Get Mystery Box with random crypto!

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ከ270 ሚሊየን ብር በላይ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎችን ለመልሶ | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ከ270 ሚሊየን ብር በላይ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎችን ለመልሶ ማቋቋም አውሏል
ዩኒቨርስቲው ከ5 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፣
********************
(ኢ ፕ ድ)
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ለማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ከ270 ሚሊየን ብር በላይ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ለመልሶ ማቋቋም ማዋሉን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን ገለጹ።
ዶክተር አስራት ዪኒቨርስቲው በተከታታይና በመደበኛው መርሃግብር በተለያየ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት እንደገለጹት፣ ዩኒቨርስቲው ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማድረግ ለማህበረሰቡ ከ15 በላይ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እየሰራ ነው። ዩኒቨርስቲው በጦርነት ለተጐዱ ወገኖች መልሶ ለማቋቋም 277 ሚሊየን ብር አውጥቷል ብሏል።
ህወሓት በከፈተው ጦርነትና ባለፉት አራት አስርት አመታት በወልቃይት፣ ጠለምት፣ በጭናና በሌሎች አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሰው ሰብአዊ፣ ቁሳዊ፣ ባህላዊ፣ የቋንቋና በሌሎች እሴቶች ላይ ያደረሰውን ውድመትና ግፍ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስገንዘብ የጥናት ቡድን በማቋቋም ላለፉት አንድ አመት ተኩል ጥናት አድርጓል።
በቀጣይ ሳምንት 387 ገጾች ያሉት አማርኛ መጽሃፍ ይመረቃል። በቀጣይም ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሙ አማዞን ላይ ይቀመጣል ብለዋል።
ዩኒቨርስቲው በ319 መርሃግብሮች እያስተማረ ይገኛል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር 56 የሚሆኑ የምስራቅ አፍሪካ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፣ ዛሬም የሚመረቁ አሉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር ተከተል ዮሃንስ ጐንደር ዩኒቨርስቲ ካሉት የምርምር ዩኒቨርስቲ አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያከናወናቸው ያሉ የምርምር ስራዎች በርካታ ናቸው። ተመራቂ ተማሪዎች ኢትዮጵያ ከገጠማት ፈተና እንድትወጣ ምክንያታዊ በመሆን የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዩኒቨርስቲው ሶስት ሺ 927 ወንዶችና አንድ ሺ 600 ሴቶችን በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ፣ በሶስተኛ ዲግሪ አስመርቋል።
በምረቃ ፕሮገራሙ ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር ተከተል ዩሃንስና የዩኒቨርስቲው የቦርድ አመራር፣የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በሞገስ ተስፋ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio