Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የራሱን ህይወት ማጥፋቱ ተረጋገጠ __ ባሳለፍነው ሳምንት በሞት ያ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የራሱን ህይወት ማጥፋቱ ተረጋገጠ
__

ባሳለፍነው ሳምንት በሞት ያጣነው ተወዳጀ ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን በገመድ አንቆ ህይወቱን እንዳጠፋ ኢትዮጲካሊንክ የሬዲዮ ኘሮግራም ዘገበ።

የዛሬ 6 ወር ገደማ ስኳር ህመም ያለበት ይህ ጀግና ሰው ገነን አንድ እግሩን ይቆረጣል ከዛ በኅላ ህይወት እንዳስጠላው ና ወዲህ ወዲያ ሲል ባለቤቱ እሷ መኪና እየነዳች እንደምታደርሰው ኢትዮጲካሊንክ አሳውቆ አንድ ቀን ግን ባለቤቱን ግዬን ሆቴል ስራ አለብኝ አድርሺኝ ብሏት አድርሳው ወደ ቤት ብትመለስም እሱ ግን ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ስልኩን በማጥፋት ሆቴል ይዞ ተደብቆ ትንሽ ቀናትን ቆይቷል::

ከዛ ግን ለጋዜጠኛ ሰይድ ኪያር ደውሎ ያለበትን ቦታ ነግሮት ሰይድም ወዲያው መጥቶ ስኳሩ በጣም እንደወረደና ባለቤቱ ጋር ደውሎ ስኳሩ በጣም ወርዷል ሲላት ባለቤቱም " በቃ ሚሪንዳ " ይጠጣበት ብላ እንደመለሰች ከዛ ግን ሄዳ እንኳን እንዳላየችው ታውቋል::

ብቻውን እዛ ክፍል ውስጥ የከረመው ይህ ታላቅ ሰው ገነነ ምን እንደሆነ ለምን እንደዚህ ውሳኔ እንደወሰነ ባይታወቅም ራሱን በገመድ አንቆ እንደገለ በምርምራ ታውቋል።

በጣም የሚያሳዝነው ግን ባለቤቱ ሞቱን ስትሰማ ወደ አረፈበት ሆቴል በመሄድ ለፖሊስ መናገር ና ማሳወቅ ሲገባት ሬሳውን ወደ ቤቷ አምጥታ ስታለቅስ የጎረቤት ሰዎች ለፖሊስ አመልክቺ እንጂ ብለው ሲጠይቋት ለፖሊስ ያመለከተች ሲሆን ፖሊስም እንዴትት የሞተ ሰውን አስክሬን ለፖሊስ መናገር ና ማሳወቅ ሲጋባሽ አስክሬኑን ይዘሽ ወደ መኖሪያ ቤትሽ ትሄጃለሽ ብሎ አንድ ቀን እስር ቤት አውሏት እንደነበር ኢትዮጲካሊንክ ዘግቧል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS