Get Mystery Box with random crypto!

Ethio-zena

የቴሌግራም ቻናል አርማ etioz — Ethio-zena E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etioz — Ethio-zena
የሰርጥ አድራሻ: @etioz
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 994
የሰርጥ መግለጫ

💥ይህ ቻናል ስለ ኢትዮጵያና በአለም ያሉትን ሁሉ መረጃዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው
ስለተቀላቀሉ እናመሰግናለን፡፡ https://t.me/ DSSWZ9iewmU2Njc8
ለክሮስ ጥያቄ
@metioz12
#Report ላይ የሆናችሁ በዚህ ሀሳብና አስተያየት ያድርሱን።
@Techexpertt_bot
ለተለያዩ አስተያየቶች እና
መረጃዎችን ለመላክ
@tioze

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-18 17:14:25 ብሩኖ ፈርናንዴዝ ዛሬ ጠዋት የመኪና አደጋ አጋጥሞት ነበር !!!

ፖርቱጋላዊ ኮኮብ ብሩኖ ዛሬ ጠዋት አስደንጋች የሚባል የመኪና ግጭት ገጥሞት የነበረ ሲሆን ነገርግን ግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ታውቋል ። ብሩኖ ከአደጋው በሁዋላም በመልካም ጤንነት በዛሬው እለት የቡድን ጓደኞቹን በመቀላቀል በማንቸስተር ዩናይትድ ልምምዱን ለማድረግ ተዘጋጅቷል ።


@tioze
@tioze
1.5K viewsአቤ የእህቱ 𝓪𝓫𝓮 𝔂𝓮 𝓮𝓱𝓽𝓾, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 17:13:12
1.5K viewsአቤ የእህቱ 𝓪𝓫𝓮 𝔂𝓮 𝓮𝓱𝓽𝓾, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 17:07:45 ዛላታን ኢብራሂምኦቪች ከሰጣቸው አወዛጋቢ እና አስቂኝ አስተያየቶች መሃል አንዳንዶቹ

"ስለኔ በሚፅፉት ነገር እኔ ምንም አይመስለኝም፤ ሚዲያውን የማልፈልግበት ደረጃ ደርሻለሁ። እነሱ ግን እኔን ይፈልጋሉ"

" ተሰጥኦ ሊኖርህ ይችላል ነገርግን ተሰጥኦ ብቻ እስከመጨረሻው እንድትሄድ አያደርግህም"

" ምናልባት እኔ የስዊድን የምንግዜም ምርጡ ተጫዋች ነኝ። እኔ ያደረኩትን ማንም አላደረገም።በስዊድን ያለውን ወርቃማ ኳስ አንድ ተጫዋች ሁለት ግዜ ብቻ ነው ያሳካው። እኔስ ስንት ይመስላቹሃል? እኔ 11 አሳክቻለሁ። ቆይ እኔ እብሪተኛ ነኝ? መልሳችሁ ምንም ይሁን ግን እኔ ምርጡ ነኝ"

ጠያቂ: ስለ ዘረኝነት ምን ታስባለህ

ዘላታን ካየናቸው ነገሮች ሁሉ መጥፎ እሱ ነው። በነጭ እና በጥቁር፣ በሀይማኖቶች ምንም አይነት ልዩነት መፈጠር የለበትም ምክንያቱም ይሄ ከኔ በላይ ሊያደርጋቸው አይችልምና

ጠያቂ: በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ አጥቂ ማነው

ዘላታን "ሉካኩ ጥሩ ነው አግዌሮም እንደዛው"

ጠያቂ: አንተስ

"አንበሶች እራሳቸውን ከሰዎች ጋር አያነፃፅሩም"

"ወደ ፒኤስጂ እንደ ጀግና መጣሁ እንደ ሌጀንድ ወጣሁ"

አዘጋጅ [አቤ]

@tioze
@tioze
1.3K viewsአቤ የእህቱ 𝓪𝓫𝓮 𝔂𝓮 𝓮𝓱𝓽𝓾, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 12:23:19 በሀገር ውስጥ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ!

ከዚህ ቀደም ወደ ዉጭ ሀገር በመላክ ይሰጥ የነበረዉን አገልግሎት በሀገር ዉስጥ ለመስጠት ያስችላል የተባለለት ለወንጀል ምርመራ የሚያግዝ የዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ምርመራ በሀገር ዉስጥ ለመጀመር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።አገልግሎቱ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ስለሚጀምረዉ ቴክኖሎጂው አተገባበር እና ስለሙከራው ውጤታማነት በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለህዝብ መረጃ እንደሚሰጥ የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄላን ኢብራሂም ተናግረዋል።

ለወንጀል ምርመራ ስራ የሚያግዙ አዳዲስ የፎረንሲክ ምርመራ ማሽኖችን ወደ ሀገር አስገብቶ ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን የገለጸዉ ፖሊስ ሌሎች አሰራሮቹንም በቴክኖሎጂ እያዘመነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪም የአቪየሽን ፖሊስ፣ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል ነዉ የተባለው።

[@AddisZeybe]
@etioz
@etioz
1.5K viewsmetitse(@etioz ), 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 09:19:51 የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa

የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
የስራው አይነት :- accounting
የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week

የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
ፆታ - አይጠይቅም
ዕድሜ - 25እስከ 45
መኖሪያ ቤት - በነፃ
ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#10 persons
#Requirements
Passport
photo
Degree documents
Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680


@Etioz
@etioz
1.3K viewsmetitse(@etioz ), edited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 12:56:00 ከፍተኛ ስርቆት በመዲናችን አዲስ አበባ ተፈጽሟል ተባለ!

- ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ተብሏል!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጎሮ ሰፈራ ልዩ ቦታው ፖስታ ቤት መቲ ጋራዥ አካባቢ በቀን 11፣ 2014 ዓ.ም የቻይና ነጋዴዎች ተከራይተው ይሰሩበት የነበረው መጋዘን ላይ ከፍተኛ ስርቆት የተፈጸመው፡፡በዚህ ስርቆት 418 ያህል ቴሌቪዥኖች የተሰረቁ ሲሆን ቁጥራቸው የማይታወቅ ላፕቶፕ ኮምፒተሮች የመኪና ባትሪዎች እንደዚሁም 63ሺህ ጥሬ ገንዘብ አብሮ መሰረቁን ነው ኢትዮ ኤፍ ኤም አገኘሁት ያለው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

እነዚህ ነጋዴዎች መጋዘኑን የተከራዩት ከአንድ ወር በፊት የነበረ ሲሆን ከቻይና በርካታ እቃዎችን እያስመጡ ለነጋዴዎች ያከፋፍሉበታል የነበረ መጋዘን ነው፡፡አቶ መኮንን ድርጊቱን ያቀነባበሩት የጥበቃ ሰራተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ያላቸውን ግምት ያስቀመጡ ሲሆን አሁን ላይ እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ብለዋል፡፡

ቃላቸውን ለፖሊስ የሰጡት የጥበቃ ሰራተኞች በበኩላቸው ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ያሉት አቶ መኮነን ፣ከድርጊቱ መፈጸም በላይ የጸጥታ አካላት የሰጡት ምላሽ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡

የቤት አከራዩ አቶ መኮንን ስርቆቱ በተፈጸመበት እለት መብራት ጠፍቶ እንደነበረ እና የአይሱዚ መኪና መጋዘን ውስጥ ገብቶ መጫኑን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ጥቆማቸውን እንዳደረሱዋቸው ተናግረዋል፡፡

[Ethio FM]
@etioz
@etioz
1.2K viewsmetitse(@etioz ), 09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 12:15:32
ተዋናይ ዊል ስሚዝ ኦስካርስ በተሰኘው የፊልም ጥበብ የሽልማት መድረክ የሚስቱን ስም አንስቶ ያብጠለጠለውን ታዋቂውን ኮሜዲያን ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ።

ክሪስ ሮክ፤ የዊል ስሚዝ ሚስት ጄዳ ፒንኬት ስሚዝን የፀጉር ቁርጥ በቀልድ ወረፍ ካደረገ በኋላ ነው ይህ የተከሰተው።ዊል ስሚዝ ከመቀመጫው በመነሳት ወደ መድረኩ አቅንቶ ክሪስ ሮክን በጥፊ አጋጭቶ ሲመለስ ብዙዎች ጉዳዩ ቀልድ ነው ብለው አስበው ነበር።ነገር ግን ወደ ወንበሩ ከተመለሰ በኋላ "የሚስቴን ስም በ. . . አፍህ አታንሳ" ብሎ ሲጮህ ነው ብዙዎች ተዋናዩ ማምረሩን የተረዱት።

ስሚዝ ከዚህ ብዙዎችን ካስበረገገ ድርጊት በኋላ የኦስካር ሽልማቱን ሲያነሳ ለድርጊቴ ይቅርታ በሉኝ ብሏል።"አካዳሚውን [ኦስካር ሸላሚው ኮሚቴ] እንዲሁም ለሽልማት የታጩ የተውኔት አጋሮቼን ይቅርታ መጠየቅ እሻለሁ" ሲል ተማፅኗል።

ዊል ስሚዝ፤ ኪንግ ሪቻርድ በተሰኘው ፊልም ላይ የቴኒስ ከዋክብቱን ቬነስና ሰሪና ዊሊያምስ አባት ሆኖ በመተወኑ ነው በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስም የከበደውን የኦስካር ሽልማት ያገኘው።"ጥበብ የሕይወት ቅጂ ናት።ልክ እንደ ተወንኩት ሪቻርል ዊሊያምስ የእብደት ሥራ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ፍቅር የእብድ ሥራ እንድትሠሩ ያደርጋችኋል።"

ባለቤቱ ፒንኬት ስሚዝ ከዚህ በፊት የፀጉር መነቀል የሚያስከትል አለፔሲያ የተሰኘ በሽታ እንዳለባት ተናግራ ነበር።የዊል ስሚዝ ጥፊ ሰላባ የሆነው ክሪስ ሮክ በሁኔታው እጅግ ተደናግጦ "በቴሌቪዥን ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ክስተት ታድመናል" ሲል ተደምጧል።

Via BBC
@etioz
@etioz
1.0K viewsmetitse(@etioz ), 09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 11:07:52 የጉጂ አባ ገዳ መኖሪያ ቤታቸው ላይ 'ኦነግ ሸኔ' ጥቃት መፈጸሙን ተናገሩ!

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ እና የጉጂ አባ ገዳ የሆኑት ጂሎ ማንዶ ታጣቂዎች በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።አባ ገዳ ጂሎ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ዕለት መጋቢት 14/2014 ዓ.ም. ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቤታቸው ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራውን እና መንግሥት ሸኔ የሚለውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ግን ታጣቂዎቻቸው 'የተባለውን ጥቃት አልፈጸሙም' ሲሉ አስተባብለዋል።አባ ገዳው ጥቃት በተፈጸመበት ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ባለመኖራቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውንና በንብረት ላይ ከደረሰው ውጪ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል።

"በቁጥር ስንት ሆነው እንደመጡ ባላውቅም በአራት ሞተር ሳይክሎች መጥተው ቤቱ ላይ ተኩስ ከፈቱ። በርካታ ጥይት ተኩሰው ቤት ሰባብረው፣ ቤት ውስጥ የነበረ አንድ ኩንታል ቡና በትነው ሄዱ እንጂ ሰው እና ከብት ምንም አልሆነም" በማለት የነበረውን ሁኔታ አባ ገዳ ጂሎ ያስረዳሉ።አባ ገዳው ታጣዊዎች ትጥቅ ፈትተው የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ ማስተላለፋቸው የጥቃቱ ዒላማ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ያምናሉ።"እነርሱ መጀመሪያም ቂም ይዘውብኝ ነበር። እየደወሉ፤ 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር በሰላም ግቡ እያልክ የምትቀሰቅሰው አንተ ነህ' ሲሉኝ ቆይተዋል" በማለት አባ ገዳው ይናገራሉ።

"እየደወሉ '600 የሚሆን ሠራዊት አስገብተህ (ትጥቅ አስፈትተህ) መሳሪያቸውን ወርሰሃል፤ ያን መሳሪያ እስክታመጣ በሕይወትህ ፍረድ' ይሉኛል" ሲሉ ጂሎ ማንዶ ከታጣቂዎቹ ይደርስባቸው ስለነበረው ዛቻ ያስረዳሉ።እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ቃል አቀባይ የሆነው ኦዳ ተርቢ፤ የኦሮሞ ነጻነት ጦር አባ ገዳዎችን እና የገዳ ሥርዓትን እንደሚያከብር ገልጸው፤ "በከረዩ አባ ገዳዎች ላይ የተፈጸመውን እና የመንግሥት (የዐቢይ) ጦር ለሥርዓቱ ያለውን ንቀት ከግምት በማስገባት ይህ የተፈጸመው በእነርሱ (በመንግሥት ጦር) ሊሆን ይችላል" ብለዋል።ከዚህ ቀደም የጉጂ እና የቦረና አባ ገዳዎች 'ኦነግ ሸኔ' የኦሮሞ ጠላት ነው በማለት ማወጃቸው ይታወሳል።ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲፈቱም ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via BBC
@etioz
@etioz
1.0K viewsmetitse(@etioz ), 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 09:15:17
ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እስማማለሁ አለ!

ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ላለፉት 16 ወራት ግጭት ውስጥ የቆየው ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እንደሚስማማ ገለጸ።ህወሓት ይህን ያለው ትናንት ሐሙስ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርስ ለማስቻል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ካስታወቀ በኋላ ነው።

የፌደራሉ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የተከሰተውን ሰብአዊ ቀውስ "በእጅጉ ሊያሻሽል" ስለሚችል እና "በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል" ተስፋ በማድረግ መሆኑን ገልጿል።መንግሥት ይህ ውሳኔ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ "በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ" ጠይቋል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ ላይ በበቂ መጠን እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ጥሪውን እንደሚቀበል ገልጿል።በትግራይ ካለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታው የሚደርስ ከሆነ "የትግራይ መንግሥት ግጭት ለማቆም ቁርጠኛ ነው" ብሏል።

[BBC]
@etioz
@etioz
899 viewsmetitse(@etioz ), 06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 13:35:27
በትላንትናው እለት ከተከሰከሰው የቦይንግ አውሮፕላን እስካሁን በህይወት የተረፉ ሰዎች አልተገኙም ተባለ!

በትላንትናው እለት 132 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው የቦይንግ አውሮፕላን ከተከሰከሰ በኋላ እስካሁን በተደረገ የነፍስ አድን ስራ በህይወት የተገኘ ሰው አለመኖሩ ተዘገበ።የእንግሊዙ ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ የቻይናን መንግስታዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ በተራራማ ስፍራ የደረሰው አደጋው የነፍስ አድን ስራውን አስቸጋሪ ቢያደርገውም እስካሁን በህይወት ያለ ሰው ማግኘት አልተቻለም ብሏል።

ቦይንግ 737-800 የተሰኘው አውሮፕላን ከ30 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ መከስከሱን የዘገበው ጋዜጣው፤ በቻይና ከረጅም ጊዜ በኋላ የተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ መሆኑን ገልጿል።የነፍስ አድን ባለሙያዎች ከሰዎች ህይወት ፍለጋ በተጨማሪ የአውሮፕላን መረጃዎችን የሚመዘግበው ‘ብላክ ቦክስ’ን እየፈለጉ ሲሆን የመረጃው መገኘት የአደጋውን መንሳኤ ለማጣራት ባለሙያዎችን እንደሚያግዝ ተስፋ ተደርጎበታል።

በአሁኑ ወቅት በቻይና በርካታ በረራዎች እየተሰረዙ ነው ያለው የኢንዲፔንደንት ዘገባ፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን ባለቤት ቻይና ኢስተርን አየር መንገድ የቦይንግን ተመሳሳይ አውሮፕላኖች በሙሉ ከበረራ ውጪ ማድረጉን ገልጿል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ መስጠታቸውም ተሰምቷል።

Addis Zeybe
@etioz
@etioz
874 viewsmetitse(@etioz ), 10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ