Get Mystery Box with random crypto!

'ዓለም አቀፍ ተቋማት ሕወሓት እየፈጸመ ያለውን የሽብር ድርጊት ሊያጋልጡ ይገባል' -አምባሳደር ጥሩ | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

"ዓለም አቀፍ ተቋማት ሕወሓት እየፈጸመ ያለውን የሽብር ድርጊት ሊያጋልጡ ይገባል"
-አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የቀድሞ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር
**************
(ኢ ፕ ድ)
ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በአሸባሪው ሕወሓት እየተፈጸሙ ያሉ ከፍተኛ የመብት ጥሰት እና ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን በተመለከተ ተገቢ ምርመራ አካሂደው ሊያጋልጡት እንደሚገባ የቀድሞ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ገለጹ።
አምባሳደር ጥሩነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪ ቡድኑ ሕፃናትን በጦርነት በመማገድ፣ ለትግራይ ሕዝብም የቀረበን ሰብአዊ ድጋፍ ከጉሮሮ በመንጠቅ እየፈጸማቸው ያሉ ወንጀሎች ጭካኔ የተሞላባቸውና የሚወገዙ ናቸው።
ሕወሓት አሁን እያደረጋቸው የሚገኙት ወንጀሎች ፍላጎቱን ለመረዳት የሚያስቸግር ነው። ለትግራይ ሕዝብ ነፃነትና መብት እየተዋጋሁ ነው ይበል እንጂ የያዘው መንገድ የትግራይን ሕዝብ ወደ ከፋ ችግር የሚያስገባ ነው።
እንደርሳቸው ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የትግራይ ሕዝብን ከሕወሓት የሽብር ቡድን ለማላቀቅ መሥራት አለበት። ፌዴራል መንግሥቱ በሕዝቦች ላይ የሚፈጸሙ ማናቸውም....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=80566
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio