Get Mystery Box with random crypto!

'ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም' ያለው የሜድስን ተማሪ ከሞት ተርፏል እምሩ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

"ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም" ያለው የሜድስን ተማሪ ከሞት ተርፏል

እምሩ ሙስጠፋ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሜዲስን ተማሪ ሲሆን በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ቤተሰቦቼን አደራ፣ እኔ ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም፣ እኔ መኖር እፈልጋለው መኖር ግን አልተፈቀደልኝም፣ ባልፈጠር ይሻለኝ ነበር ባልፈጠር እኔንም ቤተሰቤንም አላስቸግርም" በማለት ራሱን እንደሚያጠፋ ከገለፀ በኋላ በጓደኞቹ፣ በፖሊስ እና በዩኒቨርሲቲው ጥረት ራሱ ላይ ጉዳት ሳያደርስ ተይዟል። ቤተሰብ እስኪመጣ በነቀምት ከተማ ፖሊስ እንደሚቆይ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሃሰን ዩሱፍ (PHD) ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS