Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ዓዳም- Tena Adam

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotena1 — ጤና ዓዳም- Tena Adam
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotena1 — ጤና ዓዳም- Tena Adam
የሰርጥ አድራሻ: @ethiotena1
ምድቦች: ውበት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.69K
የሰርጥ መግለጫ

👉 ይህ የTelegram channel ስለ ጤናዎ በጥቂቱ ግንዛቤ ያስጨብጣል።
👉 ማንኛውንም ጤና ነክ ጉዳይ እናማክራለን
📝 (ጤና ዓዳም- Tena Adam 📁📂
ጥያቄ አስተያየት 👉👉 @Amydan

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-20 17:18:48 የማህፀን ሞኝ እጢዎች (Uterine fibroids)
በዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት

ትክክለኛ የአማርኛ ትርጓሜ ባይኖራቸውም Uterine fibroids የማህፀን ሞኝ እባጮች/እጢዎች ብንላቸው ካላቸው ባህሪ ጋር ያስኬዳል ብዬ አስባለሁ።

የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) ከማህፀን የመሀከለኛው ክፍል ወይም ከማህፀን ጡንቻ ላይ የሚነሱ እጢዎች ናቸው።

ብዙን ጊዜ እጢ ስንል በጭንቅላታችን የሚመጣው መጥፎና የካንሰርነት ባህርይ ያለው ነገር ቢሆንም እነኚህ uterine fibroids ወይም የማህፀን ሞኝ እባጮች ግን የካንሰርነት ባህሪ የሌላቸው እና ወደ ካንሰር የመቀየር እድላቸውም እጅግ በጣም አናሳ እና ጥናቶችም እንደሚያሳዩት በዚህ እጢ ከታከሙ 580 ሴቶች አንዷ ብቻ ይህ እጢ ወደ ካንሰር ሊቀየርባት እንደሚችል ያሳያሉ።

የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) አንዲት ሴት በመውለጃ ዘመኗ ላይ የሚከሰቱ የእጢ አይነቶች ሲሆኑ በተለይ ደግሞ ከ 30 እስከ 40 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ላይ አብዝተው ይከሰታሉ።

እነኚህ እጢዎች ብዙን ጊዜ የህመም ስሜት ስለሌላቸው ነው እንጂ እስከ 70% የሚሆኑ ሴቶች ይህ እጢ በማህፀናቸው ላይ አለ ተብሎ ይታሰባል።

ይህ እጢ ለምን ይከሰታል

የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) ለምን እንደሚከሰቱ እርግጥ የሆነ ጥናት ባይኖርም መላምቶቹ ግን የሚያሳዩት በማህፀን ጡንቻ ውስጥ የሚገኙ የዘረመል ችግር ያለባቸው የጡንቻ ህዋሶች Estrogen የተሰኘው ንጥረ ነገር(hormone) ሲነካቸው ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ ስለሚራቡ እና ወደ እጢነት ስለሚያድጉ ነው።

የዚህ እጢ ምልክቶች ምንድን ናቸው

ባብዛኛው ጊዜ ምንም አይነት ምልክት የሌላቸው ሲሆን ለሌላ ህመም በሚደረግ የአልትራሳውንድ ምርመራ እንደ ድንገት ሊገኙ የሚችሉ እጢዎች ናቸው። ነገር ግን ከዛ ባለፈ ህመሙ የሚሰማቸው ሴቶች የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ:-

የወር አበባ ለውጥ
የወር አበባ መብዛት እና መቆየት ካለበት ጊዜ በላይ አሳልፎ ከቆየ
የወር አበባ ህመም
የደም ማነስ ምልክት:- ብዙ ደም ከመፍሰስ የመጣ

የወገብ ህመም እና ከእንብርት በታች የህመም ስሜት፣ በተለይ በግንኙነት ጊዜ ሊብስ የሚችል

ሽንት እንቢ ማለት ወይም ቶሎ ቶሎ ማለት

የሰገራ ድርቀት፣ እና የሆድ ህመም

በሆድ ላይ ቀስ ብሎ እየጨመረ የሚሄድ እብጠት ማስተዋል

በተደጋጋሚ ውርጃ መከሰት

እርግዝና እንዳይፈጠር መከልከል

እነኚህ እባጮች/እጢዎች መቼ ነው ህክምና የሚያስፈልጋቸው

ብዙን ጊዜ ምንም አይነት ህመም ከሌላቸው በጊዜ ሂደት አንዲት ሴት ስታርጥ ወይም የወር አበባ ማየት ባቆመች ጊዜ መጠናቸው እየኮመሸሸ እና እያነሰ ስለሚመጣ በመድሀኒትም ሆነ በቀዶ ህክምና መታከም አያስፈልጋቸውም፤ ነገር ግን አንዲት ሴት :-

በእጢው ምክንያት የመጣ የወር አበባ መዛባት ፣ በብዛት ካለ እና ደም ማነስ ካመጣባት

ከፍተኛ የሆነ ህመም ካላት (ከእጢው ጋር የተገናኘ)

እጅግ መጠኑ የበዛ እጢ ከሆነ

እርግዝና ከከለከላት ወይም ደግሞ እርግዝና ተከስቶ ለውርጃ እንደምክንያት ከሆነ (ሌሎች እርግዝና የሚከለክሉ ወይም ውርጃን የሚያመጡ ነገሮች ሁሉ ከተጣሩ በውሀላ)

ሊሰጡ የሚችሉ ህክምናዎች

የመድሀኒት ህክምና:- ይህ ህክምና የሚፈሰውን የደም መጠን ለመቆጣጠር የሚሰጥ ህክምና ነው።

ኦፕሬሽን :- ይህ እጢውን በኦፕሬሽን የማውጣት ህክምና ሲሆን ፤ በተጨማሪ ግን የተለያዩ የኦፔሬሽ አይነቶችም ሊኖሩ ይችላሉ (በኛ ሀገር የማይሰሩም አሉ)

ማህፀንን እስከነ እጢው ማውጣት:- ይህ ኦፕሬሽን ሴቲቱ ወልዳ የጨረሰች ከሆነች ወይም ደግሞ እጢውን ለማውጣት በሚደረግ ኦፕሬሽን ጊዜ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ማህፀን ማውጣት የሴቲቱን ህይወት የሚያተርፍ አንዳች አማራጭ ሆኖ ሲገኝ የሚደረግ የኦፕሬሽን አይነት ነው።
628 viewsሠው መሆን, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 10:37:43 ትኩረት ልናደርግባቸው የሚገቡ የጉበት በሽታዋና ዋናዎቹ ምልክቶች

1) የሰውነት ክፍል ማበጥ፥ በሰውነት ውስጥ የፈሳሽ ክምችት እና ጥርቅም የከፍተኛ የሆነ የጉበት ጉዳት እንደተከሰተ ማሳያ ምልክት ነው።
ይህም የአልበሚን መጠንን ከፍ በማድረግ በደም ውስጥ አላስፈላጊ እና ከመጠን በላይ የሆነ ፈሳሽ እንዲኖር ያደርጋል፤ ይህ ሂደት ደግሞ የችግሩ ተጠቂ የሆነውን ሰውነት በአላስፈላጊ ሁኔታ ያሳብጠዋል።
2) የቆዳ እና የአይን ቀለም መቀየር፥ በተለምዶ የወፍ በሽታ ተይዟል በሚል ምክንያት ባህላዊ ህክምና የሚደረግለት የቆዳ በተለይም ደግሞ የአይን ቀለም ወደ ቢጫነት መለወጥም ጉበት በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን ማሳያ ምልክት ነው። ይህ የሰውነት እና የአይን ወደ ቢጫነት መቀየር ደግሞ ደምን በሃሞት እንዲቀላቀል ያደርገዋል
3) የሆድ ህመም፥ በላይኛው እና በታችኛው የቀኝ የሆድ ክፍል የሚከሰት የሆድ ህመም የዚህ ችግር ተጠቂ ስለመሆንዎት ማሳያ ነው፤ በእነዚህ የሆድ ክፍሎች ላይ የውጋት እና ትር ትር የሚል ተደጋጋሚ ስሜት የዚህ በሽታ ምልክቶች ናቸው።
4) የሽንት ቀለም መቀየር፥ ይህ ሁኔታ ከተከሰት ጉበት በኩላሊት በኩል የሚያደርገውን የማጣራት እና ፅዳጅን የማስወገድ ሂደት አደጋ ላይ ነው ማለት ነው፤ የሽንት ቀለም ጠቆር ያለ ቢጫ አይነት ቀለም ሲኖረው።
5) የሰውነት መቆጣት፥ ሌላው የጉበት በሽታ ተጠቂ ስለመሆንዎት ማሳያ መንገድ ደግሞ የቆዳ ላይ መቆጣት ነው፤ የፈሳሽ በሰውነት ውስጥ በበቂ ሁኔታ አለመኖር ቆዳን በማስቆጣት የማሳከክ እና የማደብደብ ምልክት ያሳያል።ከዚህ ባለፈም ቆዳን ወደ ቢጫነት የመቀየርና በእግር የውስጠኛው ክፍልና የእጅ መዳፍን ማቅላትም ሌላው ምልክቱ ነው።
6) ተደጋጋሚ የሆነ የማቅለሽለሽ ስሜት፥ ጉበት ላይ የሚደርስ ጉዳት ጨጓራ ብዛት ያለው አሲድ እንዲረጭ በማድረግ ለጨጓራ ህመም ይዳርጋል፤ በዚህ ሂደት ውስጥም ተደጋጋሚ የማቅለሽለሽና የማስመለስ ችግር ይከሰታል።
7) የምግብ ፍላጎት ማጣትና መቀነስ፥ የምግብ ፍላጎት ማጣትና መቀነስ ዋናውና አንደኛው ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ ጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ማሳያ ሲሆን ልዩ የሆነ የህክምና ክትትልም ያስፈልገዋል።
ከዚህ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ፈጣን የሰውነት ክብደት መቀነስ ደግሞ ለዚህ ማረጋገጫው ነው። ለዚህ ችግር የሚታዘዙ ንጥረ ምግቦች ታማሚውን ለማገገም ሊረዱት ይችላሉ።
8) በሰውነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የፈሳሽ ክምችት፥ ከባድ የጉበት ላይ ጉዳት ለበርካታ ጊዜያት በሰውነት ውስጥ፤ በተለይም በእግር፣ በጉልበት፣ በታችኛው የመጫሚያ ክፍል እና በሆድ አካባቢ ለበርካታ እና ረጅም ጊዜ የሚቆይ የፈሳሽ ክምችትን ያስከትላል።

ከዶክተር ሀያት ሸረፋ
ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ
592 viewsሠው መሆን, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 06:03:01 በጨጓራዎ ውስጥ የሚመነጨውን ከመጠን በላይ አሲድ(Hyperacidity) በቀላሉ በማስወገድ የቃር ችግሮን በነዚህ ምክሮች ያስወግዱ

ምግብን እንዲፈጭ የሚያደርግ ከጨጓራ የሚመነጭ ፈሳሽ ጋስትሪክ ጁስ ይባላል፡፡ የሚመነጨው አሲድ ማለትም ሐይድሮክሎሪክ አሲድ የበዛ እንደሆነ ሐይፐርአሲዲቲ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ ነው በጨጓራ ላይ ቁስል የሚያስከትለው፡፡

ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ መከሰቱን የሚሳብቁ ምልክቶች

1. የሚያቃጥል የሕመም ስሜት ከጨጓራ ተነስቶ እስከ ደረት አልፎም ጉሮሮ ጋር የሚደርስ ቃር፡፡

2. መራራ አሲድ ወደ ጉሮሮ ወይም አፍ መድረስ፡፡

3. ሆድ መነፋት፡፡

4. ደም ወይም ጥቁር ነገር የቀላቀለ አይነምድር፡፡

5. ደም የተቀላቀለ ትውኪያ፡፡

6. ማግሳት፡፡

7. ምግብ ያለመፈጨት ችግር፡፡

8. ስቅታ፡፡

9. ማቅለሽለሽ፡፡

10. ያለምንም ምክንያት ክብደት መቀነስ፡፡

11. ደረቅ ወይም ፉጨት ያለው ሳል ወይም ዘላቂ የጉሮሮ ቁስል፡፡

12. የጆሮ ሕመም፡፡

ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ እንዲከሰት የሚያደርጉ አባባሽ ምክንያቶች

1. ብዙ ምግብ መመገብ ወይም ከተመገቡ በኃላ ወዲያውኑ ጋደም ማለት፡፡

2. ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት፡፡

3. ከባድ ምግብ ተመግበው በጀርባ መተኛት ወይም ወዲያውኑ አጎንብሰው ስራዎችን መስራት፡፡

4. በመኝታ ጊዜ ምግብ መመገብ፡፡

5. ውጥረት፡፡

6. አሲድ ያላቸው እንደ ብርቱካንና ሎሚ ፍራፍሬዎችን መመገብ፣ከዚህ በተጨማሪ ቲማቲም፣ቸኮሌት፣ነጭና ቀይ ሽንኩርት ወይም ቅመም ወይም ቅባት ያላቸውን ምግቦች መመገብ፡፡

7. የአልኮል፣የለስላሳና ካፊን ያለባቸው ቡናና ሻይ ምግብዎችን መመገብ፡፡

8. ሲጋራ ማጨስ ፡፡

9. ነፍሰጡር መሆን፡፡

10. አንዳንድ መድኃኒቶች እንደ አስፕሪን፣አይቢፕሮፍን፣አንዳንድ የጡንቻ ማፍታቻ ወይም የደም ግፊት ሕክምና መድኃኒቶችን መውሰድ፡፡



መፍትሔ



1. ቅመም የገባበትና ማጣፈጫ ያለበትን ወይም የተጠበሰ ምግብ አይብሉ፡፡

2. አልኮል መጠጦችን ያስወግዱ፡፡

3. ወተት፣ክሬም፣ቅቤ ይመገቡ፡፡

4. ሙዝ፣ማንጎ፣ሐብሐብና ቴምር የዘውትሩ፡፡

5. ምግብዎን ቶሎ ቶሎ አይመገቡ፡፡ በደንብ አኝከው ይዋጡ፡፡

6. በቀን ቢያንስ 8 ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡

7. ጣፋጭ ፣ቆምጣጣና ከፊኖ ዱቄት የተዘጋጁ ምግብዎችን አይመገቡ፡፡

8. ጠዋት ፍራፍሬ፣ምሳ የተቀቀለ አትክልት መብላት ያሻል ከምግብ በፊት ሁል ጊዜ አንድ ኩባያ አጥሚት ይጠጡ፡፡

9. በእግር መሄድ ያዘውትሩ ፡፤

10. በተቻለ መጠን ደስተኛ ይሁኑ፡፡

11. ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ፀረ- አሲድ መድኃኒት በመግዛት በመድኃኒት ባለሙያ ምክር ይውሰዱ፡፡

መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ!
642 viewsልዑል, 03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 06:02:05 የማር ጥቅም ከህክምና አንፃር //Health Benefits of Honey

ማር ስኳር እስከተገኝበት 16ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ተፈጥሯዊ ማጣፈጫ በመሆን ያገለግል ነበር የአሰራር ሂደቱ በጣም አስደናቂ ከመሆኑም ባሻገር በብዙ ሰዎች ተወዳጅና ተመራጭ የምግብ ዓይነት ነው። በፍሩክቶስ (fructose) ይዘቱ በጣም የበለፀገ ስለሆነ ብዙ የህክምና ጥቅሞች አሉት። እነሱም እንደሚከተለው ይቀርባሉ፦

1. የካንሰርና የልብ ህመም ይከላከላል!

የተፈጥሮ ማር ፍላቮንድና አንቲ ኦክሲዳንት (Antioxidant) በውስጡ ይዟል እነዚህ ነገሮች በካንሰርና የልብ ህመም የመጠቃት እድልን ይቀንሳሉ።

2. የአንጀት መቁሰልን ይከላከላል!

ማር አንጀታችን በባክቴሪያ ሲጠቃና በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይቆስል ይከላከላል።

3. ማር ፀረ ባክቴሪያና ፀረ ፈንገስ ነው!

በኒውዝላንድ ዋይካቶ ዩኒቨርስቲ የማር ምርምር ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ፒተር ሞላን ሪፓርት እንደሚያሳየው ማር ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ አለው ምክንያቱም ንብ ማር ውስጥ ሀይድሮጂን ፐር ኦክሳይድ (hydrogen per oxide) የተባለ ኢንዛይም ትጨምርበታለች።

4. የአትሌቶችን ብቃት ይጨምራል!

በደሮ ጊዜ የሚገኙ አትሌቶች ብቃታቸውን ለመጨመር ማርን ይጠቀሙ ነበር ይህ ተግባር በአሁኑ ዘመናዊ አትሌቲክስ የተረጋገጠ ሲሆን የግላይኮጂን መጠን በማመዛዘን ጉልበት እንዲያገኙ ያደርጋል።

5. ማር ሳል እና የጉሮሮ መቆጣትን ይቀንሳል!

ቀይ ማር ለሳል በጣም ጠቃሚ ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በ110 ህፃናት ላይ በተደረገው ጥናት መሰረት እኩል መጠን ያላቸው ቀይ ማር እና ዴትሮሜትሮፌን(DetromethorpHan) ተመሳሳይ የሆነ በምሽት ከሚነሳ ሳል እኩል የማስታገስ አቅም ያላቸው ሲሆን ሰላማዊ እንቅልፍ እንዲኖረን ያደርጋል።

6. አምስቱ ነገሮችን ያመጣጥናል!

ማር እይታ እና የክብደት መቀነስን ያሻሽላል። ስንፈተ ወሲብን እና ቅድመ ዘር ፍሰትን ይፈውሳል እንዲሁም የሽንት መስተጓጐልን፣ የመተንፈሻ አካላት ስርዓትን፣ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽን መከላከል ይችላል።

7. ማር በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቆጣጠራል!

ማር ምንም እንኳን አነስተኛ መጠን ያለው ስኳር ቢኖረውም ሰው ሰራሽ ከሆነው ስኳር ጋር ግን ተመሳሳይ አይደለም። የፍሩክቶስና ግሉኮስ ጥሩ የደም የስኳር መጠንን ቅንጅት ይቆጣጠራል። በተጨማሪም አንዳንድ የማር አይነቶች አነስተኛ/ዝቅተኛ የስኳር መጠን ስላላቸው የደም የስኳር መጠን እንዳይዋዥቅ ያደርገዋል።

8. ማር የሰውነት ቁስለትንና ቃጠሎን ይፈውሳል!

ማርን በውጨኛው የሰውነት ክፍላችን ላይ ከሲልቨር ሰልፋዲያዚን(Silver Sulfadiazine) አብረን መጠቀም ፍቱን መድሀኒት ነው። በማር ውስጥ ያሉት ቀላል ስኳሮችና የፀረ ባክቴሪያ ባህሪው ቁስል ቶሎ እንዲድን ያደርገዋል።

9. ስነ ህይወታዊ ባህረ!

አንዳንድ የማር አይነቶች የተለመድ የማይጓድ ባክቴሪያዎችን ይዘዋል እነሱም 6 የሚሆኑ የላክቶ ባሲላይ ዝርያዎችና 4 የቢፊዶ ባክቴሪያ ናቸው። በመሆኑም ማር ዘርፈ ብዙ የሆነ ህመምን የመፈወስ ጥበብ እና ባህሪያት አካቷል።

10. ለቆዳ ውበት!

የማር የፀረ ባክቴሪያ በዋነኛነት ለቆዳ ተስማሚ እና ጠቃሚ ነው። ከሌሎች ጋርም በመሆን ቆዳን የማለስለስና የማርጠብ ከፍተኛ አቅም አለው።

ትኩረት የሚሹ የማር መልዕክቶች

ጠቆር ያለ ጠይም ማር አንቲ ኦክሲዳንት ባህሪ አለው
ከአንድ አፀዋት ብቻ የሚሰራ ማር አነስተኛ የግላይሴሚክ ኢንዴክስ (Glycemic Index) አላቸው።

በመጨረኛም

እርስዎ የኢንሱሊን መቆጣጠሪያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት መድሀኒት የሚወስድ ከሆነ፣ ከመጠን ያለፈ የኮሌስትሮል መጠን በሰውነትዎ ካለ፣ የስኳር በሽተኛ ከሆኑና ከአቅም በላይ ውፍረት ከኖረብዎትጣፋጭ ነገሮችን ማለትም ማር እና ስኳር የመሰሉ ነገሮችን አብዝቶ ከመውሰድ ራስዎን ይቆጥቡ።

ስለሆነም የማርን ጠቀሜታ በአግባቡ ለማጣጣም ንጽህናው የተጠበቀና ተፈጥሮአዊ ማርን ብቻ በመጠቀም በማር ውስጥ የሚገኝውን የቫይታሚን፣ ኢንዛይምና ሌሎች ንጥረ ነገሮችና ሚነራሎችን ማግኝት ይችላሉ።
539 viewsልዑል, 03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 20:23:30
518 viewsሠው መሆን, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:46:24 ፎሮፎር | Seborrheic dermatitis

ፎሮፎር ምንድነው?

ፎሮፎር እየተመላለሰ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፍ የቆዳ ህመም አይነት ነው። ፎሮፎር በባህሪው ጠንካራ ያልሆነ ብዙም ምልክት የሌለው እና ትንንሽ ብናኞች ያሉት ሊሆን ይችላል፤ይህ የተለመደው አይነት ፎሮፎር ሲሆን ዳንድረፍ (dandruff) በመባል ይታወቃል።

በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የሚባለው የፎረፎር አይነት አብዛኛውን የራስ ቆዳችንን እንዲሁም ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን ላይ ጭምር ሊከሰት ይችላል፤ ቅርፊቶቹም ወፍራም እና ከራስ ቆዳችን ጋር የተጣበቁ ሊሆኑ ይችላሉ

ፎሮፎር ምን አይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል?

- ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ አመት ባሉ ህጻናት እና ከጉርምስና እድሜ በላይ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ይከሰታል
- አብዛኞቹ ፎሮፎር የሚኖርባቸው ግለሰቦች ሌላ ተጓዳኝ ህመም አይኖራቸውም አንዳንድ ጊዜ ግን ከHIV ፣ Parkinson ፣ የሚጥል ህመም (Epilepsy) ፣ ጭንቀት ገር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል

ፎሮፎር መንስኤው ምንድነው?

-የፎሮፎር መንስኤ በትክክል ይሄ ነው ተብሎ መናገር ባይቻልም ከቆዳችን ጋር ተስማምተው በሚኖሩ (normal flora) የፈንገስ አይነት (Malassezia) ምክንያት ይከሰታል ተብሎ ይታሰባል

-ፎሮፎር ወዝ አመንጪ እጢዎች (Sebaceous glands) ተከማችተው በሚገኙበት የአካል ክፍሎቻችን (የራስ ቆዳ ፣ ፊት፣ ደረት አካባቢ፣ የላይኛው የጀርባችን ክፍል ፣ የውጭኛው የጆሮ ክፍል ፣ ብብት ፣ ጡት ስር ፣ በላይኛው የጭን ክፍል እና ብልት መሀከል በሚገኘው ቦታ) ላይ ይከሰታል

ፎሮፎር እንዴት ይታከማል ?

- መድሀኒትነት ያላቸው መታጠቢያ ሻምፖዎችን (ketoconazole 2%, Selenium sulfied, Ciclopirox , Zinc pyrithione) በመጠቀም ፎሮፎርን መቆጣጠር ይቻላል።
- ሻምፖውን ተቀብተን ከ5-10 ደቂቃ አቆይተን መታጠብ ይህንንም በሳምንት ከ 2-3 ጊዜ መደጋገም ያስፈልጋል
- ከዚህ በተጨማሪ የማሳከክ ስሜት ካለው፣ጠንካራ የሚባለው የፎሮፎር አይነት ከሆነ፣ከራስ ቆዳችን ውጪ ከተከሰተ፣ተጓዳኝ ህመሞች ካሉ እንዲሁም ህጻናት ላይ ከተከሰተ የቆዳ ሐኪም በሚያዘው መሰረት ተጨማሪ መድሀኒቶች ያስፈልጋሉ።

ፎሮፎር ለምን ይመላለሳል?

መንስኤው በትክክል ስለማይታወቅ እና ምክንያት ነው ተብሎ የሚታሰበው የፈንገስ አይነት ከቆዳችን ጋር ተስማምቶ የሚኖር በመሆኑ ፎሮፎርን በህክምና ማዳን አይቻልም(not curable) ለዚህም ነው የሚመላለሰው ፤ ነገር ግን ምልክቶቹን መቆጣጠር እና የሚመላለስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል

ፎሮፎር እንዳይመላለስብን ምን እናድርግ?

ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ምልክቶቹ እስኪጠፉ በሻምፖ መታጠብ ያስፈልጋል(የቆዳ ሐኪሙ ተጨማሪ መድሀኒቶችን ሊያዝ ይችላል)፤ ምልክቶቹ ከጠፉ በኋላ ሻምፖውን በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ መጠቀም ፎሮፎር እንዳይመላለስ ይረዳል

ፎሮፎር ፀጉር እንዲነቃቀል ያደርጋል?

በፎሮፎር ምክንያት የፀጉር መነቃቀል የተለመደ አይደለም ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የማሳከክ ስሜት ካለ ጊዜያዊ የሆነና ተመልሶ የሚተካ የፀጉር መነቃቀል ሊያስከትል ይችላል

በመጨረሻም የቆዳ ሐኪም ሳያማክሩ መድሀኒቶችን ባለመጠቀም ቆዳዎን ከተጨማሪ ጉዳት ይጠብቁ!!

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

via: HakimEthio
496 viewsልዑል, 09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:46:04 ጋዝ ለጠጣ ወተት መስጠት ጎጂ ወይስ ጠቃሚ?

ዛሬ በስራ ገበታ ከገጠመኝ ጀባ ልበላችሁ። እናትን ጨምሮ የእናት ጎረቤት የሆኑ በመደናገጥ ስሜት እየሮጡ ይመጣሉ። ምን ሆናቹ ነው ብለን ስንጠይቅ የሁለት አመት ልጅ ነጭ ጋዝ ጠጥቶ ነው አሉን። ወዲያውም ወተት እንደሰጡት ሁለት ጊዜ እንዳስመለሰው ነገሩን። እኔም ካነበብኩት ጀባ ልበላችሁ።

ሃይድሮካርቦኖች ሃይድሮጂን እና የካርቦን አተሞችን የያዙ ሰፊ የኬሚካሎች ቡድን ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ቤንዚን ፣ ኬሮሴን ፣ የመብራት ዘይትና የቤት እቃ ዘይት ሁሉም የሃይድሮካርቦን ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ፔትሮሊየም ወይም ክሩድ ዘይት በተፈጥሮ ከመሬት በታች የሚገኝ የተቀጣጣይነት ጸባይ ያለው ፈሳሽ ነው። የተገነባው ከውስብስብ የሀይድሮካርቦን እና ሌሎች ውህዶች ጥምረት ነው።ከነዚህም የተለያዩ ግልጋሎቶች መካከል ፤ እንደየተጥቃሚው ፍላጎት ፣ከምግብ ማብሰያ ኬሮሲን እስከ መኪና ቤንዚን እና የጭነት መኪና ናፍጣ እንዲሁም የአውሮፕላን ማብረሪያ ልዩ ቤንዚን ፣ የሞተር ዘይትና የፋብሪካ ማሺን ማንቀሳቀሻ ጠቀሜታው ያለው ሲሆን። በተለምዶ ከምናገኛቸው የተጣራ ነዳጅ ዘይት አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፦ጋዞሊን ፥ ዲዝል ጄት ፊዩል፥ አስፋልት እና ፔትሮ ኬሚካል

የተጣራ ዘይት ምርት ውጤቶች ወይንም ሪፋይንድ ክሩድ ኦይል መደብ ውስጥ የሚገኙት ውስጥ ፦ ጋዞሊን - ቤንዚን ፥ ሂቲንግ ኦይል - ፥ የማሞቂያ የማብሰያ ጋዝ ፥ ዲዝል - ናፍጣ ፥ ኬሮሲን - የኩራዝ ጋዝ ፥ አውቶሞቢል ሉብሪኬቲንግ ኦይል - የመኪና ሞተር ዘይት ፥ፕሮፔይን - ቡቴን ጋዝ ፥ ፔትሮኬሚካል - ከዘይት የሚገኙና ክተለያዩ የዘይት ዓይነቶርች ጋር ለመቀመሚያና መደባለቂያ የሚያስችሉ የዘይት ክፍሎች ፥ አስፋልት - የመንገድ መስሪያ ሬንጅ

በአሜሪካ ውስጥ በየአመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑት መመረዞች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከስድስት አመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የሚከሰት ሲሆን፡፡ ከእነዚህ መርዛማዎች ውስጥ ከ55,000 በላይ የሚሆኑት ትናንሽ ልጆች ሃይድሮካርቦኖችን መዋጥ ያካትታሉ ፡፡

አንድ ሰው በአጋጣሚ የሃይድሮካርቦን ምርትን ከጠጣ እና ወደ ሳንባ ውስጥ ከገባ የመተንፈስ ችግር ሊፈጠር ይችላል፡፡ ከከባድ ጉዳት አለፍ ካለም እስከ ሞት አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሃይድሮካርቦኖች ዘይት ፈሳሾች ናቸው፡፡ ዘይት ያለው ፈሳሽ ወደ ሳንባ ውስጥ ካልገባ በስተቀር ብዙዎች ጎጂ አይደሉም፡፡

ሃይድሮካርቦን ወደ ሳንባ ሲገባ ምልክቶቹ በተለምዶ እንደ ሳል እና / ወይም የትንፋሽ እጥረት ናቸው፡፡ ሃይድሮካርቦን ወደ ወደ ሆድ ሲገባ ብዙውን ጊዜ ከማስገሳት እስከ ተቅማጥ ማምጣት እንዲሁም የጨጓራ ግድጊዳ መላጥ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሆኖም ወደ ሳንባዎች ውስጥ ከገባ የሳንባ ምች የመሰለ ሁኔታ ሊያስከትል ይችላል- የማይመለስ ፣ ቋሚ የሳንባ ጉዳት ፣ አልፎ ተርፎም ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡

አንዳንድ ሃይድሮካርቦኖች እራስ መሳት ፣ እራስ ስቶ መንቀጥቀጥ ፣ የተዛባ የልብ ምት ወይም በኩላሊት ወይም በጉበት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ጨምሮ ሌሎች ጉዳቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ ፡፡ አደገኛ ሃይድሮካርቦኖችን የያዙ ምርቶች ምሳሌዎች በቀለሞች እና በደረቅ ጽዳት እና በቤት ውስጥ ማጽዳት ኬሚካሎች ውስጥ የሚያገለግሉ አንዳንድ ፈሳሾችን ያካትታሉ፡፡

ብዙ የሃይድሮካርቦን ምርቶች ልጅን የሚቋቋም ማሸጊያ የላቸውም፡፡ ይህ ልጆች ሊጠጧቸው የሚችሉትን አደጋ ከፍ ያደርገዋል። እ.ኤ.አ. በ2002 የዩኤስ የሸማቾች ምርት ደህንነት ኮሚሽን (ሲፒሲሲ) አሥር በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ሃይድሮካርቦኖችን በያዙ ምርቶች ላይ ሕፃናትን የማይቋቋሙ ማሸጊያዎች እንዲቀመጡ አፀደቀ ፡፡ አዲስ የማሸጊያ መስፈርቶች ኩባንያዎች አሥራ ሁለት ወራትን ማሸጊያቸውን እንዲለውጡ ያስችላቸዋል ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ምርቶች ያለ ልጅ-ተከላካይ እሽግ በቤታችን ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ሃይድሮካርቦን የያዙ ምርቶች አንዳንድ ምሳሌዎች- ይህ የሃይድሮካርቦን ምርቶች በከፊል ዝርዝር ነው።

መዋቢያዎች - የሕፃን ፣ የፀጉር እና የመታጠቢያ ዘይቶች; የፀሐይ መከላከያ; የጥፍር ኢሜል ማድረቂያዎች እና የመዋቢያ ማስወገጃዎች።

የጽዳት ምርቶች - ማጽጃዎች (ለምሳሌ-የእንጨት ዘይት ፣ ብረት ፣ ማጣበቂያ እና ጥድ) ፣ የቦታ ማስወገጃ እና የፈሳሽ የቤት ውስጥ እቃዎች ፡፡
አውቶሞቲቭ - ቤንዚን ፣ ኬሮሴን ፣ ቤንዚን ተጨማሪዎች ፣ የነዳጅ መርፌ ማጽጃዎች እና የካርበሬተር ማጽጃዎች፡፡

በምልክት ህመምተኛው ውስጥ የሃይድሮካርቦን መጋለጥ በተለምዶ ሶስት መንገዶች ይከሰታል፡፡ በመጀመሪያ ፣ ሳያስበው የቤት ውስጥ ምርቶችን በልጆች መመገብ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ፣ የቆዳ ወይም እስትንፋስ የሙያ መጋለጥ፡፡ በመጨረሻም ፣ በጉርምስና ዕድሜዎች እና ጎልማሶች ሆን ተብሎ የሃይድሮካርቦኖችን ለመዝነኛነት በሚጠቀሙ ጊዜ፡፡

ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብዎት?
- ማስታወክን አያስገድዱ.
- ለተጠቂው ወተት አይስጡ ምክንያቱም በሚያስመልስበት ጊዜ ተጨማሪ ሃይድሮካርቦን ወደ ሳንባ ገብቶ የከፋ ጉዳት ስለሚያስከትል እራሱን ለሳተ ተጎጂ ምንም ፈሳሽ በአፋ አይስጡ ፡፡
- ሁኔታውን እራስዎ ለማስተካከል አይሞክሩ ፡፡ መጀመሪያ ሁል ጊዜ ለእርዳታ ይደውሉ ወይም ወደ እክምና ተቋም ይውሰዱ፡፡

የሃይድሮካርቦኖች መመረዝ ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች

ልጆችን ገና በልጅነታቸው ስለ መርዝ ያስተምሯቸው፡፡
ምርቶችን በምግብ ወይም በመጠጥ መያዣዎች ውስጥ ሳይሆን በመነሻ መያዣዎች ውስጥ ያቆዩ፡፡ (እንደ ቤንዚን እና የመብራት ዘይቶች ያሉ ምርቶች በጋራጅ ወይም በክምችት ስፍራዎች ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ መያዣዎች ውጭ ባሉ ጠርሙሶች ውስጥ በብዛት ይገኛሉ)

ከተጠቀሙ በኋላ ወዲያውኑ ምርቶችን ያስቀምጡ፡፡
የፅዳት ሰራተኞችን ፣ ቀለሞችን ፣ ፀረ-ተባዮችን እና ሌሎች አደገኛ ምርቶችን ከህፃናት በማይደርሱበት እና በተዘጋ ካቢኔ ውስጥ ያከማቹ፡፡

የመርዝ መቆጣጠሪያ ማዕከል ቁጥር በስልኩ ላይ ወይም በአጠገብ ይለጥፉ፡፡

ምልክቶች እስኪከሰቱ ድረስ አይጠብቁ፡፡ ጥሩ መመሪያ; አንድ ሰው አንድ ነገር ከጠጣ እና መርዛማ መሆኑን እርግጠኛ ካልሆኑ; ወዲያውኑ ወደ መርዝ ማእከል ይደውሉ ወይም ህክምና ማህከል ይዉሰዱ።

አንባቢዎቼ መልዕክቴም ወደ ብዙዎች ትደርስ ዘንድ … እንድታቋድሷት (ሼር እና ላይክ እንድታደርጓት) በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ሐኪም
437 viewsልዑል, 09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:30:05
529 viewsልዑል, 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:30:01 ዛሬ July 6 ዓለምአቀፍ የመሳሳም ቀን ነው[International Kissing Day]
...

የመሳሳም የጤና ጥቅሞች

በቅንነት ሼር #ያድርጉት
ለዛሬ የመሳሳም የጤና ጥቅሞችን ይዘን ቀርበናል ነገር ግን ከትክክለኛ አጋር ፣በትክክለኛው ቦታና ጊዜ መሆኑ አይዘንጋ! ሁሉም ነገር ጥቅም እንዳለው ሁሉ ጉዳትም አለውና፡፡
#1.መሳሳም የልብ ትርታንና የደም ዝውውርን በማፍጠን ለልብ ዘብ ይቆማል፤ የደም ግፊትና የኮሌስትሮል በሽታዎችን ይከላከላል፡፡

#2.በመሳሳም ሰዓት የፍቅር ስሜትን ለማርካት 30 የፊት ጡንቻ ሰራዊቶች ይዘምታሉ፤ በዚህ እግረ መንገዱን የፊት መጨማደድን ወደ ወጣትነት ይቀይራል፡፡

#3.መሳሳም ጭንቀትን በማስወገድ አንጎላችን ላይ ሠላም ያሠፍናል፤ በዚህም ጊዜ ኬሚካሎች (neurotransmitters) እና ኦክሲቶክሲን ሆርሞን በብዛት ይመረታሉ፤ እነዚ ኬሚካሎች የጭንቀት መከላከያ ሐይል ናቸው፡፡

#4.በተደጋጋሚ መሣሣም በሆድ፣ በፊኛና በደም ብክለት የመሠቃየት ችግርን ይሸኛል፡፡

#5.በጥልቅ ስሜት መሣሣም ከልክ ያለፈ ውፍረት ለመቀነስም ያግዛል፤ 1ደቂቃ ስንሳሳም 26ካሎሪ የመቀነስ ዕድል አለ፡፡

#6.ሰዎች በሚሳሳሙበት ወቅት የምራቅ ፍሰት ይጨምራል፤ ምራቅ ደግሞ ባክቴሪያዎችን, ቫይረሶችን እና ፈንገሶችን የሚዋጉ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል፡፡ ስለሆነም ጥልቅ መሳም የአፍ፣ የጥርስ እና የድድ ጤንነትን ይጠብቃል።

#7.ስትሳሳም/ሚ እና ስትሳም/ሚ የመወደድ፣ የመደነቅና የመፈለግ ስሜት ይፈጥራል፤ ይህ ደግሞ ሞራልና በራስ የመተማመን ስሜትን ይጨምራል፡፡

#8.ጧት ጧት ባለቤታቸውን ስመው የሚሠናበቱ ወንዶች/ሴቶች ስመው ከማይሠናበቱት በ5 ዓመት ዕድሚያቸው ይጨምራል፡፡

#9.ፍቅር በርካታ የጤና ጥቅሞች ምንጭ ነው፡መሳሳም ደግሞ የጤናማና የዘላቂ ፍቅር መሠረት ነው፡፡
...
መሳሳም እነዚህን ሁሉ የጤና ጥቅሞች ቢኖሩትም አንዱ የግንኙነቱ ባለደረባ በህመም ከተጠቃ የህመሙ መተላለፊያ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን ሁኔታዎች መተግበር ከመሳሳም ጋር ተያይዘው ከሚመጡ ህመሞች ይጠብቆታል፡፡

እርስዎ ወይም ሌላው ሰው ሲታመሙ ከመሳሳም ይቆጠቡ።
እርስዎ ወይም እነሱ ንቁ የሆነ ጉንፋን፣ ኪንታሮት ወይም ቁስሎች በከንፈር አካባቢ ወይም በአፍ አካባቢ ሲያዙ ማንንም ሰው ከንፈር ከመሳም ይቆጠቡ።
ጥሩ የአፍ ንጽህናን ይጠብቁ፡፡
ጉንፋን ካለብዎ ወደ ውጪ ይሳሉ እና ያስነጥሱ።
ስለ ክትባቶች ዶክተርዎን ያነጋግሩ. እንደ ኩፍኝ፣ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ፣ ሜኒንጎኮካል ኢንፌክሽን ያሉ አንዳንድ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ክትባቶች አሉ።

በነገራችን ላይ 2 የሚዋደዱ ሰዎች እየተሳሳሙ የቆዩበት የዓለማችን ረዥም ጊዜ ተብሎ በጊነስ የተመዘገበው 30ሰዓት ከ59ደቂቃ ነው፡፡

[በዶክተር አለ]
550 viewsልዑል, 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 02:06:17
940 viewsልዑል, 23:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ