Get Mystery Box with random crypto!

የሌለዉን እንዳለ ማስመሰል ይደክምሃል! ህይወት በነብርና በሚዳቆ መካከል እንዳለዉ እልህ አስጨራሽ | ❤ ዘ🌌ART 😂

የሌለዉን እንዳለ ማስመሰል ይደክምሃል!

ህይወት በነብርና በሚዳቆ መካከል እንዳለዉ እልህ አስጨራሽ ሩጫ ናት፡፡ ብዙ ጊዜ ሚዳቆ ሮጣ ታመልጣለች፡፡ ነብር ደርሶ የሚይዛት ከስንት አንዴ ነዉ..

ይሄ ለምን እንደሆነ ታዉቃለህ? ነብር የሚሮጠዉ ‘ለአንድ ምሳ!’ ሚዳቆ ግን ‘ለዉድ ህይወቷ’ ስለዚህ አላማ ከጊዜያዊ ፍላጎት እንደሚበልጥ ትረዳለህ፡፡

የሚዳቆ አላማ ሕይወቷን ማትረፍና ሌላ ቀንን ማየት ሲሆን የነብር ደግሞ ‘በልቶ መዘረር’ ነዉ፡፡ ከስንት አንዴ ከበላና ከጠገባ በኋላ ሚሊየን ሚዳቆ በአፍንጫዉ ስር ቢያልፉ ምን ገዶት!

ለመኖር እልህ ሲይዝህ ለመብላት መኖር ታቆማለህ፣ ለሻይ መጠጫ ተራራ መፈንቀል፣ የሌለዉን እንዳለ ማስመሰል ይደክምሃል...ወደ እዉነተኛዉ መንገድ የዛኔ መመለስ ትጀምራለህ፡፡ ያም ለአላማ መኖር!
@ethiopsak