Get Mystery Box with random crypto!

ለምፅ | Vitiligo ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት (acquired) የቆዳ ቀለም ባለመመረ | ጤና ዓዳም- Tena Adam

ለምፅ | Vitiligo

ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት (acquired) የቆዳ ቀለም ባለመመረቱ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው

ለምፅ በንክኪ አይተላለፍም

ለምፅ ከህጻናት ጀምሮ በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ሊታይ ይችላል

ለምፅ በምን ምክንያት ይከሰታል?

ምክንያቱ ይሄ ነው ተብሎ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ፤ የተለያዩ መላምቶች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፤ከነዚህም መካከል "የሰውነታችን በሽታ የመከላከያ ስርአት (immunity system) የራሳችንን የቆዳ ቀለም አምራች ህዋሳትን(melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው" የሚለው መላምት በይበልጥ ተቀባይነት አለው።

በዚህም ምክንያት ለምጽ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚከሰቱ ሌሎች ህመሞች (autoimmune diseases) ጋር ተያያዥነት አለው ተብሎ ይታሰባል ፤ ለምሳሌ ከየስኳር ህመም፣ የእንቅርት ህመም (autoimmune type)፣ ላሽ (alopecia areata)....

ለምፅ ከጭንቀት (emotional stress)፣ ከእርግዝና፣ ከአደጋ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል

የለምፅ ምልክቶች

ለምጽ ያለበት ቦታ ወደ ነጭነት የሚያደላ ቀለም ሲኖረው ከዚህ ውጪ ማሳከክ ወይም ቦታው ላይ ቅርፍቶች መኖር የለምጽ ባህሪ አደለም

በማንኛውም የቆዳችን ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

ለምፅ አንድ ቦታ ላይ ብቻ (focal)፣ በግራ ወይም በቀኝ የሰውነት ክፍል ብቻ (segmental) ወይም አብዛኛው የቆዳችኝ ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

የለምፅ ህክምና

የህክምናውን አይነት የሚወስኑ ሁኔታዎች ፦
የህመሙ ጥንካሬ (severity)
እየተስፋፋ መሆኑ ወይም ባለበት መቆሙ
የህክምናው በቀላሉ መገኘት እና የህመምተኛው የመክፈል አቅም...

የህክምና አይነቶች
የሚዋጥ
የሚቀባ
Phototherapy (ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ ብርሀንን በመጠቀም የሚሰጥ ህክምና)
Excimer laser
የቀዶ-ጥገና (surgery) ህክምና

የማንጣት ህክምና (depigmentation)
አብዛኛው የሰውነት ክፍል በለምፅ ከተጠቃ እና ለማከም አስቸጋሪ ከሆነ ጤነኛውን የቆዳ ክፍል በማንጣት የማመሳሰል ሂደት ነው (Michael Jackson ይህ ህክምና ተደርጎለታል)

ስለህክምናው ሂደት ማወቅ ያለብን

ህክምናውን ከጀመርን በኋላ የህክምናውን ውጤት ለማየት ከ 2-3 ወር ሊፈጅ ይችላል

ጠቅላላ ህክምናው ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ያለማቋረጥ መከታተል ያስፈልጋል

ህክምናው ከተጠናቀቀ በኋላ ለምፁ እንደገና ሊመለስ ይችላል

ከንፈር ላይ፣ጣት ላይ እንዲሁም ከቆዳው በተጨማሪ ፀጉርም አብሮ ነጭ ከሆነ የመዳን እድሉ ዝቅተኛ ነው

ለምፅን ባንታከምስ?

ለምፅ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ጫና ያሳድራል
እየሰፋ ሊሄድ ይችላል
ቆዳችን በፀሐይ ጨረር እንዲጠቃ ሊያረግ ይችላል (ፀሐይ መከላከያ/sunscreen መጠቀም ያስፈልጋል)

በመጨረሻም

ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት