Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ etiradioshow — ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
የቴሌግራም ቻናል አርማ etiradioshow — ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
የሰርጥ አድራሻ: @etiradioshow
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.56K
የሰርጥ መግለጫ

አትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ በሀገር ውስጥ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን ፕሮግራም
ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት ከ3-4 እና ሰኞ ምሽት ከ12-1 በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሚቀርብ

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 13:34:27 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሐረሪ ክልል መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በሐረሪ ክልል መጀመሩን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።
ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ገልጿል።
በሐረሪ ክልል የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ፤ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።
ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶችን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል እንደሚያገኙ ተገልጿል።
የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን መቀጠል ይችላሉም ተብሏል።
በሐረሪ ክልል አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ፤ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገልጿል። (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6M
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን ።
304 views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:34:21
266 views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:45:12 የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ተጀመረ


ኢትዮ ቴሌኮም ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርሟል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል አገልግሎት ቅንጦት ሳይሆን ዘመኑ የሚጠይቀው ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል።

ቴሌብር በፋይናንስ ስርአት ውስጥ ያልተካተቱ ዜጎችን በማካተት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እና ብቁ ተዋናይ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መፍትሔ መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ውጤቱም ዘመን ተሻጋሪ እንደሚሆን አመላክተዋል ።

ተገልጋዮች ኤጀንሲው ለሚሰጣቸው 27 አገልግሎቶች የሚጠየቁትን ክፍያ በቴሌብር መፈጸም ይችላሉ ተብሏል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ እንደተናገሩት የተቋሙን አሰራሮች ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሠራ ቢሆንም በተለይ ከአገልግሎት ክፍያ ጋር ያለውን የአሠራር መጓተት በቀላሉ መፍታት አልተቻለም።

አሁን የተጀመረው የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር መፈጸም የሚያስችለው አሠራር ባለጉዳዮች ያለምንም ውጣውረድ እና እንግልት በኦንላይን አገልግሎት እንዲስተናገዱ እና ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነውን የዘመኑን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብር ተጠቅመው የአገልግሎት ክፍያቸውን በቀላሉ እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በአሁኑ ወቅት 15 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ 27 ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እንዲሁም ከ7 ሺ በላይ ደንበኞች በቀን የሚያስተናግድ ሲሆን፣ በቀን በአማካይ ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ የአገልግሎት ክፍያ እያስተናገደ ይገኛል፡፡


አዲስ በተተገበረው አሰራር መሠረት ባለጉዳዮች በኤጀንሲው አገልግሎት ካገኙ በኋላ በሚላክላቸው ወይም በሚሰጣቸው የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በመጠቀም የመኪና ሽያጭ ውል፣ የስጦታ፣ የውክልና፣ የብድር፣ የማህበር ምስረታ እና ቃለ ጉባኤ የመሳሰሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በአጭር ቁጥር (*127#) መፈጸም ይችላሉ፡፡


ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6M
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን ።
298 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:45:02
306 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:06:36
328 views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:19:04
የኢትዮጲያ አየር መንገድ በ2014 በጀት አመት የነበረውን የኢኮኖሚ ቀውስ በመቋቋም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው 2014 በጀት ዓመት 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በስሩ የሚገኙ ተቋማትን የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2015 ቀጣይ አቅጣጫዎችን ገምግሟል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ባለፈው በጀት ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ቀውስ ተቋቁሞ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ 6 ሚሊየን 900 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ መንገደኞችን ያጓጓዘ ሲሆን 7 ሺህ 700 ቶን የጭነት አገልግሎት መስጠቱም ተመላክቷል፡፡

የተገኘው ገቢ ከ2013 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸርም 79 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ማሞ ምህረቱ ÷ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን እና ሌሎች ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ያስመዘገበው ውጤት የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6M
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን ።
429 views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:03:28 የአየር መንገድ ተጓዦች በሻንጣ የሚያስገቡትን የልብስና የጫማ ብዛት የሚገድብ ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ ከቀረጥ ነፃ ይገቡ የነበሩ ዕቃዎች 87 በመቶ እንዲቀንሱ ተደርጓል

መንገደኞች ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቧቸው የግል መገልገያ የሆኑ ልብስና ጫማዎች ‹‹ለአንድ ቤተሰብ ከሚያስፈልገው›› እንዳይበልጡ የሚገድብ ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ‹‹የሻንጣ ንግድ›› ለሚያካሄዱ ግለሰቦች አመቺ ሁኔታ ፈጥሮ የነበረውንና በኅዳር 2014 ዓ.ም. ዕገዳ የተጣለበትን መመርያ ቁጥር 51/2010 የሚተካ ነው፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ መነሻ፣ ሚኒስቴሩ ረቂቅ መመርያውን ወደ ፍትሕ ሚኒስቴር ልኮ እንዳስመዘገበ ገልጸው፣ በሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሸዴ ፊርማ እንደሚወጣ አስረድተዋል፡፡

በ2010 ዓ.ም. ወጥቶ ከዘጠኝ ወራት በፊት ዕገዳ የተጣለበት የቀድሞው መመርያ፣ ለግል መገልገያ የሚውሉና ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ የተዘጋጁ ልብስና ጫማዎች ብዛት ላይ ገደብ አላስቀመጠም ነበር፡፡ አሁን የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ በአንፃሩ ያለ ቀረጥ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ልብሶች፣ ጫማዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች ‹‹አንድ ቤተሰብ ከሚያስፈልገው›› መብለጥ እንደሌለባቸው ይደነግጋል፡፡ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች ደግሞ ‹‹አንድ ሰው በሚያስፈልገው›› መጠን እንደሚሆኑ መመርያው ላይ ሠፍሯል፡፡

በተጨማሪም ረቂቁ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚፈቀድላቸው የግል መገልገያ የቁሳቁስ ዓይነቶች 16 ብቻ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በቀድሞው መመርያ ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ የግል መገልገያ ዕቃዎች 130 የነበሩ ሲሆን በአዲሱ ረቂቅ ይህንን በ87 በመቶ ቀንሶታል፡፡

ከዚህ ቀደም ለግል መገልገያ ተብሎ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ይፈቀዱ የነበሩት ቴሌቪዥን፣ የማዕድ ቤት ዕቃዎች፣ የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ መጻሕፍት፣ የሕፃናትና መጫወቻና መገልገያዎች ዕቃዎች በረቂቅ መመርያው ውስጥ አልተካተቱም፡፡

መድኃኒቶች፣ የሕክምናና የፅዳት ዕቃዎች በረቂቁ ላይ የተቀመጡት ሳይዘረዘሩ በጥቅል ነው፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በ2010 ዓ.ም. በወጣው የግል መገልገያ ዕቃዎች መመርያ መሠረት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያገደው፣ መመርያው መንገደኞች ለግል መገልገያ ተብሎ ካለ ቀረጥ የሚገቡ ዕቃዎች በሕጋዊ ንግድ ላይ ኢፍትሐዊ ውድድር በመፍጠሩ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡

ከአራት ዓመት በፊት ወጥቶ በነበረው መመርያ መሠረት ተመላላሽ ነጋዴዎች በተለይ እንደ ልብስና ጫማ ያሉ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ከዱባይ፣ ከታይላንድና ከሌሎች አገሮች ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ይሸጡ ነበር፡፡

ይሁንና አልባሳትንና ጫማዎችን ለንግድ ዓላማ ለማዋል ቀረጥ ከፍለው ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ ነጋዴዎች፣ በዚህ አሠራር ምክንያት ኢፍትሐዊ ላልሆነ ውድድር እንደተጋለጡ የጉምሩክ የኮሚሽኑ የቅሬታ ክፍል ኃላፊ አቶ ዘሪሁን አሰፋ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ተመላላሽ ነጋዴዎች በሳምንት ሦስት ጊዜ በተለይ አልባሳትን ከቀረጥ ነፃ ማስገባታቸው፣ በገበያው ውስጥ ልዩነት መፍጠሩን ያስታወሱት አቶ ዘሪሁን፣ ‹‹ቀረጥ እየከፈሉ የሚያስገቡ በርካታ ነጋዴዎች እኛ ዘንድ እየመጡ መወዳደር አልቻልምን ብለው ቅሬታ አቅርበው ነበር፤›› ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከቀረጥ መሰብሰብ የነበረበት ገቢ በዚህ ምክንያት እንደታጣ አስረድተዋል፡፡

ማንኛውም መንገደኛ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተፈቀዱ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ሲያስገባ ቀረጥና ታክስ እንዲከፍል፣ የሚገባው ዕቃ ለንግድ ይውላል ተብሎ ከታመነ በቅጣት እንዲስተናገድ በኅዳር ወር ተወስኖ ነበር፡፡ ለንግድ ይውላል ተብሎ የታመነን ዕቃ ከአንድ ጊዜ በላይ ሊያስገቡ ሲሉ የተያዙ መንገደኞች፣ ጉዳያቸው በወንጀል ምርመራ እንዲታይም ኮሚሽኑ ትዕዛዝ አስተልፏል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን ይህንን ዕገዳ ሲያስተላልፍ አገልግሎቶች የሚታገዱት ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከኮሚሽኑ የተወጣጣ ኮሚቴ ጥናት አድርጎ መመርያው እስከሚሻሻል እንደሆነ ገልጾ ነበር፡፡

አሁን በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ለግል አገልግሎት የሚውሉ ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ የፎቶግራፍ ካሜራ፣ ዊልቸር፣ የእጅ ሰዓት፣ ሲጋራ፣ የፀጉር መተኮሻና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው 14 ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ፈቅዷል፡፡ እነዚህ ዕቃዎች ብዛታቸው ገደብ የተቀመጠለት ሲሆን፣ የአብዛኞቹ ብዛት አንድ ብቻ ነው፡፡

ከዚህ ውጪ መንገደኞች ‹‹አንድ ቤተሰብ ከሚያስፈልገው›› ሳይበልጥ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው ልብሶች፣ ጫማዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎችን ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ወጥተው ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በውጭ አገር ሲኖሩ የነበሩና ጓዛቸውን ጠቅልለው ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር የሚመለሱ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግለሰቦች፣ ሲገለገሉባቸው የነበሯቸውን ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ይህ ተሽከርካሪን የማያካትት ሲሆን፣ ተመላሾቹ ሌሎች ዕቃዎቻቸው ቢያንስ አንድ ዓመት ያገለገሉ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ረቂቅ መመርያው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች በስጦታ የሚላክላቸውን የግል መገልገያ ዕቃ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ከፍለው መረከብ እንደሚችሉ ደንግጓል፡፡ ስጦታው የመጣለት ሰው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሌለው ከሆነ ዕቃው የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ላይ የሚሰላ 30 በመቶ የገቢ ግብር ይከፍላል፡፡

በስጦታ የሚላከው ዕቃ የተገዛበትና እስከ ማስጫኛ ወደብ ድረስ የሚኖረው ዋጋ ከአንድ ሺሕ ዶላር መብለጥ እንደሌለበት በመመርያው ሠፍሯል፡፡ አንድ ግለሰብ በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ ስጦታ ሊቀበልም አይችልም፡፡

ከአንድ ወር በፊት የ2015 በጀት ዓመትን የጀመረው መንግሥት 786 ቢሊዮን ብር በጀት ሲያፀድቅ፣ የ309 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዳለበት አስታውቋል፡፡ የፌደራል መንግሥት ይህንን ጉድለት ለመሙላት በተጀመረው በጀት ዓመት ገቢን ለመጨመር የሚያስችሉ የታክስ ሕግ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርግ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
ምንጭ፦ሪፖርተር

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6M
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን ።
331 viewsedited  09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:00:37 የከተማ አስተዳደሩ ለማስታወቂያ በሚሆኑ ዋና ዋና 120 ቦታዎች ላይ ጨረታ ሊያወጣ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙና ለማስታወቂያ ተብለው በተለዩ ቦታዎች ላይ ጨረታ ሊያወጣ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ጨረታውን የሚያወጡት የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮና የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በአንድ ላይ ሆነው ነው፡፡ ቦታዎቹን የማዘጋጀቱ ሥራ ‹‹ወደ መጨረሻው›› እንደ ደረሰ የባለሥልጣኑ የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አዲሱ መለሰ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ቦታዎቹ ለጨረታ የሚቀርቡት ለምን ዓይነት ማስታወቂያ እንደሆነ ተለይቶ መሆኑን አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

ለጨረታ የሚቀርቡት ቦታዎች ከአያት ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከመገናኛ ወደ ቦሌ፣ ከመገናኛ በአራት ኪሎ እስከ መርካቶ በሚወስዱት ዋና መንገዶች፣ እንዲሁም ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት በቸርችል ጎዳና በሚያስወርደው ዋና መስመር እንደሆነ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ለማስታወቂያ የሚሆኑ ቦታዎችን በጨረታ ለማስተላለፍ ዝግጅት የጀመረው ሰኔ 2014 ዓ.ም. ላይ የውጭ ማስታወቂያ ደንብ ቁጥር 128/2014 በከተማዋ ካቢኔ ከፀደቀ በኋላ ነው፡፡

በከተማዋ ውስጥ ማንኛውንም ቦታ ማግኘት የሚቻለው በጨረታ አልያም በምደባ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ አዲሱ፣ ለውጭ ማስታወቂያ የሚሆን ቦታ አሰጣጥን አስመልክቶ የተጋዘጀ መመርያ እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ምክንያት እስካሁን ለውጭ ማስታወቂያ የሚሆን ቦታ ይሰጥ የነበረው በምደባ እንደነበር፣ ነገር ግን አብዛኛዎቹ በከተማዋ ውስጥ የተተከሉ የውጭ ማስታወቂያዎች ሕገወጥና ፈቃድ የሌላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በከተማው በሚገኙ 400 የማስታወቂያ ቢል ቦርዶች ጥናት አድርጎ ከ200 በላይ የሚሆኑት ፈቃድ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ ከውጭ ማስታወቂያ ደንብ መፅደቅ በኋላ፣ የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ አሰጣጥን አስመልክቶ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን የሚዘረዝር ስታንዳርድ ያወጣ መሆኑን፣ አሁን ደግሞ የውጭ ማስታወቂያ ማጫረቻ መመርያ እንዳዘጋጀ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

መመርያው ከባለድርሻ አካላት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት እንደተደረገበት የገለጹት አቶ አዲሱ፣ ‹‹እንደ ፀደቀ ነው የምንወስደው፤›› በማለት በአጭር ጊዜ ውስጥ ፀድቆ ሥራ ላይ እንደሚውል ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ አዲሱ ገለጻ፣ በዚህ መመርያ ላይ ለማስታወቂያ የሚሆኑ ቦታዎች በጨረታና በምደባ ሊሰጠጡ እንደሚችሉ ተቀምጧል፡፡ ጨረታ የሚወጣው በዋና መንገዶች ላይ በሚገኙ ቦታዎች፣ የመንግሥት ሕንፃዎችና መሠረተ ልማቶች ላይ የሚሰቀል ማስታወቂያ ነው፡፡ ዋና ዋና መንገዶች የሚባሉት በተለይም ከ20 ሜትር በላይ ስፋት ያላቸውን እንደሚመለከት አስረድተዋል፡፡

በእነዚህ ቦታዎች ላይ ማስታወቂያ መስቀል የሚፈልጉ የመንግሥት ተቋማት ጨረታ መሳተፍ እንደማይጠበቅባቸው የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ‹‹መንግሥት በልዩ ሁኔታ የሚወሰንባቸው ቦታዎች ሲኖሩ በምደባ የሚሰጥበት ሁኔታ ይኖራል፤›› ብለዋል፡፡

በመጋቢና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች የሚሰቀሉ ማስታወቂያዎች ከጨረታ ውጪ በምደባ እንደሚሰጡም አስታውቀዋል፡፡

በከተማዋ ውስጥ መሬት የሚመራውና የሚተዳደረው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በመሆኑ፣ ለጨረታ የሚቀርቡት ቦታዎች የተለዩት ከቢሮው ጋር በጋራ በመሆኑን እንደሆነ አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ የተለዩት ቦታዎች አብዛኛዎቹ ከዚህ ቀደም ማስታወቂያ ያልነበረባቸው አዲስ ቦታዎች ናቸው፡፡ የተወሰኑት ደግሞ በሕገወጥ መንገድ ማስታወቂያ ተሰቅሎባቸው የነበሩና ባለሥልጣኑ በቅርቡ ባደረገው ዘመቻ ያስለቀቃቸው እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

‹‹ቦታዎቹ ሲለዩ ምን ዓይነት ማስታወቂያ ይሰቀልባቸው የሚለውም አብሮ ተለይቷል፤›› ብለው፣ ቦታዎቹ ለቢልቦርድ ወይም ለኤሌክትሮኒክ ስክሪን ማስታወቂያ ሰሌዳነት እንደሚውሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹መመርያው ሲፀድቅ አብረን እናሳውቃለ፤›› በማለት ጨረታውን የሚያሸፉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቦታውን ለምን ያህል ጊዜ እንደሚይዙ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

ይሁንና በሊዝ ለተሰጠ መሬት የሚኖረውን ዘመን እንደማይከተልና ቦታው እንደሚሰቀልበት የማስታወቂያ ዓይነት እንደሚወሰን አስረድተዋል፡፡ ይህንንም ሲያብራሩ፣ ‹‹የቢልቦርድ ኅትመት የሚዘጋጀውና ዲጂታል ስክሪን የሚተከልበት እኩል ቦታና እኩል ጊዜ አይኖረውም፡፡ የዲጂታል ስክሪኑ ከፍተኛ ወጪ የሚወጣበትና አዲስ ቴክኖሎጂ ነው የዕድሜ ዘመኑ የተለየ ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡

በሰኔ ወር ላይ የፀደቀው የውጭ ማስታወቂያ ደንብ በመሬት፣ በሕንፃ፣ በንግድ ድርጅት፣ በአጥር ወይም በማናቸውም መሰል አካል ላይ የሚተከል፣ የሚለጠፍ ወይም በማናቸውም መንገድ የሚሠራጭ የውጭ ማስታወቂያን የሚመለከት ነው፡፡

ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ለአጭር ጊዜ የሚተከል፣ የሚለጠፍ ወይም በማናቸውም መንገድ የሚሠራጭ የውጭ ማስታወቂያ የሚተላለፈው ወቅታዊ ሁነቱ ከመከናወኑ በፊት ከአንድ ወር በላይ ላልበለጠ ጊዜ ሲሆን፣ ሁነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ከሰባት ቀናት በላይ መቆየት እንደማይችል ደንቡ ደንግጓል፡፡

የውጭ ማስታወቂያ በማናቸውም መንገድ ከማሠራጨቱ በፊት ለፈቃድ ሰጪው የአገልግሎት ክፍያ መክፈል እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ በምሥልና በጽሑፍ የሚሠራጭ የውጭ ማስታወቂያ የክፍያ ተመን በማስታወቂያ ሰሌዳው ስፋት በሜትር ካሬና በቆይታ ጊዜው የሚሰላ ሲሆን፣ በድምፅ የሚተዋወቅ የውጭ ማስታወቂያ በሚወስደው ጊዜ ይሰላል ተብሏል፡፡

በአዲሱ የከተማ አስተዳደሩ የውጭ ማስታወቂያ ደንብ ቁጥር 128/2014 መሠረት፣ በበራሪ ወረቀቶች የሚሠራጩ ማስታወቂያዎችን ጨምሮ ሁሉንም የውጭ ማስታወቂያዎች መጠቀም የሚቻለው፣ ይዘታቸው በከተማው ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ታይቶና በከተማው የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ ሲሰጥ ብቻ ነው፡፡
ምንጭ፦ሪፖርተር

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6M
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን ።
312 viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:03:27
አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽንስ ለመጪው ዘመን መለወጫ በአል የሚውሉ ፍጆታዎችን በድረገጹ ማቅረብ ሊጀምር ነው

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽንስ አ.ማ ለመጪው የዘመን መለወጫ በአል የሚሆኑ የፍጆታ እቃዎች እና የእርድ እንስሳቶች በድረገጹ ለሽያጭ እንደሚያቀርብ ገለጸ፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል በቀለ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደተናገሩት ማቾች ባሉበት ቦታ ሆነው አሸዋ ዶት ኮም (ashewa.com ) ድረገጽ አልያም የሞባይል መተገበሪያን በመጠቀም ለበዓል የሚሆኑ ምግብ ነክ የሆኑ ግብአቶችንም ሆነ ዶሮ፣ በግ፣ ፍየል እና በሬ መግዛት የሚችሉበት ስርአት ተዘጋጅቷል፡፡

ከመጪው ቅዳሜ ነሐሴ 28 2014ዓ.ም ጀምሮ ለመጪው የ2015 ዘመን መለወጫ በአል የሚሆኑ ፍጆታዎች ሽያጭ በድረገጹ እና በሞባይል መተግበሪያው አማካኝነት እንደሚጀመር አቶ ዳንኤል አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ደንበኞች የፈለጉትን ግብአትም ሆነ የእርድ እንስሳ ከገዙ በኋላ ካሉበት እንደሚደርሳቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የእርድ እንስሳት የሚገዙ ደንበኞች የመረጡት እንስሳ ከየትኛው አካባቢ የመጣ እንደሆነ ፤ ኪሎው እና የመጓጓዣ ወጪውን የተመለከቱ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ተደርጎ ስርአቱ ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽንስ አ.ማ ከተሰማራባቸው አስራ አንድ የቴክኖሎጂ ዘርፎች መካከል በድረገጹ የሚሰጠውን የምርት አቅርቦት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት በትላንትናው እለት ማስጀመሩ ይታወሳል ፡፡
ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6M
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን ።
431 viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:26:00
372 views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ