Get Mystery Box with random crypto!

'የምትማሩት ለደመወዝ ብቻ ከሆነ ከሰላሳ ቀን በላይ አሻግራችሁ የምታዩት ራዕይ የላችሁም ማለት ነው | Ethio cyber

"የምትማሩት ለደመወዝ ብቻ ከሆነ ከሰላሳ ቀን በላይ አሻግራችሁ የምታዩት ራዕይ የላችሁም ማለት ነው።"

በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነው “ጃክ ማ” ሲሆን 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አለው ጃክ ማ እንዲህ ይላል፡-
‘’ ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!

አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው።

ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው።

ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል!

እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል።

በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰአት እስከ 12 ሰአት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13