Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ተቋማትን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ሁሉም አካላት ድጋፍ | Ethio University

በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ተቋማትን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ጥሪ አቀረቡ።

በትግራይ ክልል ሥራ ያቆሙ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በዚህም መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

ተቋማቱን ሥራ ለማስጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ በተጨማሪ ለመማር ማስተማር አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማሟላት በጀት ሊመደብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮቹ ጥሪ አቅርበዋል።

share share

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1