Get Mystery Box with random crypto!

#MoE ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን የማስፈተን ፤ ይህ ባይሆ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን የማስፈተን ፤ ይህ ባይሆን እንኳን ተማሪዎችን ወደ ማዕከል ዩኒቨርሲቲዎች በማስመጣት ፈተና ለመስጠት እያሰበ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለህ/ተ/ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ ባለፈው ዓመት ተጀምሮ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በታብሌት ለመስጠት የተጀመረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገፋንበት ነው ብለዋል።

ሂደቱ አሁን ላይ በአቅም ጉዳይ መቆሙን የገለፁት ሚኒስትሩ " ሁሉንም ሂደት ከጨረስን በኃላ ይሄ የሚጠይቀውን ወደ 1 ሚሊዮን ታብሌት ሃገር ውስጥ ለማስገባት ወደ 460 ሚሊዮን ዶላር ይጠይቃል፤ ይሄን ከቻይና መንግስት ጋር በሚደረግ ንግግር በእርዳታ ሊመጣ የሚችልበትን መንገድ በብዙ መንገድ ጠ/ሚኒስትሩም ገብተውበት እየገፋን ነው " ብለዋል።

" እሱ እንኳን ቢያቅተን በዚህ ዓመት የምንችለውን ሁሉ ሞክረን የምንወስደው እርምጃ ግን አንዱ በየትምህርት ቤቶቹ ፈተናን መፈት ትተን የሚያስወጣንን ወጪ አውጥተን ተማሪዎቹን ከየትምህርት ቤታቸው አምጥተን በየዩኒቨርሲቲ ማዕከላት ውስጥ ፈተናዎቹን እንዲወስዱ ማድረግ ነው ፤ ይሄን ነው አንዱ ልንሄድበት እያሰብን ያለነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የፈተና ስርቆት መቆም አለበት ያሉ ሲሆን " ስርቆት መቆም ያለበት ሰነፍ ተማሪን እና ጎበዝ ተማሪን ለመለየት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሞራል መሰረታችንን እየበላው በመሆኑ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም ፤ በቀጣይ አመት የሚጀመረው የመውጫ ፈተና የተገባበት አንድ ተማሪ ከታችን ያለውን አጭበርብሮ አልፎ ቢመጣ ኮሌጅም ከገባ በኃላ እንደገና ፈተና እንደሚጠብቀው አውቆ ቢያንስ ኮሌጅ ከገባ በኃላ በደንብ ተምሮ እንዲያውቅ ነው ብለዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS