Get Mystery Box with random crypto!

የሶማሊያው አዲሱ ፕሬዝዳንት ወደ ኤርትራ ማቅናት ህወሃት ደጋፊዎች ስጋት መፍጠሩ እየተገለጸ ይገኛል | ሰበር ዜና ETHIOPIA

የሶማሊያው አዲሱ ፕሬዝዳንት ወደ ኤርትራ ማቅናት ህወሃት ደጋፊዎች ስጋት መፍጠሩ እየተገለጸ ይገኛል።


ከዚህን በፊት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው አጋርነት ስጋት ውስጥ ከቶቸው የነበሩ የህወሃት ሰዎች የፋርማጆ መሸነፍ ትልቅ ለውጥ ያመጣልናል ብለው ተስፋ አደርገው ነበር። ይሁን እንጂ አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በተመረጡ ማግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተቀራርበው መስራት እንደሚፈልጉ መልዕክተኛ መላካቸው፤ የበዓለ ስሜታቸው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ቁጥር አንድ እንግዳ አድርገው መጋበዛቸው፤ በትላንትናው እለት ደግሞ ወደ ኤርትራ በመሄድ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ለህወሃት ሰዎች ትልቅ ስጋት ፈጥሯል። በዚህም ሳያበቃ አልቡርሃን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ጦርነት መግባት ጣጣው ለከፋ ነዉ ስለዚህ አሸማግሉኝ ብለው ለኬንያ አማላጅ ሲልኩ መቆየታቸው ሲገለጽ ነበር። ይህንኑ በሚያጠናክር መልኩ በኢጋደ ስብሰባ ወቅት በአልቡርሃን ጥያቄ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ያዝ እንግዲህ ጁንታው አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ከዚህ በላይ ምን ምስክር ሊሆን ይችላል?