Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን ሸዋ አጣዬ አካባቢ በአማራ ልዩ ኃይል ላይ የደረሰዉን ገዳት አስመልክቶ ከአማራ ህዝባዊ ኃይ | ETHIO ZENA (ኢትዮ ዜና)🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በሰሜን ሸዋ አጣዬ አካባቢ በአማራ ልዩ ኃይል ላይ የደረሰዉን ገዳት አስመልክቶ ከአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ህዝብ መከታ መሆኑን በተደጋጋሚ በተግባር ያረጋገጠዉ የአማራ ልዩ ኃይል ባልተሟላ ሎጅስቲክስ እና አመራር ውስጥ ሆኖ የአማራን ህዝብ ከጥ*ፋት ለመታደግ መ*ራር መስዋዕትነት በመክፈል ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ሐምሌ 03 እና 04 ቀን 2014 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ጥ*ቃት በመከላከል ላይ እያሉ በተቀነባበረ ሴ*ራ ምክንያት ቁጥራቸው በርከት ያለ የልዩ ኃይል አባላት ተሰ*ውተዋል። በርካቶችም ከባድ እና ቀላል ጉ*ዳት ደርሶባቸዋል። የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በክልሉ ውስጥ በተደራጀ ታ*ጣቂ አማካኝነት በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ በደረሰው ጉዳት መሪር ሀዘን የተሰማው መሆኑን ይገልፃል።

መላው የልዩ ኃይላችን አመራር እና አባላት ውድ ህይወታችሁን የምትሰጡለት የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነበትን የህልዉና አ*ደጋ ለመቀልበስ የምታደርጉትን ተጋድሎ እያደነቅን የአማራ ብልፅግና የሚባለውን ድርጅት ተጠቅመው ሊያ*ጠፋፉን የሚፈልጉ ዋነኞቹ ጠላ*ቶቻችን እናንተን ከፋኖ ወንድሞቻችሁ ጋር በማጋጨት የአማራዉን ኃይል በመ*በተን ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉትን ጥረት እንድትረዱ እና ከቆማችሁለት ዓላማ ውጭ ስምሪት የሚሰጣችሁን የፖለቲካ አመራር በቃ*ህ እንድትሉት፤ ባልተሟላ የመረጃ፣ የአመራር እና የሎጅስቲክስ አቅርቦት ለአደጋ እያጋለጣችሁ ያለዉን የፖለቲካ አመራር ልዩ ኃይሉን ለከፋ አደ*ጋ ከሚያጋልጥ ስዉር ሴ*ራው እንዲታቀብ ወታደራዊ አካሄዱ በሚፈቅደው አሰራር መሰረት በየአደረጃጀታችሁ እንድትታገሉት ጥሪ እናስተላልፋለን።

በአካባቢው ያላችሁ የአማራ ፋኖ አባላት ልዩ ኃይሉ ላይ ከሆነውም የከፋ ጉ*ዳት እንዳይደርስ ላደረጋችሁት ተጋድሎ ከፍተኛ አድናቆት ያለን መሆኑን እየገለፅን ሁሉም የፋኖ አመራር እና አባላት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ጥበብ እና ብስለት የተሞላበትን አካሄድ በመከተል ከልዩ ኃይላችን ጋር ስምሪት ጋር ተያይዞ ጠላ*ቶቻችን የሸረቡልንን የመጠ*ፋፋት ሴ*ራ እንድና*ከሽፍ ጥሪ እናቀርባለን።

በመጨረሻም መስዋዕትነት ለከፈሉ የልዩ ኃይላችን ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ)
ሐምሌ 05 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕርዳር-ኢትዮጵያ