Get Mystery Box with random crypto!

#ጠቢብ_ችግሮች_አይኖሩትም! “ለዚህም ነው ጠቢብ ሰው ከጠበቀው ውጪ አይገጥመውም የምንለው” | ❤ ዘ🌌ART 😂

#ጠቢብ_ችግሮች_አይኖሩትም!

“ለዚህም ነው ጠቢብ ሰው ከጠበቀው ውጪ አይገጥመውም የምንለው”
#ሴኔካ

ባለቅኔው ሄሶድ እንዲህ ይላል፤ “ዝምተኛ ምላስ ታላቅ ሃብት ናት” ሮበርት ግሪን የኃይል ህጎች ካላቸው መሃል፡- ከሚያስፈልገው ባነሰ ተናገር የሚል ይገኝበታል።

የምናወራው ማውራታችን እንደሚጠቅመን እያሰብን ነው፤ ሆኖም ሁኔታዎችን ያብስብናል። ወዳጆቻችን ካበሳጩን ልክ ልካቸውን ለመንገር ይቃጣናል። ምናልባትም እነሱ የሚፈልጉት እንድንሰማቸው ብቻ ይሆናል። በሌላ ሁኔታዎች ዓለም ችግሮችን ወደ እኛ ለመጫን ትሞክራለች፤ ሆኖም ችግሩን ለማስወገድ የምንሄድበት መንገድ በራሱ ሌላ ችግሮችን ይጭንብናል።

እናም ዛሬ የችግሩ አካል ትሆናለህ ወይስ የመፍትሄው? የዓለምን ጥበብ ትሰማለህ ወይስ በጫጫታ ውስጥ ትዋጣለህ?



ነገ መልካም ይሆናል !
https://t.me/ethiopsak
@z_yise