Get Mystery Box with random crypto!

በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ

ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተገድሏል


በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ ሁለቱ ሲገደሉ ሌላኛዉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን ተኩስ ከፍተዋል ብሏል።

ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል ብሏል ፖሊስ፡፡

ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ታጣቂዎቹ  በመኪናቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS