Get Mystery Box with random crypto!

UTOPIANISM ጦቢያዊነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ etoyopiawi — UTOPIANISM ጦቢያዊነት U
የቴሌግራም ቻናል አርማ etoyopiawi — UTOPIANISM ጦቢያዊነት
የሰርጥ አድራሻ: @etoyopiawi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 148
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia Utopia ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-30 18:59:40
"...ስለዚህ የዚህ በሽታ እውነተኛው መድኃኒት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ታላቅ ተስፋ የተፈጸመው በክርስቶስ ሰው መሆን ነው፡፡"
130 viewsኢዮባብ, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 18:55:41 #አክራጦን ነገ ጠብቁን
110 viewsኢዮባብ, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 21:40:17 አለመኖር

መኖርም የሚጀመረው አለመኖርን ከመፍራት ነው።

....የሰው ልጆች በመጀመሪያ በውልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ የመጀመሪያው ትግላችን ከአለመኖር ጋር መታገል ነው። እርግጠኛ ነኝ ስለ ልጅ አወላለድ ሥርዓት ያስተማሯችሁ መምህሮቻችሁ የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከሚቀጥሉት አርባ አመታት በላይ የበለጠ ፋይዳ አለው ብለዋችኋል፡፡ እውነት ነው ምክንያም የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከመሞት በፊት ያለው ትልቁ የህይወት
ለውጥ ነው፡፡

በእርግጥ መምህሮቻችሁ ይህን ያስተማሯችሁ ህፃን ልጅ ሲወለድ በአግባቡ አለመተንፈሱ በአንጎሉ ዕድገት ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ትኩረት በመስጠት ነው፡፡ ለኔ ግን ከዚያም በላይ ፋይዳ አለው፡፡ ማለትም ሰው ሲወለድ የለመደው በጎ ነገር በጠቅላላ ይቀየራል። በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው ረሃብ የለም፡፡ በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው ብርድ የለም።

ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም መከራም የለም። በምቾት መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሃ ውስጥ መንሳፈፍ ነው። ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድንበት ቅፅበት ይለወጣል። መተንፈስ ግድ ይለላ። ረሃብን ለማስታገስ መጥባት እንጀምራለን፡፡ ይበርደናል ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን ለመኖር። አለበለዚያ መኖር የለም። መታን በረሃብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሃታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ።

በእናታችን ማህፀን ውስጥ የምናውቀው መኖርን ብቻ ነው። መውለድ ግን አለመኖር አመላካች ነው። ይህ ስጋት ታዲያ በህይወታችን ሙሉ የሚዘልቅ ነው። በየደረጃው በየእድሜያችን ለአለመኖር ስጋት እንደተጋለጥን እንዘልቃለን።

የምንኖርበት አለም ደግሞ የሰው ልጅ የዘመናት የአለመኖር ስጋን ለማስወገድ በመመኘት የገነባው የአኗኗር ስርዓት አለው። ይህም ስርዓት ከመወለዳችን ይረከብና። በወላጆች ዘመድ ጎረቤት ሰፈር ብሄር ቋንቋ ባህል ሃይማኖትና ልምድ ያሉበት ዓለም ከእኛ ቀድሞ ይጠብቀናል። ይህ ሁሉ ባለበት ዓለም ተወልደን በእኚህ ቀድመው በተዘጋጁ ስርዓቶች ውስጥ አለመኖርን ሸሽተን ለመኖር ስንል እንታሰራለን።
148 viewsኢዮባብ, 18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 21:56:08 #አንጨነቅ

በርግጥም ተፈጥሮአችንን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው እርሱ ነውና፥ የሚያስፈልገን ምን እንደ ኾነም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፡- “ርግጥ ነው፥ እርሱ አባታችን ነው፡፡ የምንሻቸው ነገሮችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደሚያስፈልጉን አያውቅም” ማለት እንደ ምን ይቻልሃል? የገዛ ተፈጥሮአችንን እንኳን የሚያውቅ እርሱ፣ ማወቅ ብቻም ያይደለ ይህን ተፈጥሮአችንን የፈጠረ እርሱ፣ የፈጠረ ብቻ ያይደለ እንዲህ [ያስፈልጋል የምንለው ነገር እንደሚያስፈልገው] አድርጎ የፈጠረው እርሱ፥ አንተ ራስህ ለራስህ ያስፈልገኛል ከምትለው በላይ ምን እንደሚያስፈልግህ ያውቃል፡፡ ተፈጥሮአችን እንደዚህ ያለ ነገር እንዲያስፈልገው አድርጎ የፈጠረው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ስለዚህ እርሱ አስቀድሞ ያስፈልገዋል ብሎ ፈቅዶ ለፈጠረው፣ እንደሚያስፈልገው አድርጎ ፍላጎት ለሰጠው ተፈጥሮህ አያስፈልገውም ብሎ እንደ ገና ራሱን መቃወም አይቻለውምና፥ ተፈጥሮህ የሚሻውንና አጽንቶ የሚያስፈልግህን ነገር አይነሳህም፡፡

ስለዚህ አንጨነቅ፡፡ በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና፡፡ እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና፡፡ በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል፡፡ እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም “አትጨነቅ” የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍህ ተጨማሪ ቅጣት በራስህ ላይ ከማምጣት በቀር፥ ተጨንቀህ የምታተርፈው ነገር ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየኼደ “ምን እበላለሁ?” ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየኼደም “ምን እጠጣለሁ?” ብሎ አይብከነከንም፡፡ እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቊጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን፡፡ ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን ፳፪፥፫)
163 viewsኢዮባብ, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 18:14:30 ነገረ ድክትምና
136 viewsኢዮባብ, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 21:11:14 እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዎንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ
159 viewsኢዮባብ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 20:19:41 ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ፤ ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ።
165 viewsኢዮባብ, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ