Get Mystery Box with random crypto!

'ፓርከር ሶላር ' የተሰኘው ፕሮብ እጅግ በፍጥነት በፀሐይ ዙሪያ በመንቀሳቀስ ሁለት ሪከርዶችን አ | Ethio cyber

"ፓርከር ሶላር " የተሰኘው ፕሮብ እጅግ በፍጥነት በፀሐይ ዙሪያ በመንቀሳቀስ ሁለት ሪከርዶችን አሻሻለ።

ፕሮቡ በፀሐይ ዙሪያ እየተሽከረከር ፀሐይን እንዲያጠና ናሳ የላከው ሲሆን በፀሐይ ዙሪያ እጅግ በፍጥነት በመንቀሳቀስ ከዚህ ቀደም ሪከርዱን የያዘው በሰከንድ 165 km እየተጓዘ ነበር።

በቅርቡ ደግሞ ይሄው ፕሮብ ይሄንን ፍጥነት በማሻሻል በሰከንድ እስከ 200km ተጉዟል ይህ ማለት ከአዲስ አበባ ደብረብርሃን በሰከንድ ውስጥ ደረሶ መልስ ማድረግ ይችላል እንደማለት ነው በዚህም ምክንያት የሰው ልጆች ከፈጠሯቸው ተንቀሳቃሽ ነገሮች መካከል በፍጥነት በመንቀሳቀስ የሚስተካከለው ተንቀሳቃሽ ነገር የለም ነገረ ግን ቴክኖሎጂ እያደገ ሰለሚሄድ ይሄው ሪከርድ በቅርቡ መሻሻሉ አይቀርም የብዙዎች ግምት ነው።

ፕርቡ ሌላው አለምን ያስገረመው እና ሪከረድ ያሻሻለው በፀሐይ ዙሪያ እጅግ ተቃርቦ በመንቀሳቀስ ነው እንደሚታወቀው ፀሐይ በበጋ ወቅት ወይም በዚህ ሰአት 147,000,000km ከምድራችን እርቃ ትገኛለች ይሁን እንጂ ሙቀቷ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር ብዙዎቻችን በዚህ ሰአት ስስ ልብሶችን ለብሰን እየተንቀሳቀስን ነው ነገር ግን ይህ የናሳ ፕሮብ ከሳምንት በፊት ፀሐይን እስከ 7,000,000km ብቻ መቅረብ ችሏል በዚህ ምክንያት ፀሐይን እጅግ ተቃርቦ የተንቀሳቀስ የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ ውጤት ሁኖ በታሪክ ተመዝግቧል።

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1