Get Mystery Box with random crypto!

+ ለክረምት ፲፩ኛ እሑድ (ከነሐሴ ፳፪-፳፮) + እማኅበር እስከ አብርሃም ዕጒለቋዓት ደሰያት «ዓይ | ❤️ዕፀ ፍህሶ ወዕፀ መአዛ❤️

+ ለክረምት ፲፩ኛ እሑድ (ከነሐሴ ፳፪-፳፮) +
እማኅበር እስከ አብርሃም ዕጒለቋዓት ደሰያት «ዓይነ ኵሉ» ይትበሃል።

መዝሙር:- «ይሁበነ ዝናመ በጊዜሁ፣ ይሁበነ ዝናመ በጊዜሁ፣ ወይሁበነ እክለ በረከት፤ ያርኁ ክረምተ ይገብር ምሕረተ ወይሁበነ ዝናመ ዝናመ በረከት፤ [ይ] ከሢቶ ዓይኖ ሰፊሆ የማኖ፤ ይፌኑ ሣህሎ ወበዘአእመረ ይሴባሕ፤ [ይ] ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ፤ ወብውህ ሎቱ ይኅድግ ኃጢአተ፤ [ይ] ዓይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያሁ፤ ይሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ።

❖ መልእክታት:-
➊· ዕብራውያን ፫ : ፩-ፍጻሜ /3 : 1-ፍጻሜ
➋· ያዕቆብ ፭ : ፩ - ፲፪ /5 : 1 - 12
➌· የሐዋርያት ሥራ ፳፪ : ፩ - ፳፪ /22:1-22

❖ ምስባክ ዘቅዳሴ
ዓይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ።
አንተ ትሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ።
ትሰፍሕ የማንከ ወታጸግብ ለኲሉ እንስሳ ዘበሥርዓትከ።
ትርጉም፦
የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤
አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ።
አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።
(መዝ ፻፵፬ : ፲፭ - ፲፮ /144:15-16)

❖ ወንጌል ዘቅዳሴ
ዮሐንስ ፮ : ፵፩-ፍጻሜ /6:41-ፍጻሜ
@፵፩
እንግዲህ አይሁድ። ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ ስላለ ስለ እርሱ አንጐራጐሩና።
፵፪
አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ። ከሰማይ ወርጃለሁ እንዴት ይላል? አሉ።
፵፫
ኢየሱስ መለሰ አላቸውም። እርስ በርሳችሁ አታንጐራጕሩ።
፵፬
የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
፵፭
ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።
፵፮
አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን ዐይቶአል።
፵፯
እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።
፵፰
የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።
፵፱
አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤

ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው።
፶፩
ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።
፶፪
እንግዲህ አይሁድ። ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል? ብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ።
፶፫
ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።
፶፬
ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
፶፭
ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።
፶፮
ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
፶፯
ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።
፶፰
ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል
፶፱
በቅፍርናሆም ሲያስተምር ይህን በምኵራብ አለ።

ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ። ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ።
፷፩
ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው። ይህ ያሰናክላችኋልን?
፷፪
እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?
፷፫
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።
፷፬
ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ። ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ከመጀመሪያ ያውቅ ነበርና።
፷፭
ደግሞ። ስለዚህ አልኋችሁ፥ ከአብ የተሠጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ።
፷፮
ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሔዱም።
፷፯
ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ። እናንተ ደግሞ ልትሔዱ ትወዳላችሁን? አለ።
፷፰
ስምዖን ጴጥሮስ። ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሔዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤
፷፱
እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።

ኢየሱስም። እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።
፸፩
ስለ ስምዖንም ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ ተናገረ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነ እርሱ አሳልፎ ይሠጠው ዘንድ አለውና።

✞ ቅዳሴ - ዘኤጲፋንዮስ (ዐቢይ) - በግዕዝ ዜማ
____