በርቀት ፕሮግራም በሁለተኛ ዲግሪ ማስተማር ሆነ መማር ተከለከለ
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በርቀት መርሐ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ማስተማር እንደማይቻል አሳውቋል፡፡
በርቀት መርሐ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ማስተማር የማይቻል መሆኑን በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር፣ ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ም/ዋ/ዳይሬክተር ቸሩጌታ ገነነ ገልጸዋል።
ተማሪዎችን ሲመዘግቡም ሆነ ሲያስተምሩ በሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ጠበቅ ያለ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ኃላፊው ተናግረዋል።
በተጨማሪም በዲፕሎማ ደረጃ በግብርና እና በመምህርነት የተማሩ ግለሰቦች ወደ ሌላ የትምህርት ስልጠና ዓይነት ቀጥለው መማር እንደማይችሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አስታውሰዋል።
share share
@EthioUniversty1 @EthioUniversty1