Get Mystery Box with random crypto!

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በምግብ መከላከል፣ መቆጣጠርና ማከም (Food as medicine to p | ጤና ዓዳም- Tena Adam

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በምግብ መከላከል፣ መቆጣጠርና ማከም (Food as medicine to prevent and reverse chronic diseases)

በአለም አቀፍ ደረጃ ምንም እንኳን የመድኀኒት ህክምና እየዘመነና እየተመደበለት ያለው የገንዘብ መጠን ቢጨምርም በመድሀኒት ህክምና ብቻ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ማከም ከባድ ፈተና ውስጥ ወድቋል ወይም የሚጠበቀው ያክል ውጤታማ ሊሆን አልቻለም
ይህንን የሚያረጋግጥልን በአለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከሚከሰት 55 ሚሊዮን ሞት ውስጥ 70% የሚሆነው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት ነው ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ በልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች (CVD) ምክንያት የሚከሰት ሞት ከ 40% በላይ ሲጨምር በስኳር በሽታ ምክንያት የሚከሰት ሞት ደግሞ በ93% ጨምሯል (Physicians Association for Nutrition – PAN, 2021)

ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ውስጥ በልብ ሕመም፣ በስትሮክ እና በስኳር በሽታ ከሚሞቱት ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ጤነኛ ባልሆነ ምግብ ወይም የምግብ ስርአት ምክንያት ነው

በአንጻሩ ደግሞ ጤነኛ ምግብ (የምግብ ስርአትን) መከተል እንደ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት መጨመር ፣ የልብ ህመም ፣ ካንሰር ፣ ስትሮክንና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል፣ መቆጣጠር ፣ ማከም ወይም ህክምናውን ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ ድርሻ እንዳላው ጥናቶች አመልክተዋል

በ2018 LIFE LINE SCREENING-How Healthy Eating Prevents Disease በሚለው ሪፓርታቸው እንዳመለከቱት ከሆነ ቀለል ያሉ የአኗኗር ዘይቤን በመተግበር በተለይም ጤነኛ ምግብ (የምግብ ስርአትን) በመከተል እስከ 80% ድረስ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን የመከላከል አቅም እንዳለን አመልክተዋል

ይህንን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በምግብ የመከላከል እና የመቀልበስ አቅም the power of nutrition in disease prevention and treatment በማለት ይገልጹታል

Muluken Fekadie (Asst. Prof. of Biochemistry)

via: HakimEthio