Get Mystery Box with random crypto!

በዓለም ላይ ሌላ፣ ይኽ ሁሉ የተቀናጀ መከራ ወርዶበት ጸንቶ የቆመ አገር... በየጊዜው ይኽን ሁሉ | ጠይም | Teyim 🌹

በዓለም ላይ ሌላ፣ ይኽ ሁሉ የተቀናጀ መከራ ወርዶበት ጸንቶ የቆመ አገር... በየጊዜው ይኽን ሁሉ መከራ እና ሽብር ተሸክሞ ቆሞ የሚሄድ ሕዝብ መኖሩን እንጃ። የመጣበትን መከራ ተቋቁሞ እያሸነፈ፣ ጸንቶ የቆመ አንድ አገር፣ አንድ ሕዝብ ግን አለ። ቅኝ ግዛትን አልቀበልም ውረድ ከጫንቃዬ ብሎ የቀለም አስተሳሰብን ቀይሮ ዓለምን ያስተማረ ግን አንድ አገር፣ አንድ ሕዝብ አለ።

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊ

ይኽንንም የምናልፈው ነን! Yes, we're gonna make it past!

እስከዚያ እርስ በርሳችን እንጠባበቅ። ስሜታችንን አሸንፈን አገራችንን እንድታሸንፍ እንርዳት። የሀሰት ወሬዎችን አናሰራጭ። በሀሰት ወሬዎች አንሸበር። ማኅበራዊ ሚዲያን በአግባቡ እንጠቀምበት። ዝም ማለት አያዋጣንም። ዝም ማለት ባለብንም መናገር አያዋጣንም። ሚዛኑን እንጠብቅ።