Get Mystery Box with random crypto!

#DebreMarkosUniversity ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም ነባር እና አዲስ | 🇪🇹ኢትዮ University

#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም ነባር እና አዲስ አንደኛ ዓመት መደበኛ ቅድመ-ምረቃ እና የሬሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም መሠረት የምዝገባ ጊዜዉ እንደሚከተለዉ ተገልጿል፦

- የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ ነባር ተማሪዎች ከመጋቢት 16-17/2016 ዓ.ም

- በ2016 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ፍሬሽማን እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ከመጋቢት 16-17/2016 ዓ.ም

ማሳሰቢያ:
* ለነባር 1ኛ ዓመት ተማሪዎች እና የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደዉ #በየነበራችሁበት ካምፓስ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

* በሀገር አቀፍ የማለፊያ ዉጤት ያመጣቹህ አዲስ የአንደኛ ዓመት(ፍሬሽማን) ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደዉ #በዋናዉ ግቢ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

* የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ የሪሜድያል ተማሪዎች በስማችሁ ቅደም ተከተል መሰረት ስማችሁ ከA-G የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እና ስማችሁ ከA-H የሚጀምር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ #የምትመዘገቡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በዋናዉ ካምፓስ የምትመዘገቡ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

* አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው እንዲሁም ስምንት 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

በተለያየ ምክንያት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ 1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1