Get Mystery Box with random crypto!

አለመኖር መኖርም የሚጀመረው አለመኖርን ከመፍራት ነው። ....የሰው ልጆች በመጀመሪያ በውልደት | UTOPIANISM ጦቢያዊነት

አለመኖር

መኖርም የሚጀመረው አለመኖርን ከመፍራት ነው።

....የሰው ልጆች በመጀመሪያ በውልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ የመጀመሪያው ትግላችን ከአለመኖር ጋር መታገል ነው። እርግጠኛ ነኝ ስለ ልጅ አወላለድ ሥርዓት ያስተማሯችሁ መምህሮቻችሁ የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከሚቀጥሉት አርባ አመታት በላይ የበለጠ ፋይዳ አለው ብለዋችኋል፡፡ እውነት ነው ምክንያም የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከመሞት በፊት ያለው ትልቁ የህይወት
ለውጥ ነው፡፡

በእርግጥ መምህሮቻችሁ ይህን ያስተማሯችሁ ህፃን ልጅ ሲወለድ በአግባቡ አለመተንፈሱ በአንጎሉ ዕድገት ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ትኩረት በመስጠት ነው፡፡ ለኔ ግን ከዚያም በላይ ፋይዳ አለው፡፡ ማለትም ሰው ሲወለድ የለመደው በጎ ነገር በጠቅላላ ይቀየራል። በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው ረሃብ የለም፡፡ በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው ብርድ የለም።

ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም መከራም የለም። በምቾት መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሃ ውስጥ መንሳፈፍ ነው። ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድንበት ቅፅበት ይለወጣል። መተንፈስ ግድ ይለላ። ረሃብን ለማስታገስ መጥባት እንጀምራለን፡፡ ይበርደናል ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን ለመኖር። አለበለዚያ መኖር የለም። መታን በረሃብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሃታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ።

በእናታችን ማህፀን ውስጥ የምናውቀው መኖርን ብቻ ነው። መውለድ ግን አለመኖር አመላካች ነው። ይህ ስጋት ታዲያ በህይወታችን ሙሉ የሚዘልቅ ነው። በየደረጃው በየእድሜያችን ለአለመኖር ስጋት እንደተጋለጥን እንዘልቃለን።

የምንኖርበት አለም ደግሞ የሰው ልጅ የዘመናት የአለመኖር ስጋን ለማስወገድ በመመኘት የገነባው የአኗኗር ስርዓት አለው። ይህም ስርዓት ከመወለዳችን ይረከብና። በወላጆች ዘመድ ጎረቤት ሰፈር ብሄር ቋንቋ ባህል ሃይማኖትና ልምድ ያሉበት ዓለም ከእኛ ቀድሞ ይጠብቀናል። ይህ ሁሉ ባለበት ዓለም ተወልደን በእኚህ ቀድመው በተዘጋጁ ስርዓቶች ውስጥ አለመኖርን ሸሽተን ለመኖር ስንል እንታሰራለን።