Get Mystery Box with random crypto!

Please read &share! በሚሆነው ነገር አትሸበሩ! ምንም አዲስ ነገር የለም። ኅብረት | ጠይም | Teyim 🌹

Please read &share!

በሚሆነው ነገር አትሸበሩ! ምንም አዲስ ነገር የለም። ኅብረት እንጂ ሽብር መፍትሄ አይሆንም። የየአገሩ መንግስት ይኽንን ወከባ የሚፈጥረው ለማሸበርና መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር ነው። ይኽንን ተገንዝበን በያለንበት እርስበርስ እንጠባበቅ። በነውር ነገር ውስጥ ስማችሁ እንዳይጠራ አደራ። በእናንተ እንዲደርስ የማትፈልጉትን በሌላው ሰው ላይ አታድርጉ። ጎረቤቶቻችሁን፣ ዘመዶቻችሁን ጠብቁ። ግርግር ለሌባ ያመቻልና ዙሪያችሁን በንቃት ጠብቁ። የሚያጠራጥር ነገር ስታዩ ለህግ አሳውቁ እንጂ እናንተ ለፍርድ አትቀመጡ። የውጭ አገር ሰዎች ሕዝባቸውን ወደ አገራቸው እንወስዳለን ቢሉ፣ እንዳቂሚቲ አገር ስላላቸው ነው። ያለችንን አንዲት አገር መጠበቅ እና ኅብረት መፍጠር ደግሞ የእኛ ፈንታ ነው። የሰው አገር ሰው የሰው ነው። ሲፈልግ ይሄዳል ሲፈልግ ይመጣል። እንዲሁ የሰው አገርም የሰው ነው። ሲፈልጉ ያስገቡናል፣ ሲፈልጉ ያስወጡናል። ስለዚህ የአገሬ ልጆች፣ በፍጹም አትሸበሩ። አይዞን! ሁላችንም አብረን ነን!! ኹሉም ታሪክ የሚሆን ነው!!

~ Yohanes