Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ዓዳም- Tena Adam

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotena1 — ጤና ዓዳም- Tena Adam
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotena1 — ጤና ዓዳም- Tena Adam
የሰርጥ አድራሻ: @ethiotena1
ምድቦች: ውበት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.69K
የሰርጥ መግለጫ

👉 ይህ የTelegram channel ስለ ጤናዎ በጥቂቱ ግንዛቤ ያስጨብጣል።
👉 ማንኛውንም ጤና ነክ ጉዳይ እናማክራለን
📝 (ጤና ዓዳም- Tena Adam 📁📂
ጥያቄ አስተያየት 👉👉 @Amydan

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-03 01:51:00 የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) እና የባሕል ሕክምናው መዘዙ

(ከታች የቀረቡት ሁለት ታሪኮች በእውነታኛ ገጠመኞች የተመሠረቱ ሲሆን 'አቶ አበበ' እና 'አቶ ከበደ' የሚሉት ስሞች እውነተኛ የታካሚዎች ስም አለመሆኑን እንገልጻለን)

አቶ አበበ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ የ5 ልጆች አባት ናቸው፡፡ የሚኖሩት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ላለፉት 2 ዓመታት በኪንታሮት (Hemorrhoid) በሽታ ታመው ከነገ ዛሬ ይሻለኛል ሲሉ ቢቆዩም ሕመሙ ግን እየተባባሰባቸው መምጣት ጀመረ፡፡ ሕመሙ ሲብስባቸው ጎረቤታቸውን በማማከር ወደ ባሕል መድኃኒት ቤት ያመራሉ፡፡

ባለመድሃኒቱም የሚቀባ የባሕል መድሃኒት ይሰጣቸውና እንደሚያድናቸው አረጋግጦላቸው ይሸኛቸዋል፡፡ አቶ አበበ የተሰጣቸውን መድኃኒት እንደተባሉት መቀባት ይጀምራሉ፡፡ በሦሥተኛው ቀን ኪንታሮቱ ይፈነዳና መግል ማውጣት ጀመረ፡፡ በአራተኛው ቀን አቶ አበበ ራሳቸውን ይስታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጆቻቸው ተደናግጠው ወደ ሆስፒታል ያመጧቸዋል፡፡

ሆስፒታል ሲደርሱ የአቶ አበበ የልብ ምት በጣም ይፈጥናል፡፡ የደም ግፊታቸው በጣም ወርዷል፡፡ በድንገተኛ ክፍል ያሉ የጤና ባለሙያዎች በመረባረብ በመርፌ መድሐኒቶችን ፣ ግልኮስ፣ ፈሳሻ ንጥረ ነገርና የተለያዩ ምርመራዎችን ቢያደርጉላቸውም ቁስሉ ኢንፌክሽን ፈጥሮ በደም ውስጥ ስለተሰራጨ የደም ግፊታቸው ሊስተካከል አልቻለም፡፡ ከዚህም የተነሳ አቶ አበበ ጽኑ ሕሙማን ክፍል በአስቸኳይ እንዲገቡ ተደርጎ የተለያዩ የሕክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

ሌላኛው ታካሚ አቶ ከበደ ናቸው፡፡ እድሜያቸው 58 ሲሆን የባሕርዳር ኗሪ ናቸው፡፡ ከ5 ዓመት በፊት ጀምሮ የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) ጀምሯቸው በየጊዜው እየተባባሰቸው ይሄዳል፡፡

ከዚህም የተነሳ አንድ ታዋቂ የባሕል ሕክምና አዋቂ ጋር ይሄዳሉ፡፡ ባለመድኃኒቱም ከመረመራቸው በኋላ በመርፌ የሚወጋ መድኃኒት አዘዘላቸውና ያበጠው ኪንታሮት ላይ መድኃኒቱን በመርፌ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም እንደሚድን ነግሯቸው ይሰነባበታሉ፡፡

ወደ ቤት ከሄዱ በኋላ ኪንታሮቱ እብጠቱ እየጨመረ ይሄድና በሳምንቱ ይፈነዳል፡፡ ከዛም ተመልሰው ሲሄዱ ባለመድኃኒቱ እየቆየ እንደሚድንላቸው ነግሮ ይሸኛቸዋል፡፡ ይሁንና ቁስሉ ከመዳን ይልቅ እየሰፋ፣ መግል እያመንጨና እየተባባሰ ይሄዳል፡፡ የዚህን ጊዜ ቁስሉን በጨውና በውሃ እያጠቡ በቤት ይቆያሉ፡፡ ቁስሉ እየሰፋ በመሄዱ ከጥቂት ወራት በኋላ አቶ ከበደ ሰገራ መቆጣጠር ያቅታቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ዳይፐር መጠቀም ይጀምራሉ፡፡

ከዚህም በኋላ ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ የሕመሙ ደረጃ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ አቶ ከበደ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተልከው በተደረገላቸው ምርመራ የፊንጢጣ መቆጣጠሪያ ጡንቻዎቹ ሙሉ በሙሉ በመጎዳታቸው በሆዳቸው በኩል የሰገራ መውጫ (Permanent colostomy) እንዲሠራላቸው ተወሰነ፡፡

ከነዚህና መሰል ብዙ ታሪኮች እንደምንረዳው ለኪንታሮት ተብለው ከትልልቅ ከተማ እስከ ገጠር የሚሰራጩ የባሕል መድኃኒቶች በኅብረተሰቡ ላይ ምን ያህል ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነ ነው፡፡

የባሕል ሕክምና በአግባቡ ትኩረት ተሰጥቶት ከዘመናዊ ሕክምና ጋር ቢዛመድ ለማኅበረሰባችን አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል ቢታመንም የዕለት ተዕለት ገጠመኞቻች ይህ ዓይነቱ የኪንታሮት የባሕል ሕክምና ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለመናገር ያስደፍረናል፡፡

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids) ምንድነው?

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids)፦በፊንጢጣ ላይ የሚገኙ ደም መላሽ የደም ስሮች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም ከ45 - 65 ዓመት ባሉት ሰዎች ላይ በብዛት ይከሰታል

የኪንታሮት በሽታ በዋናነት በሁለት (types) ይከፈላል
፩. ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoids)፦ በውጨኛው የፊንጢጣ ክፍል ላይ የከሰት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመምም (Pain) ያስከትላል፡፡

፪. ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoids)፦ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመም አይኖረውም
ይህ የኪንታሮት ዓይነት 4 ደረጃዎች (grades) አሉት።

አንደኛ ደረጃ (Grade-1) ይህ ደረጃ በፊንጢጣ ግድግዳ ላይ እብጠት ሲኖር ነው፡፡ እብጠቱ በዋናነት በስተ ግራ፣ በፊት ለፊትና በስተኋለኛው የፊንጢጣ ግድግዳ ላይ ይከሰታል፡፡

ሁለተኛ ደረጃ (Grade-2) በዚህ ጊዜ የእብጠቱ መጠን ጨምሮ ለሽንት ሲቀመጡ በሚኖር ማማጥ እባጩ ወደውጪ ሲወጣና በራሱ ጊዜ ወደውስጥ ሲመለስ ነው፡፡

ሦሥተኛ ደረጃ (Grade-3) - በዚህ ጊዜ እባጩ ለሽንት ሲቀመጡ ወደውጪ ይወጣና በራሱ ስለማይመለስ የግድ በእጅ መመለስ ሲፈልግ ነው፡፡

አራተኛ ደረጃ (Grade-4) በዚህ ጊዜ እባጩ ላይመለስ በፊንጢጣ ይወጣና ይቀራል፡፡

አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors)

የሆድ ድርቀት -አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸው ምግቦችን ማዘውተር (ፓስታ፣ ማኮሮኒ፣ ነጭ ዳቦ...) እና በቂ ውሃ አለመጠጣት
እርግዝና
የትልቁ አንጀት ካንሰር
ሽንት ቤት ተቀምጦ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
ረጅም ጊዜ የቆዬ ተቅማጥ (chronic diarrhea)
ዕድሜ መጨመር

ምልክቶች (clinical features)

ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደማቅ ቀይ ደም
በፊንጢጣ አካባቢ ማሳከክ
ከፊንጢጣ የወጣ ሥጋ መሳይ እባጭ
በፊንጢጣ አካባቢ የህመም ስሜት መኖር

የኪንታሮት መዘዞቹ (complications)
ኪንታሮቱ ውስጥ የደም መርጋት (thrombosis)ና ከፍተኛ ሕመም
ወጥቶ አለመመለስ (irreducible)ና መበስበስ (Necrosis)
መመርቀዝ (infection)ና መግል መቋጠር
ያልተለመደ የሰውነት ክፍተት (fistula)
የሰውነት መሰንጠቅ (fissure)
ሰገራን አለመቆጣጠር (Incontinence)
የተለመደ ባይሆንም የደም ማነስ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ኪንታሮት እንዴት ይታከማል?

በመጀመሪያ ሕመሙ ያለበት ሰው እንደማንኛውም ሕመም ወደ ሐኪም ቤት ሄዶ ለመታከም ፍርሃትን/ሐፍረትን ማሰወገድ ይጠበቅበታል፡፡

፩. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን (አትክልትና ፍራፍሬ..) መመገብ
፪. ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድ
፫. ለብ ባለ ውሃ ጨው ጨምሮ 20- 30 ደቂቃ በቀን ሁለቴ ወይም ሦሥቴ መዘፍዘፍ (በበረዶም ሊሆን ይችላል)
፬. ሁሌም ከተፀዳዱ በኃላ በንጹሕ ውሃ መታጠብ
፭. ሻካራ የመፀዳጃ ወረቀቶችን አለመጠቀም
፮. የሰገራ ማለስለሻ መድኃኒት
፯. የሚቀቡ የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት መጠቀም

አብዛኛውን ጊዜ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ብቻ ሕመሙ ሊሻሻልና ሊጠፋ ይችላል፡፡በእነዚህ ሕክምናዎች ካልተስተካከለ
ቀለል ያለ ቀዶ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

መከላከያ መንገዶች

በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ፣ ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድና የሆድ ድርቀትን ማስወገድ
ሰገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያሳልፉ ወደ ሽንት ቤት መሄድ
መፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ
ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶችን ሲያዩ ወደ ሕክምና ተቋም መሔድና ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

ዶ/ር ዮሐንስ ክፍሌ ፤ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ሬዚደንት
857 viewsልዑል, 22:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:35:20 ስለኩላሊት ካንሰር
(Renal cell cancer)
በጥቂቱ እነሆ:-
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

መግቢያ፦ በአሁኑ ጊዜ የኩላሊት ካንሰር(incidence) እየጨመረ ቢመጣም ገዳይነቱ ግን እየቀነሰ መምጣቱን ጥናቶች ያሳያሉ። ይህም ሊሆን የቻለው ህብረተሰቡ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ የማድረግ ልምድ ማዳበሩና በቀላል ምርመራ ማወቅ በመቻሉ በጊዜ ህክምናው ስለሚሰጥ ነው።
****

ለኩላሊት ካንሰር አጋላጭ ነገሮች(risk factors)

1) እድሜ መጨመር(ageing)
በተለይ 60 እና 70ዎቹ የዕድሜ ክልል ላይ የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
2) ወንድ መሆን( male gender)
ወንዶች ላይ የመከሰት ዕድሉ ከሴቶች የበለጠ ነው(M:F=~2:1)።
3) በዘረመል(genetic)
በዘር የመከሰት ዕድሉ በሁለት እጥፍ(2x) የሚደርስ ነው። በዘረመል የሚመጣው ካንሰር በወጣትነት የዕድሜ ክልልና በሁለቱም ኩላሊቶች ላይ ሊከሰት ይችላል።
4) ሲጋራ ማጨስ(smoking)
5) ውፍረት(obesity)
6) የደም ግፊት (hypertension)
7) በደም ዕጥበት የሚታከም የቆየ ኩላሊት ድክመት (chronic renal failure on dialysis)
*

የኩላሊት ካንሰር አይነቶች(histology)

ዋና ዋናዎቹ የኩላሊት ካንሰር አይነቶች:-

1) Clear cell Renal cell cancer
አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው(~75%) የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

2) Papillary Renal cell cancer
ከ10-15% የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

3) Chromophobe renal cell cancer
እስከ 5% የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

4) Cortical duct carcinoma
በአብዛኛው ታችኛው የዕድሜ ክልል ላይ የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር ሲሆን ብዙውን ጊዜ አይከሰትም(rare)።

5) Renal medullary carcinoma
በጣም ሊከሰት የማይችል(very rare) ነገር ግን በጣም ገዳይ የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው። በልዩነት የሲክል ሴል በሽተኞች(sickle cell disease) ላይ ይከሰታል።
እነዚህ የካንሰር አይነቶች በባሪያቸው ቅደም ተከተል ሲቀመጡ
*Papillary RCC(የተሻለው)-->Chromophobe RCC-->Clear cell RCC--> Collecting duct Ca-->Renal medullary ca(መጥፎው)
****

የኩላሊት ካንሰር ምልክቶች

50%ቱ ለሌላ ህክምና በሚደረግ የአልትራሳውንድ/ሲቲ ስካን ምርመራ ወቅት በአጋጣሚ የሚታወቅ/የሚገኝ(incidental) ነው። ይህም ማለት አብዛኛው የኩላሊት ካንሰር ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል።
የሽንጥ ህመም(flank pain)
የሽንጥ ዕብጠት(flank mass)
ደም የቀላቀለ ሽንት(haematuria)
➜እነዚህ ሦስቱ ምልክቶች ከታዩ የካንሰር ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑንም ያመላክታሉ።
ሌሎች ምልክቶች
➜ክብደት መቀነስ
➜የደም ግፊት(hypertension)
➜በደም ውስጥ የካልሽየም መጠን መጨመር(hypercalcemia)
➜የደም ማነስ(anemia) ወይም የደም መብዛት(polycythemia)
➜ የጉበት ችግር መከሰት(Stauffer's syndrome)
የኩላሊት ካንሰር መኖሩ በሚታወቅበት ጊዜ እስከ 20% ድረስ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ተሰራጭቶ ሊገኝ ይችላል። ይህም በደም ዝውውር ወይም በሊፍፋቲክ(hematogeneous or lymphatic) ሊሰራጭ ይችላል። በደም ዝውውር ወደ ሳንባ፣ አጥንት፣ ጉበትና አንጎል ሊሰራጭ ይችላል።
****

የምርመራ መንገዶች
1) አልትራሳውንድ(ultrasound)
ካንሰር መኖር አለመኖሩን በአልትራሳውንድ (በእርግጠኝነት ባይሆንም) ማወቅ ይቻላል።

2) ሲቲ ስካን(CT scan): ከአልትራሳውንድ በተሻለ የካንሰሩን መኖርና የካንሰሩን ደረጃ(stage) ለማወቅ ይጠቅማል።

3) MRI: በCT scan ማወቅ ካልቸቻለ ወይም CT scan ማንሳት የማይቻልባቸው ምክንያቾች ሲኖሩ ይታዘዛል።
****

የኩላሊት ካንሰር ደረጃዎች(staging)

እንደማንኛውም የካንሰር አይነት አራት ደረጃዎች(stage 1-stage 4) ሲኖሩት ደረጃው በጨመረ ቁጥር በካንሰር የመኖር(cancer specific survival)ዕድሜን ይቀንሳል:: ይህም ማለት በደረጃ 1 (stage 1) የ5ዓመት cancer specific survival ከ90%በላይ የሚደርስ ሲሆን በደረጃ 4(stage 4) 5አመት የመኖር ዕድል ደግሞ ከ5% በታች ነው።
****

የኩላሊት ካንሰር ህክምናዎች

1) ቀዶ ጥገና ህክምና(partial/radical/cytoreductive nephrectomy)፦ ለሁሉም የኩላሊት ካንሰር ደረጃዎች የሚደረግ ህክምና ነው(ወደሳንባ፣ አጥንት፣ ጉበትና አንጎል የተሰራጨን ካንሰር ጨምሮ) ።

2) የጨረር ህክምና፦ ወደ አጥንት(spine) እና አንጎል የተሰራጨውን ካንሰር ለማከም እንደ አማራጭ ህክምና ይወሰዳል።

3) Target and immunotherapy: በዋጋ ደረጃ ውድ ሲሆኑ በህይወት የመኖር ጊዜን እምብዛም አይጨምሩ

4) ኬሞ ቴራፒ(chemotherapy): የኩላሊት ካንሰር ሁሉንም ኬሞ ቴራፒዎች መቋቋም ስለሚችል እንደ አንድ የህክምና አማራጭ አይወሰድም።
****

የኩላሊት ካንሰር መጥፎ ትንቢያዎች(poor prognosis signs) ከሚያሳዩት ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።
1) የወረደ የሰውነት ወቅታዊ አቋም(poor performance status)
2) ትልቅ የዕጢ መጠን(larger tumor size)
3) ከፍተኛ የካንሰር ደረጃ(higher tumor stage)
4) የተሰራጨ ካንሰር(distant metastasis)
5) መጥፎ ካንሰር አይነት (bad histology type like collecting duct and renal medullary ca) እና ሌሎችም።
****

መውጫ:- የኩላሊት ካንሰር ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገለት ሰው ከህክምና ክትትል መጥፋት የለበትም ምክንያቱም እስከ 2-4% ድረስ ድጋሜ የመከሰት ዕድል(recurrence) ሊኖር ስለሚችል።

ዶ/ር ልጃለም መኮንን
የኩላሊትና ሽንት ቧንቧ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት(Urologist)
753 viewsልዑል, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 14:05:01 የሬቢስ በሽታ ምንድን ነው?

- በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) የምንለው ሬቢስ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ከእንስሳት ወደ የሰዉ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ ነው።

- የእብድ ውሻ በሽታ የተባለበት ምክንያት በአበዛኛው የቫይረሱ ተሸካሚዎች በአካባቢያችን የሚገኙ ውሾች በመሆናቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ የለሊት ወፍ ፣ ፈረስ ፣ ላም ፣ የቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

- ከዉሻ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የሬቢስ በሽታ በአብዛኛው ታዳጊ ሀገራትን የሚያጠቃ ሲሆን በተለይ ህጻናት ለጆችን ስለበሽታው እና ከትባቱ በቂ ግንዛቤ በሌላቸው የሀገራችን ክፍሎች ላይ በብዛት ይስተዋላል።

መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው?

- በቫይረሱ ከተጠቁ እንስሳት በተለይ ከውሾች ወደ የሰው ልጅ በንክሻ ወይም በመቧጨር ከአፉቸው በሚወጣ ፈሳሽ (saliva) በቀጥታ ቆዳን ዘልቆ የሚገባ ከሆነ ወይም በሰወነታችን ትኩስ ቁስል (fresh skin wounds) ካለ ሊተላለፍ ይችላል።

- በተለይ የተነከስነው ወይም የተቧጨርነው አንገት እነ ከአንገት በላይ ከሆነ ቫየረሱ በፍጥነት ወደ ማእከላዊ የነርቭ ስርአት (central nervous system) ቅርብ ስለሆነ በፍጥነት ወደ አንጎል (brain) በመድረስ ለሞት ሊዳርገን ይችላል።

- የሬቢስ በሽታ theroetically ከቫይረሱ ተሸካሚ ሰው ወደ ሰው በንክሻ ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል።

ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?

-አንድ ሰው በቫይረሱ ከተጋለጠ በዃላ ምልክት እስከሚያሳይ (incubation period) ከ3ሳምንት እስከ 3 ወር ሊቆይ ይችላል።

- ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች የተነከሰበት ቦታ ለይ መጠዝጠዝ አና መደንዘዝ ፣ ትኩሳት ፣ እራስ ምታት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ጡንቻ አካባቢ የህመም ስሜት ፣ ፍራቻ ፣ ከመጠን በላይ ምራቅ መኖር ፣ ለመዋጥ መቸገር ፣ ቅዠት ፣ ግራ መጋባት ፣ ዉሃን መፍራት (hydrophobia) ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ የከፉ ደረጃ ሲደርስም ለኮማ ከዛም ለሞት ሊዳረግ ይችላል።

- ምልክቶቹን ማሳየት የጀመረ ሰው የመዳን አድሉ እጅግ በጣም ጠባብ ነው።

እንዴት መከላከል አነችላለን?

- የቤትም ሆነ የዱር እንስሳ ካለን ማስከተብ
-ሌላው መርሳት የሌለብን ነገር ክትባቱን ባልተከተቡ እንስሳት ከተነክሰን ወይም ጥርጣሬ እንኳን ቢኖርብን ግዜ ሳንሰጥ ወዲያውኑ የህክምና ባለሙያ በማማከር የተጋላጭነት ክትባቱን (post exposure prohpylaxis) መዉሰድ አለብን።

ህክምናውስ?

- የሬቢስ በሽታ ይሄ ነው ሚባል ህክምና የለውም። ምክነያቱም የሬቢስ ቫይረስ ሰውታችን ውስጥ ከገባ እራሱን ስለሚደብቅ በጸረ ቫይረስ (Anti viral) አንኳን መዳን አይችልም።

- ስለዚህ ማንኛውም አይነት ቁስል በሰውነታችን ለይ ካለ በአግባቡ መታከም እና ተጋላጭ ከሆንን ጊዜ ሳነሰጥ የህክምና ቦታ በመሄድ ከትባቱን መከተብ ብቸኛ አማራጮች ናቸው።

- በአጠቃላይ የሬቢስ በሽታ ችላ የማይባል ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ ነው።

ጤና ይብዛሎ
Dr. Ermias Mamo

via: HakimEthio
955 viewsልዑል, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 11:54:08 የጡንቻ መሸማቀቅ

የጡንቻ መሸማቀቅ በድንገት ሊከሰት የሚችል ነው። በብዛት እግር እና እጃችን ላይ ሚከሰት ሲሆን አልፎ አልፎም በሆዳችን አካባቢ ሊከሰት ይችላል።

በርካታ ጊዜም ከእርግዝና፣ ከሰውነት ድርቀት እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል።

የጡንቻ መሸማቀቅ በሚያጋጥመን ጊዜ የህመም ስሜቱ በደቂቃዎች ውስጥ የሚለቅ ሲሆን ከሰዓታት በላይ እኛ ላይ ከቆየ ግን ችግሩ ከዛም በላይ ሊሆን ይችላል።

የጡንቻ መሸማቀቅ እንዴት ይከሰታል?

በተመሳሳይ አቅጣጫ ለረጅም ሰዓት በመቀመጥ ለምሳሌ ለረጅም ሰዓት እግራችንን አጣምረን መቀመጥ።
ከልክ ያለፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራት።
በሰውነታችን ውስጥ ያለው የጨው እና የውሃ መጠን ማነስ።
በተገቢው ሰውነታችንን ሳናሟሙቅ ስፖርት መስራት ይከሰታል።

ለችግሩ ተጋላጭ እነማን ናቸው?

በሞቃት አካባቢዎች የሚሰሩ የኮንስትራክሽንና የፋብሪካ ሠራተኞች
የደም ቧንቧ አካባቢ ችግር ካለ
በልብ ድካም፣ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል እና የስኳር በሽታ ተጠቂ መሆን
ሥር የሰደደ የነርቭ ሕክምና ችግር ያለባቸው ታካሚዎች የጡንቻ መኮማተር ተጋላጮች ናቸው፡፡

የጡንቻ መሸማቀቅ በሚግጥመን ጊዜ ምን ማድረግ አለብን?

የጡንቻ መሸማቀቅ በሚያጋጥመን ጊዜ ሚፈጠርብንን ህመም ስሜት ለማስታገስ የተለያዩ ዘዴዎች እንዳሉ ይነገራሉ። ከእነዚህም ውስጥ:-

የተኮማተረውን ወይም ተሸማቀቀውን ጡንቻ እንዲወጠር በማድረግ ማፍታታት፣ እኩል የሆነ መሬት ላይ እግራችንን በማስቀመጥ እግራችንን መዘርጋት፣ ቀስ እያልን መራመድ።
ሆዳችን አካባቢ በተለይም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት የጡንቻ መሸማቀቅ ደግሞ ለብ ያለ ውሃ በእቃ ውስጥ በማድረግ ሆዳችንን በስሱ ማሸት ይመከራል።
የተሸማቀቀዉን ወይም የተኮማተረውን ጡንቻ በስሱ በማድረግ ማሸት
በሀኪም ትእዛዝ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን መውሰድ።
ከዚህ አልፎ ግን በተደጋጋሚ ጡንቻ መሸማቀቅ የሚጋጥመን ከሆነ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ሀኪም ማነጋገር ይኖርብናል።

የጡንቻ መሸማቀቅ እንዳያጋጥመን ምን ማድረግ አለብን?

የአካል ብቃት ወይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ከመስራታችን በፊት ሰውነታችንን በደንብ ማማሟቅ እና ሰርተን ስንጨርስም ሰውነታችንን ለማረጋጋት ወይም ለማቀዝቀዝ ሚረዱንን እንቅስቃሴዎች ማድረግ።

ውሃን በበቂ ሁኔታ መጠጣት በተለይም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በምናደገርግበት ጊዜ ሁሌም ከመስራታችን በፊት እንዲሁም እየሰራን ደግሞ ቢቻል በ15 ደቂቃ ልዩነት ዉሃ መጠጣት አለብን።

በካልሽየም እና በፖታሲም የበለጸጉ ምግቦችን ማለትም እንደ ሙዝ እና ሌሎችም አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር ይመከራል።

#EthioTenna
1.0K viewsልዑል, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 11:20:47
765 viewsልዑል, 08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 11:20:39 "አንድ ብር ላይ ጥያቄ አለን!"

እነ አምስት ሳንቲም ፣ አሥር ሳነቲም ፣ ስሙኒ እና ሽልንግ ካየናቸዉ ዓመታት እያለፉ ነዉ፡፡ ያኔ ዶሮ እና በግ እንዳልገዙ አሁን ዋጋ ከማጣታቸዉ የተነሳ መሬት ተጥለዉ ቢገኙ እንኳን የሚያነሳቸዉ መገኘቱ ያጠራጥራል፡፡

አሁን በሳንቲሞቹ ዓለም ዘመኑ የአንድ ብር ነዉ!! ከዋጋዋ አንጻር በወረቀት (ኖት) መታተም ስላልመጠናት ይሁን ወይም በሌላም ምክንያት ፣ በኛ ትዉልድ በወረቀት የምናዉቃት የልጅነታችን ፈርጥ የነበረችዉ አንድ ብር ሳንቲም ሆና ከመጣች ሰነባብታለች ፤ ሀገሪቱን አጥለቅልቃለች፡፡

ባዕድ ነገሮችን መዋጥ (Foreign body swallowing) የአዕምሮ ሕመም ተጠቂ የሆኑ አዋቂዎችን ሳይጨምር ከሞላ ጎደል ሁልጊዜ ሕጻናትን የምያጋጥም ችግር ነዉ፡፡ በተለይም ከ6 ወር እስከ 4 ዓመት ባለዉ የዕድሜ ክልል ያሉ ሕጻናት የ ችግሩ ሰለባ ይሆናሉ፡፡ የተለያዩ ጌጣ ጌጦች ፣ ሳንቲሞች ፣ አሻንጉሊት… ያገኙትን ይዉጣሉ፡፡

በምንሰራበት ሆስፒታል አንድ ዓመት በሚያህል ጊዜ ዉስጥ ወደ 6 ሳንቲም የዋጡ ህጻናት ታክመዉ ነበር፡፡ ከስድስቱ ሁለቱ በቅርብ በሳምንት ልዩነት የመጡ ነበሩ ፣ ሁለቱም የተዋጡት ሳንቲሞች …አንድ ብር!! ያኔ ነበር እንግዲህ አንድ ብር ጥያቄ ቢጤ የጫረችብን፡፡

አንድ ብር ስፋቷ (Diameter) ሲለካ 2.7 cm አከባቢ ነዉ፡፡ የሰዉ ልጅ ጉሮሮዉ (Esophagus) በተፈጥሮዉ ሦስት ቦታዎች ላይ ጠበብ ያለ (Constrictions) ነዉ። የመጀመርያዉና ብዙዉን ጊዜ (70%) የተዋጡ ባዕድ ነገሮች የሚቀረቀሩበት ጥበት (Cricopharyngeal sphincter) ስፋቱ (Luminal diameter) 1.5 cm ሲሆን ሁለተኛዉ ጥበት (Aortic arch እና bronchus ጉሮሮን የሚያቋርጡበት) 1.6 cm አከባቢ ነዉ፡፡ ሦስተኛዉ የጉሮሮ ጥበት (Lower esophageal sphincter) ደግሞ ከ1.6 - 1.9 cm ይሰፋል።

ጉሮሮ ከጡንቻዎች የተነሳ የመለጠጥ ባህርይ ቢኖረዉም የተጠቀሱት ቁጥሮች የአዋቂን ጉሮሮ ስፋት የሚያሳዩ ሲሆን የህጻናቱ እጅጉን ያነሱ ናቸዉ፡፡ስለዚህ አንድ ብር በስፈቷ ለ ሕጻናት ጉሮሮ ትልቅ ፈተና ነዉ፡፡

እንደምንም ጉሮሮን ቢያቋርጥ ጨጓራ ዉስጥ ሌላ ፈተና ይጠብቀዋል፣ ከ 2cm በላይ ስፋት ያላቸዉ ጠጣር ነገሮች ከጨጓራ ሲወጡ “pyloric sphincter”ን የማለፍ ዕድላቸዉ አነስተኛ ነዉ፡፡ከዚያም ቢያልፉ “Ileocecal valve” ቀጣዩ ተቀርቅረዉ የሚቀሩበት ፈታኝ ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡
.

አንድ ብር በዋጋዋ ትንሽዬ ብትሆንም ፈተናዎቿ ብዙ ናቸዉ፡፡ ባዕድ ነገር መዋጥን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባይቻልም አንድ ብር የሕጻናቱን የሆድ እቃ (GI tract anatomy) ባገናዘበ መልኩ መጠኗ (Diameter) ቢቀነስ ወይም ከ ሳንቲምነት ወደቀደመዉ የብርነት (ኖት) ክብሯ ብትመለስ ችግሩንና ችግሩን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች የሚፈጠሩ ችግሮች (ከሰመመን ፣ ቀዶ ህክምና… ወዘተ ጋር ተያይዘዉ) ይቀረፉ ይሆናል፡፡

Dr. Ayenew Gaye & Dr. Seyfeyared Abebaw
(Schwartz’s principles of surgery for the numbers)

via: HakimEthio
864 viewsልዑል, 08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 15:15:04 የሽንትዎ ቀለም ስለሰውነትዎ ጤና ምን ይነግርዎታል?

ሽንት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ክፍል ሲሆን 95% ውሀ 5% ኤሌክትሮላይቶች እና ቆሻሻዎች ናቸው ።
ጤናማ እና በቂ ፈሳሽ በሚዎስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ብዙ የጎላ ቀለም በሌለው እና ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም መካከል ነው፡፡በቂ ፈሳሾችን በማይወስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ይበልጥ የተከማቸ ሲሆን ወደ ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም የዓምበር ቀለም ይለወጣል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም እና መጠን እየዎሰዱ ያሉትን የውሀ መጠን ፣ ምግብ ፣ ቫይታሚን ጠቋሚ ነው።
የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች እና ቀለሞች እንዲሁ ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተለያዩ የሽንት ቀለም አይነቶች እና ምክንያቶች እናያለን ።

1. በጣም ነጭ ከሆነ ከመጠን በላይ ውሀ እየጠጡ እንደሆነ ያመለክታል ። ይህም የተለያዩ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በተለይም ፓታሽየም እና ሶድየም መጠናቸው እንዲያንስ ያደርጋል ይህም የልብ ጡንቻን ይጎዳል ።

2. ጥቁር ቢጫ - ይህም በቂ ውሀ እየወሰዱ እንዳልሆነ ወይም ኬቶን በሽንት ውስጥ መኖር ሊሆን ይችላል ። በቂ ውሀ አለመውሰድ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር ፣ የሰውነት ፈሳሽ መቀነስ ፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል ። ኬቶን የሚፈጠረው በቂ የሆነ ስኳር (glucose ) ሳያገኝ ሲቀር እና ቅባት (fat) ለሴሎች ጉልበት ሲጠቀም ነው ። ይህም በሽንት መልክ ይወጣል ። ከፍተኛ የኬቶን መጠን አደገኛ የስኳር በሽታ ጉዳትን (DKA) ተከትሎ ሊመጣ ይችላል ። አነስተኛ መጠን ከሆነ ለረጅም ጊዜ ካልተመገብን ሊከሰት ይችላል ።

3. ደማቅ ቢጫ - ከበቂ በላይ ሰው ሰራሽ ቫይተሚን ቢ እየወሰዱ ከሆነ

4. ቀይ- ይህ የሚፈጠረው ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ነው ። ይህም በኩላሊት ጠጠር ፣ የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ፣ የኩላሊት ካንሰር ፣ ከባድ ስፓርት

5. ጥቁር ብርቱካናማ / ቡናማ - የጉበት ችግር ያመለክታል ። የጉበት ፣ የሀሞት ቀረጢትና የቱቦዎች ችግር ተከትሎ የቢሊሩቢን በደም ውስጥ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።

6. ሀምራዊ - አነስተኛ ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ወይም ቀይ ስር ከበላን

7. ሰማያዊ - የካልስየም መብዛት /hypercalcemia

7. አረፋ ካለ - ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መኖር ፤ ይህም የኩላሊት ቁስለት ፣ የኩላሊት ጠጠር ፣ የልብ እና የኩላሊት መድከም ፣ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች

8. ብዙ የሚሸኑ ከሆነ - በሽንት ውስጥ የስኳር መኖር ነው ፤ ይህም የስኳር በሽታ ያመለክታል ።
1.5K viewsልዑል, 12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 20:01:30 ለምፅ | Vitiligo

ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት (acquired) የቆዳ ቀለም ባለመመረቱ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው

ለምፅ በንክኪ አይተላለፍም

ለምፅ ከህጻናት ጀምሮ በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ሊታይ ይችላል

ለምፅ በምን ምክንያት ይከሰታል?

ምክንያቱ ይሄ ነው ተብሎ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ፤ የተለያዩ መላምቶች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፤ከነዚህም መካከል "የሰውነታችን በሽታ የመከላከያ ስርአት (immunity system) የራሳችንን የቆዳ ቀለም አምራች ህዋሳትን(melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው" የሚለው መላምት በይበልጥ ተቀባይነት አለው።

በዚህም ምክንያት ለምጽ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚከሰቱ ሌሎች ህመሞች (autoimmune diseases) ጋር ተያያዥነት አለው ተብሎ ይታሰባል ፤ ለምሳሌ ከየስኳር ህመም፣ የእንቅርት ህመም (autoimmune type)፣ ላሽ (alopecia areata)....

ለምፅ ከጭንቀት (emotional stress)፣ ከእርግዝና፣ ከአደጋ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል

የለምፅ ምልክቶች

ለምጽ ያለበት ቦታ ወደ ነጭነት የሚያደላ ቀለም ሲኖረው ከዚህ ውጪ ማሳከክ ወይም ቦታው ላይ ቅርፍቶች መኖር የለምጽ ባህሪ አደለም

በማንኛውም የቆዳችን ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

ለምፅ አንድ ቦታ ላይ ብቻ (focal)፣ በግራ ወይም በቀኝ የሰውነት ክፍል ብቻ (segmental) ወይም አብዛኛው የቆዳችኝ ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

የለምፅ ህክምና

የህክምናውን አይነት የሚወስኑ ሁኔታዎች ፦
የህመሙ ጥንካሬ (severity)
እየተስፋፋ መሆኑ ወይም ባለበት መቆሙ
የህክምናው በቀላሉ መገኘት እና የህመምተኛው የመክፈል አቅም...

የህክምና አይነቶች
የሚዋጥ
የሚቀባ
Phototherapy (ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ ብርሀንን በመጠቀም የሚሰጥ ህክምና)
Excimer laser
የቀዶ-ጥገና (surgery) ህክምና

የማንጣት ህክምና (depigmentation)
አብዛኛው የሰውነት ክፍል በለምፅ ከተጠቃ እና ለማከም አስቸጋሪ ከሆነ ጤነኛውን የቆዳ ክፍል በማንጣት የማመሳሰል ሂደት ነው (Michael Jackson ይህ ህክምና ተደርጎለታል)

ስለህክምናው ሂደት ማወቅ ያለብን

ህክምናውን ከጀመርን በኋላ የህክምናውን ውጤት ለማየት ከ 2-3 ወር ሊፈጅ ይችላል

ጠቅላላ ህክምናው ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ያለማቋረጥ መከታተል ያስፈልጋል

ህክምናው ከተጠናቀቀ በኋላ ለምፁ እንደገና ሊመለስ ይችላል

ከንፈር ላይ፣ጣት ላይ እንዲሁም ከቆዳው በተጨማሪ ፀጉርም አብሮ ነጭ ከሆነ የመዳን እድሉ ዝቅተኛ ነው

ለምፅን ባንታከምስ?

ለምፅ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ጫና ያሳድራል
እየሰፋ ሊሄድ ይችላል
ቆዳችን በፀሐይ ጨረር እንዲጠቃ ሊያረግ ይችላል (ፀሐይ መከላከያ/sunscreen መጠቀም ያስፈልጋል)

በመጨረሻም

ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
1.4K viewsልዑል, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 14:36:14
1.1K viewsልዑል, 11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 14:35:45 በሰዉነታችን ዉስጥ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸዉ የሁለት አጥንቶች መገናኛ አካባቢ የሚገኙ መገጣጠሚያ ተብለዉ የሚጠሩ የሰዉነት ክፍሎች አሉ። እነዚህ አካላት በብዛት ለእንቅስቃሴ ይረዳሉ።

ከነዚህ መገጣጠሚያዎች መካከል የታችኛዉ የመንጋጋ አጥንት ከጭንቅላት አጥንት ጋር የሚገናኝበት አካባቢ የሚገኘዉ መገጣጠሚያ ቴምፖሮማንዲቡላር ጆይንት (TMJ) ይባላል።

አፋችን ስንከፍትና ስንዘጋ ከጆሯችን ፊት ለፊት የምንዳብሰው እንቅስቀሴ የዚህ መገጣጠሚያ ቦታ ነዉ። ይህ መገጣጠሚያ በጣም አስፈላጊ ሲሆን ምግብ ለማኘክ፣ ለንግግር ፣ አፋችን ለመዝጋትና ለመክፈት ፣ ለፊታችን እድገት ና ቅርፅ ይጠቅማል።

መገጣጠሚያ በሁለት አጥንቶች መካከል ያለ ክፍተት ሲሆን በዉስጥ ፈሳሽ ይይዛል እንደ ቲኤምጀ አይነት መገጣጠሚያ ደግሞ በሁለቱ አጥንቶች መካከል ዲስክ የሚባል የመገጣጠሚያ አካል አለዉ ።

በተለያዩ ምክንያቶች እንዚህ ሁለት ተገጣጣሚ አጥንቶች በሙሉ ወይንም በከፊል ፣ በስጋ ወይንም በአጥንት ሲያያዙ (fusions) ከዚህ በፊት በነፃነትና በቀላሉ ይንቀሳቀስ የነበረ መገጣጠሚያ ቀስበቀስ እንቅስቃሴዉን ይቀንሳል (ይደርቃል)። በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ እንቅስቀሴ ያቆማል።

ይህ አይነት ደዌ የመገጣጠሚያ መጣበቅ (አንኪሎሲስ) ይባላል። ይህ የመገጣጠሚያ መጣበቅ በቲኤምጀ ላይ ሲከሰት ነዉ የታችኛዉ የመንጋጋ አጥንት ከጭንቅላት አጥንት ጋር ተጣበቀ (TMJ ankylosis) ቲኤምጀ አንካይሎሲስ የምንለዉ።

ይህን ክስተት በአብዛኛዉ የሚከሰተዉ በፊት አጥንቶች ላይ በሚከሰት አደጋ (trauma) ሲሆን ፣ የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን ና በመገጣጠሚያ አካባቢ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖችም ይህ አይነት ክስተት ሊያመጡ ይችላሉ።

ይህ የመገጣጠሚያ መጣበቅ የሚያስከትለዉ የጤና ጠንቆች ምንድን ናቸዉ?

ይህ ክስተት ብዙ የችግሮችን የሚያስከትል ሲሆን ፣ የኑሮ ሁኔታን ፣ ምግብን እኝኮ መብላትን ፣ ንግግርን ያስተጓጉላል ። እንዲሁም በአየር እጥረት የእንቅልፍ መቆራረጥ ችግር ፣ የፊት ቅርፅ ና እድገትም በዚሁ ክስተት ተፅኖ ይደርስበታል።

የጥርስ ንፅህና መጠበቅ ስለማይቻል የጥርስ መበስበስ ፣ የጥርስ ደጋፊ አካለት ኢንፌክሽን ፣ የአፍ ሽታም በዚህ ክስተት ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ!

የዚህ ደዌ ምልክቶች ምንድን ናቸዉ?

ዋናዉ ምልክት ቀስበቀስ የአፋችን ክፍተት እየቀነሰ መሄድ ና በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ አፋችንም መክፈት አለመቻል።

መገጣጠሚያችን ጤነኛ ከሆነ አፋችን እስከ መጨረሻዉ ሲከፈት የራሳችን ሶስት እጣቶች አቁመን ማስገባት አለበት ይህም በአማካይ ከ 3.5- 5.5 ሳንቲ ሜትሮች ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪ ደንበኛችን በህፃንነቱ በፊቱ መዉደቅ ወይንም ተደጋጋሚ የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን ወይንም የጀሮ ኢንፌክሽን እንደነበረበት ሊናገር ይችላል።

ይህ አይነት ክስተት በትክክል የመገጣጠሚያ መጣበቅ መሆኑን ከታማሚዉ ታሪክ መረዳት ቢቻል የሚረጋገጠዉ ግን በጭንቅላት ራጅ ወይንም ሲቲ ስካን ነዉ ።

በራጅ ወይንም በሲቲ ስካን በሽታዉና የበሽታዉ ደረጃ ከተረጋገጠ በኋላ ነዉ በፊት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቶች የፊት ቀዶ ህክምና ተደርጎ የተጣበቀዉ መገጣጠሚያ የሚታከመዉ። በቀዶ ህክምናዉ መገጣጠሚያዉ አካባቢ ቢያስብ 1.5 ሳንቲ ሜትር ክፍተት መፈጠር አለበት።

ይህ ቀዶ ህክምና የማግዚሎፋሻ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቶችና የአነስቴዥያ ኤክስፐርቶችን የሚጠይቅ ከባድ ሰርጀሪ ስለሆነ በተሻለ ተቋምና ባለሙያዎች ባሉበት ሆስፒታል እንዲሰራ ይመከራል።

ሰርጀሪዉ ተሰርቶ የተጣበቀዉ መገጣጠሚያ ከተላቀቀ በኋልም ተመልሶ የመጣበቅ ስጋት ስላለ መገጣጠሚያዉን በተደጋጋሚ ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል።

ይህ ክስተት በብዛት በፊት ላይ በሚደርስ አደጋና በኢንፌክሽን ምክንያት ሊከሰት የሚችል በመሆኑ እነዚህን በማስወገድ ወይንም በወቅቱ ተገቢዉን ምክርና ህክምና በማድረግ ልንከላከለዉ የምንችል ደዌ ነዉ።

እንዳለመታደል ሁኖ ክስተቱ ከተከሰት ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች በጤና ላይ ሊያመጣ ይችላል። ስለሆነም ልጆቻች በፊታቸዉ ከወደቁ ወይንም ሸንጎበታቸዉ ወይንም አገጫቸዉ አካባቢ ቁስለት ከተመለከትን ፣ ተደጋጋሚ የጀሮ ኢንፌክሽን ገጥሟቸዉ ከሆነ ይህ ከፍተኛ የጤና እክል ሊያስከት የሚችለዉ የመገጣጠሚያ መጣበቅ ሊያጋጥምስቸዉ ስለሚችል ክትትል የሚያሻቸዉ መሆኑን ና በአጋጣሚ ከላይ የጠቀስኳቸዉ ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ አፍን የመክፈት አቅም ቀስ በቀስ መቀነስ ካሳየ የሚመለከትዉን የጤና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል።

የጤና ባለሙያዎችም ይህን አይነት ችግር ሲጠርጥሩ ወደ ተሻለ የጤና ተቁማና ባለሙያ ሪፈር ማድረግ ይገባቸዋል የሚል ምክሬን ለመለገስ እወዳለሁ ።

ዶ/ር ፀጋነዉ አዲሱ ተካ ፥ የአፍ ዉስጥ፣ መንጋጋና የፊት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት

via: HakimEthio
1.0K viewsልዑል, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ