ሺ ነገር ቢነግሩ ፈፅሞ አትስማቸው
በኔና ባንተ ዓለም
ወሬ አይታለም
የሚነገር ሁሉ ሚሰማ አይደለም
አይን ባለቀሰ ልብ ተከፍቶ አያድርም
በውሸታም እሳት ፍቅር አይጎረናም።
#እናልህ…………
ከመውደድም በላይ እኔ አፈቅርሀለው
ላፍቃሪ ምሳሌ በሰብልዬ ምትክ እተካልሀለው
ግና እኔ ሰብለን ሆኜ በእዜር ድርሰት ዓለም
አደራውን ጌታ አንተን በዛብህ አርጎ ይፃፍህ ግድ የለም።
#እናልህ አካሌ
ከሰዎችህ ይልቅ እኔ እሻልሀለው
ፍቅርን ከቃል በላይ ኖሬ አሳይሀለው
አትወድህም ላሉህ ለኚያ ጥላ ቢሶች ጥላ ለሌላቸው
ጥላህ ሆኜ ኖሬ ይክሰም ተንኮላቸው።

( ሰሎሜ መብራቱ )