Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ etyokenaandkald — ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ etyokenaandkald — ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ
የሰርጥ አድራሻ: @etyokenaandkald
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 191
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም ፣ ቅኔእና ቀልድየሚለቀቅበት ቻናል ነው
የሚለቀቅ ግጥም እና ቅኔ ካሎት እና እዚህ ላይ አናግሩን

👇👇👇👇👇
👉 @ethio_kene👈
👆👆👆👆👆
ለአድ ሚን በዚ ላይ አናግሩን
@eyobnagn

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-01-29 22:26:47 (....ስላንቺ....)
(ቢኒያም ወጋየሁ)
.
.
እቴ....ፈቅደሽ
እኔን ክፉ አልምደሽ
እቴ....ወደሽ
እኔን ልቤን ክደሽ
ከኔ.....
ጠፋው አንቺ ሄደሽ
... ታዲያ ለኔ...
ከመፋቀር ለተጣጣው
... ታዲያ ለኔ...
በመገፋት ለተቀጣው
... ለህይወቴ...
ይህ ነው ዕጣው?
ታዲያ ላንቺ...
በደስታ ጥግ ለተከበብሽ
ታዲያ ላንቺ...
በማጠውለግ ዙር ለከበብሽ
በፅናትሽ አንቺ ላበብሽ
ፍቀጂልኝ ልሁን ልብሽ።
ከዛማ
ወደ ጻማ
ወደ ፍጥረት:ፍቅር አበው:ሕልውና
ለአርዮስ:የተቃርኖ:ቅድስና
አሳረፈኝ:ከጥጉ ላይ:ይህ ጎዳና
ለምዶሽ አንቺን:በርኖስ ሆነኝ:የእግርሽ ዳና
እንደ ሀገር.....እንደ ማገር
እንደ እውነት...እንደ ክህነት
የሌለሽ ቃል:የስማዚያ:ብኩንነት
ስም ያሳጣሽ:የራሙኤል:ስም ጭፍራነት
አንቺ....
የዘመኔ:ረቂቅ እውነት
ሆነሽ ሳለ
ቀን ያሳያል:መሄድሽን:እየሳለ

የመሄድሽ:ሽንቁር ችንካር:ተቸክሎ
የመምጣትሽ:ግማ እውነት:ተከልክሎ
እንዴት ልየው:ስሜታችን:ዳስ አክሎ
መልመድ"መግመድ":ሆኖ ቢኖር:ባልተከፋው
በልኬቴ:በተሰፋሽ:በልኬትሽ:በተሰፋው
ለአንደበቴ:ይህ ነው ተስፋው
ስትርቂ ግን
ከመኖሬ ተሰረዝኩኝ:እኔ ከኔ ባንቺ ጠፋው።
እቴ...
እኔን ክፋ አልምደሽ
እኔን ልቤን ክደሽ
ጠፋው አንቺ ሄደሽ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
@yotorr
154 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 13:47:21
190 views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 07:11:18 እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም በጤና አደረሳቹ በአሉ የሰላም የመተሳሰብ የአብሮነት የፍቅር ያድርግልን መልካም በአል
196 views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 21:00:34 አፍቄሜሌፅ (የፍቅር ቃል እድሜ)
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ፍቅርን ያህል ነገር
ተሸክሜ ስኖር ፣ በልቤ ትከሻ
"ቃል አጠረኝ" የሚል
ቃል ካፌ አይወጣም ፣ ላወድስሽ ስሻ።
እንደውም ሳፈቅር ፣ ቃል ነው የሚተርፈኝ
እንኳንስ ቃል ሊያጥረኝ
ሁሉ ያጥርብኛል
በልብሽ ቅርፅ ውስጥ ፣ መውደድሽ ሲያገዝፈኝ
ቃልም ነው በመንፈስ
ልሳን እየሰጠ ፣ የሚያስለፈልፈኝ ።
ሻምጵራ ቅራንጳ
ወዘ ትሩሩጳ
አፍረንትረን ደስቴ
ፄፃቱ ጳፃቴ
ወኡዝ ሀአሪከ
አዝወረ ነባከ
ፊፀአ ነአቱ
ጀነወ ርዕቱ
ናፃ ፄላሟሜ
እናልሽ አለሜ
አዲስ ፊደል ባልቀርፅ ፣ አዲስ ቃል ቀምሜ
ትርጉሙ እንዲገባሽ
የልሳን ቃሎቼን ፣ በአንዲት ቃል ተርጉሜ
"አፍቄሜሌፅ" አልኩሽ!
አፍቄሜሌፅ ማለት ፣ በኔ ትርጓሜ
ሁሉ ያጥራል እንጂ
አያጥርም ማለት ነው ፣ የፍቅር ቃል እድሜ።
።።።።።።።
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ሰፊ ያልሁት አለም ፣ ባንድ እርምጃ አለቀ
ሳልሄደው ሚደክመኝ...
ተራራና ጋራው ፣ ከግሬ ስር ጠለቀ።
"ሩቅ" ያልሁት ሰማይ..
ሩቅ የሚመስለኝ ፣ ነካሁት በስንዝር
ጨረቃና ፀሀይ....
ከኮከብ ያንሳሉ ፣ ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር።
.......................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ንጉስን ከዙፋን ፣ ማርከው የሚያወርዱ
የሀያላንን አቅም ፣ በጥቅሻ ሚያርዱ
ቆነጃጅት ሴቶች ...
"ቃል አጠረኝ" በሚል ቃላት የተሞሉ
ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር..
ቃል ተገኝቶላቸው ፣ "ፋንጋዎች" ተባሉ።
.........................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
"ቃል አጠረኝ "በሚል...
ባፍቃሪ አንደበት ፣ ቃል ተትረፈረፈ
ሁሉን አሳንሶ...
በልቡ ቅርፅ ውስጥ ፣ ፍቅሩን አገዘፈ
አለሙን ሰርዞ ፣ ፍቅሩን ብቻ ፃፈ!!!
..........................................
ሳፈቅርሽ ይህን አልኩ...
ፍቅርን ተሸክሞ ፣ የሚኖር ልቦና
ሁሉም ከፍቅርሽ ስር ፣ መሆኑን አውቅና
አንቺን ለማወደስ .፣..እኔም ቃል ያጥረኛል
"ቃል አጠረኝ "ማለት...
ቃል እንደሆነ ግን ፣ ፍቅርሽ ይነግረኛል!!!
ሻምጵራ ቅራንጳ
ወዘ ትሩሩጳ
አፍረንትረን ደስቴ
ፄፃቱ ጳፃቴ
ወኡዝ ሀአሪከ
አዝወረ ነባከ
ፊፀአ ነአቱ
ጀነወ ርዕቱ
ናፃ ፄላሟሜ
እናልሽ አለሜ
አንደበት ዝም ቢል
ዝም አይልም አይኔ ፣ ዝም አይልም ጥርሴ
ቃል አለው ጆሮዬ ፣ ዝም ቢል ምላሴ።
ዝም አይልም እጄ ፣ ዝም አይልም እግሬ
እኔ ቃል ቢያጥረኝም
ሰማይና ምድሩ
ፈጣሪና ፍጡሩ
ለፍቅር ቃል አለው ፣ ይናገራል ፍቅሬ።
።።።።።
ትርጉም ብንሰጠው
ጥላቻ በራሱ ፣ ለፍቅር አለው ቋንቋ
"አፍቄሜሌፅ" አልኩሽ
የፍቅር ቃል እድሜ
ከዘላለም የሚያልፍ ፣ ዘላለም ነው በቃ።
ሀዘሩ ጣሪቃ
ሉፋሴ ጰኑቃ
ሪድዋ ሸዛጨ
አገቀ ጠየጨ

@BelayBekelaWeyaa
270 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 15:49:29 #ማነሽ?
ብቻ አላቅም ላቅም አልፈልግም
አዎ!አልፈልግም አልጨናነቅም
ግን ማነሽ?
ማወቅን ፈርቼ
መጠየቅ ጠልቼ
ማወቅ ብፈልግም
አልጨናነቅም
ለምን?እንዳትይኝ ምክንያቱን አላቅም
አንቺን ፈርቼ ነው
አንቺን ወጅጄሽ ነው
ማወቅ ጠልቼ ነው...........ምናምን
ብቻ ብቻ ብቻ መልስ የለኝም ላንቺ
ጥያቄ ብቻ ነው
አንቺን ለመጠየቅ አስቤ ግን
ፈራው
መልሱ አንቺ ጋርነው በልቤ ውስጥ
ያለው
ማነሽ ?እንዳልልሽ እኔእራሴ ማን ነኝ
ብዬ አስባለው
ጥያቄውን ይዤ አንቺ ጋር ለመድረስ
ምላሽሽ ይቆየኝ እኔ ማን እንደሆንኩ
አውቄ ልመለስ
~~~~~~~~||~~~~~~~~
እዮብ ደጀኔ ሙሉ አለም
@etyokenaAndkald
221 views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-15 13:56:00 አንቺ ባለሽበት ፣ሚባለውን እንጃ
እኔ ባለሁበት ፣ ወሬ እንደጠብ መንጃ
የታጠቀ ሞልቷል ፣ ቢደላም ቢከፋም
ጆሮ አይሰማው የለም
የሚበላ እንጂ ፣ የሚባል አይጠፋም !
#ይባላል !
።።
ለምሳሌ ያህል
ትጥቃችን ባያልፍም
ከዱላ ከድንጋይ ፣ ግፋ ቢል ከክላሽ
ወዮለት ለጠላት ፣ ኋላ እንዳይበላሽ
ኒውክለር ሲመካ
አደቧን ትያዝ ግብፅ ፣ ትረፍ አሜሪካ
አላርፍም ካሉ ግን ፣ ወየው ለሁለቱም
ባለም ፊት ፈስ በፈስ
እንዳናደርጋቸው
በእጃችን ነው ያለው ፣ ደብተራም መተቱም
ይባላል
፣፣፣፣
ለምሳሌ ያህል
ሰማንያ ሺህ ዳቦ ፣ ሊያውም በአንድ ቀን
ሊጋገር ነው ሲሉን ፣
በምን መብራት ብለን ፣ አናውቅም ጠይቀን
እንዲሁ በማመን ፣ ሆዳችን ይሞላል
በመሪ አንደበት
ደም ያፀናው ሰንደቅ ፣ ጨርቅ ነው ይባላል።
።።።
እኔ ባለሁበት ፣ በመኖሬያዬ ሀገር
ከፀሐይዋ በታች ፣ የማይባል ነገር
አንዳች አይገኝም ፣ ሁሉ አፉን ያክላል
የሚለው ያጣ ሰው
የተባለን ነገር ፣ "አይባልም "ይላል
።።
የሆነው ሆነና ፣ ባለሁበት ሀገር
የማይባል ነገር
አጋጥሞኝ አያውቅም
ለምሳሌ ያህል
አባይ በአምስ አመት
ተገድቦ ያልቃል
በኢትዮጵያ ምድር ፣ ፀሀይ አትጠልቅም
አስራ አንድ ፐርሰንት
ሀገሪቱ አድጋለች ፣ በኑሮ ብንደቅም
ስልጣን የህዝብ ነው ፣ ግን ለህዝቡ አንለቅም
ይባላል

ለምሳሌ ያህል
ባይቆጥራቸው እንጂ፣ ዘንግቶ ምናልባት
ጠቢቡ ሶሎሞን
ከጠቢቡ በላይ ፣ አይበልጥም በእቁባት
#ይባላል
በላይ በቀለ ወያ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
196 views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-15 13:51:27 ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ።
~
ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የዕንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።

የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።

የምድር የቀላይ ጥፋት
በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው
ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ ።

ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።

የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅ
በዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ።

ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ
ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ።

በአበባው መላኩ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
175 views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-15 13:50:09 ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ችግሮችን ማስወገድ ተማር!!

ጥበብ ሕይወትን የምንቀዝፍባቸው ክህሎቶች መለኪያ ነው። ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ከተፈጠሩ በኋላ ከመፍታት የተሻለ ጥበብን ይጠይቃል፡፡እውነታው ሕይወት ከባድ መሆኗ ነው፡፡ ችግሮች በሁሉም አቅጣጫ በየጊዜው ይተኮሱብሃል፡፡ እጣ ፈንታ መርገጫህ ስር ጉድጓዶችን ልትቆፍርብህ ወይም መሿለኪያዎችህን ልትዘጋብህ ትችላለች። ይህንን መቀየር አትችልም፡፡ አስቀድሞ አደጋ ያለው የት ጋር እንደሆነ ከተረዳህ ግን ወዳንተ እንዳይመጣ ለማጠር እድል ይኖርሃል፡፡ በዚህ መንገድ መሰናክሎችን ሁሉ ማስወገድ ትችላለህ፡፡ ይህንን ሀሳብ አልበር አንስታይን እንዲህ ያስቀምጠዋል፡፡ “ጎበዝ ሰው ችግሮችን ይፈታል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ችግሮችን ያስወግዳል፡፡”

ችግሩ ችግሮችን ማስወገድም የሚወደስ ነገር አለመሆኑ ነው፡፡ ሁለት ፊልሞችን አስብ፡፡
1.በመጀመሪያው ፊልም ውስጥ አንድ መርከብ ከበረዶ ክምር ጋር መጠነኛ ግጭት ይገጥመዋል፡፡ መርከቡም ይሰምጣል። በዚህ ጊዜ የመርከቧ ካፒቴን ራስ ወዳድነት በሌለበት መልኩ ራሱን አበርትቶ ተሳፋሪዎቹን ሁሉ ከመስመጥ ይታደጋቸዋል፡፡ መርከቧ ለዘለዓለሙ ከመሰወሯ ከደቂቃዎች በፊት ሁሉንም ተጓዦች በማዳን ከጀልባው ላይ ዘሎ ወደ ሕይወት አድኑ ቦቴ ውስጥ በመግባት የመጨረሻው ሰው ነበር።

2.በሁለተኛው ፊልም ውስጥ ደግሞ እንዲህ ሆነ፡፡ መርከበኛው መርከቧ ከበረዶ ክምሩ ጋር ከመጋጨቷ በፊት አስተውሎ በቂ ርቀት ላይ እንድትቆም አደረጋት፡፡

የትኛውን ፊልም ለማየት የበለጠ ትከፍላለህ?በእርግጠኝነት የመጀመሪያውን ፊልም፡፡ ሌላ ጥያቄ ደግሞ ላንሳልህ፡፡ አንተ በመርከቧ ውስጥ ተጓዥ ብትሆን ኖሮ በየትኛው ፊልም ሁኔታ ውስጥ መሆንን ትመርጣለህ? ያለ ምንም ጥርጥር ሁለተኛው ፊልምን።

እነዚህ ምሳሌዎች እውነተኛ ገጠመኞች ናቸው ብለን እናስብ፡፡ ቀጥሎ ምን ይፈጠራል? የመጀመሪያው ፊልም ውስጥ ያለው ካፒቴን የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ይጋበዛል። ምናልባት መርከበኛነቱን ትቶ አነቃቂ ንግግሮችን እያደረገ ሕይወቱን መምራት ሊጀምር ይችላል። መንገድም በስሙ ሊሰየምለት ይችላል፡፡ ልጆቹም (ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ) በአባታቸው ይኮራሉ፡፡ የሁለተኛው ፊልም ውስጥ የሳልነው ካፒቴንስ? ከስራው በጡረታ እስኪገለል ድረስ ችግሮች እንዳይከሰቱ በቅድመ ጥንቃቄ የመርከበኝነት ስራውን ይሰራል። መርሁም “ከ20 ጫማ እርቀት ላይ ልታልፈው የምትፈራውን ነገር በ500 ጫማ እርቀህ እለፈው” የሚለው የቻርሊ ሙገር የሕይወት መርህ ይሆናል፡፡

እንግዲህ ተመልከት፡- የሁለተኛው ፊልም ካፒቴን ከመጀመሪያው ፊልም ካፒቴን በሚታይ መልኩ የሚሻል ቢሆንም እኛ የምናከብረውና የምናደንቀው ግን የመጀመሪያውን ፊልም ካፒቴን ነው፡፡ ለምን? በቅድመ ጥንቃቄ የሚመጣ ስኬት ለውጪው ዓለም እይታ የሚጋለጥ አይሆንም፡፡

ጋዜጠኞች አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳይመጡ ካረጉ በሳል ሰዎች ይልቅ ችገሮችን የቀለበሱ የሥራ መሪዎችን ነው የሚያሞካሹት ።የቅድመ ጥንቃቄ ስኬቶች ለውጪው ዓለም የማይታዩ ባለመሆናቸው ምክንያት ሳይታዩና ሳይወደሱ ይኖራሉ፡፡ የእንደዚህ አይነት ስኬቶት ባለቤቶችን ጥበብ የሚያውቁት በእሱ ዙሪያ ያሉ የቡድኑ አባላት ብቻ ናቸው። እነሱም ቢሆን በተወሰኑ መልኩ ቢያውቁት ነው፡፡

የአንተስ ሕይወት? አመንክም አላመንክም ከስኬቶችህ ሁሉ 50% የሚሆኑት የቅድመ መከላከል ጥንቃቄህ ውጤቶች ናቸው፡፡ ሁላችንም እንደምናደርገው ሁሉ አንተም አንዳንድ ነገሮችን በንዝህላልነት ልታደርግ ትችላለህ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖም ግን ስህተቶችን ላለመስራት ሁልጊዜም ትጠነቀቃለህ፡፡ በአርቆ · አሳቢነት ያስወገድካቸውን በስራህ፣ በትዳርህ፣ በትምህርትህ ወይም በሌላ የሕይወትህ ዘርፍ ሊገጥሙህ የነበሩ ችግሮችን አስብ፡፡

ጥንቃቄ (prevention) ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ቅድመ ጥንቃቄ በባህሪው ቀድሞ ማየት (imagination) ይጠይቃል ቀድሞ መረዳትና የሚመጣውን መገመት ደግሞ ብዙውን ጊዜ አዛብተን የምንረዳቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ አዲስ ሀሳብ አያመጣልንም፡፡ በዓይነ ህሊና ማየት (imagination) ማለት የመጨረሻው ፍትሃዊ ነገር ሆኖ እስክናይ ድረስ ሊሆኑ የሚችሉት ነገሮች ውጤቶችና የመፈጠር እድላቸውን ሁሉ እንዲያስብ አዕምሯችንን ማሰራት ማለት ነው፡፡ ስለሆነም አስቀድሞ ማየትና መገመት ከባድ ስራ ነው።

በተለይ ጉዳዩ ስለአደገኛ ችግሮች ሲሆን ደግሞ ቀድሞ የመገመት ሥራ የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ ሊመጡ እድል ባላቸው ችግሮች ላይ ሁሉ እየተጠነቀቅክ መኖር ይጠበቅብሃል? ይህስ ሁልጊዜ የተጨናነቀ ሰው ሆነህ እንድትኖር አያደርግህም? ተሞክሮዎች የሚያሳዩት እንደዚያ እንዳልሆነ ነው፡፡ ቻርሊ ሙገር እንዲህ ይላል “በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የሚመጠብኝን አደጋዎች ስገምት ኖሬያለሁ፡፡ ሁልጊዜ ይሄንን እያሰብኩ፣ አደጋዎች ከመጡም እንዴት መመከት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ መኖሬ ደስተኛ እንዳልሆን አላደረገኝም፡፡”

ሮልፍ ዶልቢ
The art of good life


ሀገራችን እንደዚህ ውጥንቁጡ የወጣ ችግር ውስጥ የገባችው አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል የሚችሉ በሳል ሰዎች ስለሌሏት ይመሰለኛል።ጎበዝ ጦረኞች ያስፈልጉናል ግን ከዛ የበለጠ ጦርነት እንዳይከሰት ቀድመው በሳል እርምጃ የሚወስዱ መሪዎች ያስፈልጉናል። እርዳታ የሚሰበስቡ አክቲቪስቶች ቢያስፈልጉንም ከዛ የበለጠ ኢኮኖሚያችንን በዘላቂነት የሚያሻሽሉ ፖሊሲዎችን የሚቀርፁ ሙሁራን ያስፈልጉናል።

@Rasen_Felga100
@Rasen_Felga100
163 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-15 13:49:45 9 ነኛ ክፍል ላይ ሁለቴ የወደቀው ጀለስህን ስንተኛ ክፍል ነህ ሲሉት




የ 9ነኛ ክፍል የ3ተኛ አመት ተማሪ
163 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-15 13:49:44 በአውስትራሊያ አንድ ተማሪ አርፍዶ ሲመጣ እንደ ቅጣት ደረቅ ዳቦ እንዲበላ አርገዋል

ይህንን በኢትዮጲያ ሞክረነው



አስተማሪዎችም አርፍደው መምጣት ጀመሩ
154 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ