Get Mystery Box with random crypto!

' እዚሁ ሰላሌ ውስጥ 52 ቀበሌዎች 100 ሺህ እና 50 ሺህ ብር ለኦነግ ሸኔ ግብር ከፍለዋል።' | ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹

" እዚሁ ሰላሌ ውስጥ 52 ቀበሌዎች 100 ሺህ እና 50 ሺህ ብር ለኦነግ ሸኔ ግብር ከፍለዋል።" - አቶ ውብሸት ታዬ

ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ውስጥ ያያ ጉለሌ የሚባል አካባቢ ከ150 አመት በላይ የኖሩ 10 ሺህ የሚሆኑ አማሮች ለቅቃችሁ ውጡ ተብለው ነቅለው ወጥተዋል። የሚሄዱበት ሀገር ስለሌላቸው ወደ ልመና ጭምር ገብተዋል። የሚጠብቃቸው አካል ስለሌለ ነው።

በሰላሌ አካባቢ አማሮች ነቅለው እንዲወጡ ሲደረግ፣ ኦሮምዎች ደግሞ ግብር እንዲከፍሉ ሆኗል። ሰላሌ ውስጥ ሀብት ያላቸው ሰዎች ለኦነግ ሸኔ ግብር ከፍለዋል። 100 ሺህ እና 50 ሺህ ብር ግብር ከፍለዋል፣ ኦነግ ሸኔም ማህተም ያለበት ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል። ኦነግ ሸኔ ሰላሌ ውስጥ ከ52 ቀበሌ በላይ ግብር አስከፍሏል።

ወለጋ ብቻ አይደለም አማራ የሚገደለው። እዚሁ ሰሜን ሸዋ ጭምር እንጂ። ይሄ ሁሉ ሲሆን መንግስት እርምጃ አልወሰደም። አንዳንዴ እየተጠቃቀሱ የሚሰሩ ይመስለኛል።

(አቶ ውብሸት ታዬ - ለBlue24 የተናገረው)