Get Mystery Box with random crypto!

ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመታ አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ! የትምህርት ማስረጃ ማረጋ | 🇪🇹ኢትዮ University

ለትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመታ አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ!

የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመታ አገልግሎት ፈላጊዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ባላችሁበት ሆናችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ https://neta.gov.et ካመለከታችሁ በኋላ፡-

1. መስፈርቱን የምታሟሉ፡-

1.1. በSMS መልእክት የምትመጡበት ቀነ ቀጠሮ ይደርሳችኋል ነገር ግን ከቀነ ቀጠሮው በፊት ወደ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ብትመጡ አገልግሎት መስጠት የማንችል በመሆኑ እንዳትጉላሉ እናሳስባለን፤
1.2. ቀነ ቀጠሮ መቀየር ቢያስፈልጋችሁ በSMS/በኢ-ሚይል/በስ.ቁ(+251) 0111 26 14 52 /(+251)0111 26 16 23 በመደወል አዲስ ቀነ ቀጠሮ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

2. መስፈርቱን ለማታሟሉ፡-

2.1 . ያላሟላችሁት ማስረጃ ወይም ምክንያት በSMS መልእክት የሚደርሳችሁ በመሆኑ ሳታሟሉ መምጣት የለባችሁም፤

2.2 . ያላሟላችሁት ማስረጃ ካላችሁ በድጋሚ እንድታሟሉ እና ማሟላታችሁ ተረጋግጦ በSMS መልእክት ሲደርሳችሁ ብቻ እንድትመጡና እንዳትጉላሉ እናሳስባለን፡፡
3. በሀገር ውስጥ ተምራችሁ የትምህርት ማስረጃችሁን ለማረጋገጥም ሆነ በውጭ ሀገር ተምራችሁ የአቻ ግመታ ለማሰራት በኦንላይን ካመለከታችሁ በአካል ብትመጡ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝