Get Mystery Box with random crypto!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሀኪምና መምህር ዶ/ር ሙሐመድ ከድር የዕውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው ****** | 🇪🇹ኢትዮ University

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሀኪምና መምህር ዶ/ር ሙሐመድ ከድር የዕውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው
*********
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሀኪምና መምህር ዶ/ር ሙሐመድ ከድር ለህክምና ሙያና ትምህርት እድገት ላደረጉት አስተዋፅኦ ከኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበር የዕውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው።

የኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበር 60ኛ ዓመታዊ ኮንፈረንሱን ከየካቲት29_መጋቢት01/2016ዓ.ም በአ.አ ያካሔደ ሲሆን፣ዶ/ር ሙሐመድ ከድር በህክምናው ዘርፍና በመማር ማስተማር ሒደቱ በርካታ ምሁራንን በማፍራት ለሀገራቸው ያደረጉትን አስተዋፅኦ በመጥቀስ የዕውቅና ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

የጎንደር ዩኒበርሲቲ ህክምና ት/ቤት ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጌታ አያሌው በበኩላቸው የህክምና ማህበሩ ስለሰጠው እውቅና አመስግነው፣ዶ/ር ሙሐመድ ከድር የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳይንስ ኮሌጅ ህክምና ማስተማር ከጀመረበት ጊዜ ጀምረው ከተማሪነት እስከ አንጋፋ መምህርነት እያገለገሉ እንደሚገኙ ገልፀዋል፤ ለወደፊቱም ከፍተኛ አስቸዋፅኦ ለሚያደርጉ አንጋፋ መምህራን ለስራቸው ክብር ተመሳሳይ ዕውቅና ይሰጣል ብለዋል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝