Get Mystery Box with random crypto!

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ተጀመረ ኢትዮ ቴሌኮም ከፌ | ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ተጀመረ


ኢትዮ ቴሌኮም ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርሟል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል አገልግሎት ቅንጦት ሳይሆን ዘመኑ የሚጠይቀው ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል።

ቴሌብር በፋይናንስ ስርአት ውስጥ ያልተካተቱ ዜጎችን በማካተት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እና ብቁ ተዋናይ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መፍትሔ መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ውጤቱም ዘመን ተሻጋሪ እንደሚሆን አመላክተዋል ።

ተገልጋዮች ኤጀንሲው ለሚሰጣቸው 27 አገልግሎቶች የሚጠየቁትን ክፍያ በቴሌብር መፈጸም ይችላሉ ተብሏል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ እንደተናገሩት የተቋሙን አሰራሮች ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሠራ ቢሆንም በተለይ ከአገልግሎት ክፍያ ጋር ያለውን የአሠራር መጓተት በቀላሉ መፍታት አልተቻለም።

አሁን የተጀመረው የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር መፈጸም የሚያስችለው አሠራር ባለጉዳዮች ያለምንም ውጣውረድ እና እንግልት በኦንላይን አገልግሎት እንዲስተናገዱ እና ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነውን የዘመኑን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብር ተጠቅመው የአገልግሎት ክፍያቸውን በቀላሉ እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በአሁኑ ወቅት 15 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ 27 ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እንዲሁም ከ7 ሺ በላይ ደንበኞች በቀን የሚያስተናግድ ሲሆን፣ በቀን በአማካይ ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ የአገልግሎት ክፍያ እያስተናገደ ይገኛል፡፡


አዲስ በተተገበረው አሰራር መሠረት ባለጉዳዮች በኤጀንሲው አገልግሎት ካገኙ በኋላ በሚላክላቸው ወይም በሚሰጣቸው የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በመጠቀም የመኪና ሽያጭ ውል፣ የስጦታ፣ የውክልና፣ የብድር፣ የማህበር ምስረታ እና ቃለ ጉባኤ የመሳሰሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በአጭር ቁጥር (*127#) መፈጸም ይችላሉ፡፡


ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
- በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q
- በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6M
- በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf
- በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8
ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን ።