Get Mystery Box with random crypto!

Ethio-zena

የቴሌግራም ቻናል አርማ etioz — Ethio-zena E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etioz — Ethio-zena
የሰርጥ አድራሻ: @etioz
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 994
የሰርጥ መግለጫ

💥ይህ ቻናል ስለ ኢትዮጵያና በአለም ያሉትን ሁሉ መረጃዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው
ስለተቀላቀሉ እናመሰግናለን፡፡ https://t.me/ DSSWZ9iewmU2Njc8
ለክሮስ ጥያቄ
@metioz12
#Report ላይ የሆናችሁ በዚህ ሀሳብና አስተያየት ያድርሱን።
@Techexpertt_bot
ለተለያዩ አስተያየቶች እና
መረጃዎችን ለመላክ
@tioze

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-22 13:02:23 Channel photo updated
10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 13:02:03 Channel photo removed
10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 11:27:15
የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ ኝጌሎ በ58 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

አቶ ኦኬሎ ከ1989 እስከ 1995 ዓ.ም ሶስተኛው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ሲሆን÷ ባደረባቸው ህመም ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ኦኬሎ ባለትዳር እና የ 3 ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን÷ የቀብር ስነ ስርአታቸው ዛሬ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት እየተፈፀመ ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

@etioz
@etioz
808 viewsmetitse(@etioz ), 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 10:55:17
በነገው እለት በመላው አዲስ አበባ የህዝብ ውይይት ይደረጋል ተባለ!

ነገ ረቡዕ 14/07/14 ዓ.ም በመላው አዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ወረዳዎች ፤በክ/ከተማ እንዲሁም በከተማ ደረጃ የህዝብ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡በውይይቱ በየደረጃው ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችና ሃሳቦች ይደመጣሉ ብሏል የከተማ አስተዳደሩ።

@etioz
@etioz
695 viewsmetitse(@etioz ), 07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 13:06:58
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ9ኛው የዓለም የውሃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሴኔጋል ገቡ፡፡

በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራ እና የውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)ን ያካተተው የልዑካን ቡድን በ9ኛው የዓለም የውሃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዳካር ገብቷል።

በየሦስት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም የውሃ ፎረም በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በውሃ እና በንፅህና አገልግሎት ረገድ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል እንደሆነ የታመነበት ሲሆን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው።

የመድረኩ ዋንኛ ትኩረት ድንበር ተሻጋሪ ውሃማ አካላት ዘላቂ እና ሰላማዊ አጠቃቀም እና ለጸጥታ፣ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ያላቸው ጠቀሜታዎች እንዲሁም በድርቅ እየተጎዱ ባሉ በርካታ የዓለም ክልሎች ላይ ይሆናል ተብሏል።

በዚህ መድረክ ለመሳተፍ ሴኔጋል ዳካር የገቡት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴም በመድረኩ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[ETV]
@ETIOZ
@ETIOZ
688 viewsmetitse(@etioz ), 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 12:50:36
ሰበር ዜና!

133 ሰዎችን ያሳፈረ የቻይና ኢስተርን አየርመንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ!

133 ሰዎችን አሳፍሮ በሀገር ውስጥ በረራ ኩንሚግ ከተባለች ከተማ ወደ ጓንዡ ሲያቀና የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ጓንዢ በተባለ ኮረብታማ አካባቢ መከስከሱን የተለያዩ አለምአቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።እስከአሁን የደረሰው ጉዳት አልታወቀም።

@ETIOZ
@ETIOZ
620 viewsmetitse(@etioz ), 09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 10:11:04 በህንድ በኬረላ ማላፑራም አውራጃ ስታድየም ተደርምሶ ከ200 በላይ ተጎዱ!

ቅዳሜ እለት በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ  የተመልካቾች  መቀመጫው ሲናድ ትልቅ የስታድየም መብራት ወደ ሜዳው ወድቋል።ከሜዳው ተቃራኒው ክፍል የመጡ ደጋፊዎች የተጎዱትን ለመርዳት ወደ ሜዳ ሲሮጡ የሚያሳይ ቪድዮ  የሀገር ውስጡ ጋዜጣ ኤቢፒ አሳይቷል።ድርጊቱ የተከሰተው የህንድ ሰቨንስ እግር ኳስ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ በሚካሄድበት በፖንጎድ ስታዲየም ውስጥ ነው።

@ETIOZ
@ETIOZ
601 viewsmetitse(@etioz ), 07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 09:47:56 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኮንክሪት ምሰሶ ኪራይ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላና የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር አንዋር ሶውሳ ናቸው፡፡በፌርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ የተፈረመው የምሰሶ ኪራይ ስምምነት የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን ለቴሌኮም አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን ገልፀው፤ መሰረተ-ልማቶችን በጋራ መጠቀም መቻሉ ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም የኪራይ አገልግሎቱ በሃገሪቱ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የተቋሙን ገቢ ለማሳደግም ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶውሳ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር አብረው ለመስራት ዕድሉ በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ የተፈረመው የምሰሶ ኪራይ የሁለቱን ተቋማት ሃብት በጋራ ለመጠቀም የሚያስችልና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የምሰሶ ኪራይ ስምምነቱ ዋና አላማ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በተለይም ደግሞ የኮንክሪት ፖሎችን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን በፌርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ስምምነቱ ተግባራዊ የሚደረገው በታላላቅ የሃገሪቱ ከተሞች ላይ በተተከሉ የኮንክሪት ምሰሶዎች ላይ ሲሆን፤ ውሉን የፈረመው ሳፋሪኮም በሚያገኘው አገልግሎት በዓመት 988 ብር ከ70 ሳንቲም ለአንድ ምሰሶ ኪራይ የሚከፍል መሆኑን ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተከላቸው የኮንክሪት ምሰሶዎች ኪራይ ተጨማሪ ገቢ ማግኘቱ በእርጅና ምክንያት የወደቁና የዘመሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ማሻሻልና የመልሶ ግንባታ ስራ ማከናወን የሚያስችለው ይሆናል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ የሁለቱን ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያና ሌሎች የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

@ETIOZ
@ETIOZ
616 viewsmetitse(@etioz ), 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ