Get Mystery Box with random crypto!

❤ ዘ🌌ART 😂

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopsak — ❤ ዘ🌌ART 😂
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopsak — ❤ ዘ🌌ART 😂
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopsak
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 625
የሰርጥ መግለጫ

✍ግጥሞችን ➠
❤️የፍቅር መልስ✳

📚ጠቃሚ ምክሮች ➳

💌የፍቅር ወግ💥
🌏🎼 ሙዚቃዎች◀
የሚያገኙበት ቻናል፡፡
👍 Join ያድርጉ
☞ፅሑፎን በመላክ ይሳተፉ
(እንማማር)
👉cretor & admin ex
@z_arter♲︎︎︎ @z_yise

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-28 15:39:17 የምትወደውን ነገር ስታደርግ እውነተኛውን ስኬት ታገኘዋለህ!!

ስኬታማ ሰው ለመሆን ብለህ ወይም ገንዘብና ዝናን ፍለጋ የማያስደስትህን ነገር አታድርግ።ስኬት የሚመጣው የሚደሰቱበትን ነገር በማድረግ ነው። ከሁሉም የሚበልጠው ስኬት ደግሞ ደስታን ማግኘት ነው ስለዚህ የምትወደውን ነገር በማድረግ ውስጥ ትልቁን ስኬት( ደስተኛ መሆንን)ታገኛለህ። ስለዚህ ምንም ነገር ማረግ ያለብህ ካስደሰተህ እና ደስታን ከሰጠህ ብቻ ነው።

#join and share
መልካም ቀን
85 viewsy҉i҉s҉a҉k҉, 12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 21:39:23 ድፍረት ማለት ያለ ፍርሀት መኖርና እየደነፉ ማውራት ማለት ሳይሆን ፣ ከሚገባው በላይ ብንፈራና ብንደነግጥም እንኳን ያሰብነውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለት ነው ።

በአስቸጋሪ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ተረጋግቶ መውጫ ቀዳዳ በመሻት መውጣት የድፍረት አንድ አካል ነው።

ድፍረት ማለት የፍርሀት አለመኖር ሳይሆን ፍርሀት ላይ የምንቀዳጀው ድል እንደሆነ ተማርኩ፤ ጀግና የሚባለው ፍርሀት የማይሰማው ሳይሆን ፍርሀትን መማረክ የቻለው ነው። — ኔልሰን ማንዴላ


Share
@ethiopsak
199 viewsy҉i҉s҉a҉k҉, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 21:30:12 . ዛሬ በአድናቆት አጅቦ የሚከተለኝ ሕዝብ ነገ ለመሰቀል ስሄድ ደግሞ - አጅቦ ይከተለኛል፡፡

ናፖሊዮን

@ethiopsak
ነገ መልካም ይሆናል !
@ethiopsak
178 viewsy҉i҉s҉a҉k҉, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 06:49:11 ጀማንጉስ እና ግሸንማሪያም ዘንዳ እንደተወለድኩኝ
ሁዳዴ ረመዳን ስፆም እንዳልዋልኩኝ
አቦ ኢንሻአላህ !
ክርስቶስ ቢነሳ አፍጥሬ ገደፍኩኝ

@ethiopsak

ብሩክዛራሙ
224 viewsy҉i҉s҉a҉k҉, 03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 06:49:10 የጋራ መኖሪያ ።

በቤተ ዘመድ ፊት ... ቃል ቢገባልሽም
እሱም ቤት አልገባም...አንቺም ቤት የለሽም
የባልሽ ንግግር ... ቅኔው ተፈታልሽ
እሰራልሻለው ... እንዳለው ሰራልሽ

@ethiopsak

በሙሉቀን ሰ•
214 viewsy҉i҉s҉a҉k҉, 03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 04:36:13 በህይወት ስትኖር… ሁሌም መርሳት የሌለብህ ነገሮች

ደስ የሚል ቀን ሁሌም የለም።
ማንም ላይ እንዳትፈርድ…እማታውቀው ነገር ይኖራልና።
እናትህን እና ወዳጆችህን እንዴት እንደምታስደስታቸው ሁሌም አስብ።
በምታየው መጥፎ ነገር እንዳትሸነፍ።
እራስህን ከነገሮች በላይ አድርግ።
እምትችለውን አድርግ… እማትችለውን ደሞ ለ እግዚአብሔር ተወው።

@ethiopsak
255 viewsYIƧΛK, 01:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 21:12:39
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
መልካም የትንሣኤ በዓል
229 viewsYIƧΛK, 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 01:13:19
376 views¥őM , 22:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 19:55:30 # ግጥም ,,,,,,,,,,,,~=>

አንተ የማን ልጅ ነህ - ከየት ነህ አትበሉኝ ፡
ብሔሬን ተውና ችግሬን ጠይቁኝ ።
አማራ ይመስላል - ለምን ትላላችሁ ?
ኦሮሞ ይመስላል - ለምን ትላላችሁ ?
እርቃኔን ቁጭ ብዬ - በርዶኝ እያያችሁ
ከደቡብ ነህ እንዴ ? ለምን ትላላችሁ ?
ትግራዋይ ነው መሰል - ለምን ትላላችሁ ?
እህል ሆዴ ናፍቆ - ተርቤ እያያችሁ ።
ከጋምቤላ ነህ ወይ ፤ ለምን ትላላችሁ ?
አፋርም ይመስላል ፥ ለምን ትላላችሁ ?
መናገር አቅቶኝ - ታምሜ እያያችሁ ።
ሱማሌ ነህ መሰል - አፍህ ይጣፍጣል
ቆለኛ መሆንህ - በደንብ ያስታውቃል
ይህ የአደሬ ልጅ ነው ፤ ከጀጎል የወጣ ፥
ወይም የቤኒሻንጉል - ከአሶሳ የመጣ ፥
በማለት ጎሣዬን - ምን አሰቆጠራችሁ ?
ተስፋዬ ጨላልሞ - ተክዤ እያያችሁ ።
ሆድ ብሶኛል እና ፥ ይብስ አታስብሱኝ ፤
የሚዲያ አስቤዛ - ፍጆታ አታድርጉኝ ።
ስለዚህም ማን ነህ ? ከየት ነህ ? አትበሉኝ ፤
ብሔሬን ተውና ፥ ችግሬን ጠይቁኝ ። .....
በኢትዩጲያዊነቱ የሚያምን ብቻ #
@ethiopsak
571 viewsy҉i҉s҉a҉k҉, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 19:51:42 ወንድ አውቃለሁ #kuma

ወንድ አውቃለሁ
ለሴት ክብር ግድ የሌለው
ፍቅር መውደድ የማይገባው
ለሴት ገላ ሲስገበገብ
ፍቅርን ክዶ ለስሜቱ ሲራብ
አዎን ፍቀሬ ወንድ አውቃለሁ
የወንድ ትንሽ
በፍቅር ስም ሴትን ሲዋሽ
ወረድ ብሎ ከቀሚሷ
ክብሯን ሲወስድ ከነነፍሷ

አዎን ውዱ ወንድ አውቃለሁ
ባንዷ ሴት ላይ ተረማምዶ
ለስሜቱ ከእሳት ነዶ
ከሌላኛዋ ሴት የሚሄድ
አውቃለሁኝ ከሀዲ ወንድ,,,
ግን ደግሞ

ወንድ አውቃለሁ
ለፍቅር ቃሉ ያደረ
በሴት ክብር የከበረ

ለእምነት ቃሉ የሚኖር ሰው
ድንቅ የሆነ ወንድ አውቃለሁ
ስሜት ሳይሆን ፍቅር ያለው
እምነት ፅናት የተሰጠው
እንዳንተ አይነት
መልካሙን ወንድ ታድያለው

@ethiopsak
487 viewsy҉i҉s҉a҉k҉, 16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ