Get Mystery Box with random crypto!

የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ዛሬ ለምረቃ ከበቁት የክልሉ ፖሊስ አባላት መካከል | ሰበር ዜና ETHIOPIA

የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ዛሬ ለምረቃ ከበቁት የክልሉ ፖሊስ አባላት መካከል 400 ያህሉ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ፖሊስ እንደሚቀላቀሉ ገለጹ፡፡

ርእሰ መስተዳዳሩ በአፍ ሶማሊ ቋንቋ በይፋዊ የማህበራዊ ድረገፃቸው ባጋሩት መልእክት እንደገለጹት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ጋር በመሆን በጅግጅጋ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከ2,100 በላይ አዳዲስ የፖሊስ አባላትን ዛሬ በተመረቁበት ስነ-ስርዓት ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ በዛሬው እለት ከተመረቁት የክልሉ ፖሊስ አባላት መካከል 400 የሚሆኑት የመዲናዋን ፀጥታ ለማሻሻል ወደ ጅግጅጋ ፖሊስ ሀይል በቀጥታ የሚቀላቀሉ መሆኑን ጠቁመው ሌሎች የከተማ አስተዳደሮችም ልክ እንደ ጅግጂጋ ከተማ አስተዳደር የከተሞቻቸውን ፀጥታ ለማጠናከር የራሳቸውን ምልምል አባላት በቅርቡ ወደ ፖሊስ ማሰልጠኛው እንደሚልኩም ጠቁመዋል፡፡

በዛሬው እለት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ለ6 ወራት በሶማሌ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ስልጠና ሲሰጥ የነበረውን የፌደራልና የክልል ጥምር ፖሊስ ሰራዊት የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ፣ የኢፌዲሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደምመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የሶማሌ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙበሽር ዱበድ፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ አሊ፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ እንዲሁም ሌሎች እንግዶች በተገኙበት መመረቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡