Get Mystery Box with random crypto!

2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አሁንም ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ 'ሴ | Ethio University

2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አሁንም ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ "ሴቭ ዘ ችልድረን" የተባለው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ተቋም ገለጸ፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ባለመጀመራቸው ምክንያት 2.3 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ተማሪዎች አሁንም ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

የመማሪያ ክፍሎች እንደገና ተከፍተው ተማሪዎችን ያስተናግዱ ዘንድ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል ተቋሙ።

በመላ ሀገሪቱ ከ 3.5 ሚሊዮን በላይ ህጻናት (ከ16 ህጻናት አንድ) ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ድርጅቱ አመልክቷል።

ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑት ህጻናቱ፤ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለጾታዊ ጥቃት እና ላልተፈለገ ጋብቻ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል።

በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውድመት አስተናግደዋል።

በትግራይ ክልል 85 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የተጎዱ ሲሆኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ መሆናቸውን የድርጅቱ መረጃ ያሳያል።

22, ሺህ 500 መምህራን ከሁለት ዓመት በላይ ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንደቆዩም ድርጅቱ አስታውሷል።

ምንጭ፦ Save the Children