Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Entrepreneurs ኢንተርፕርነር

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopreneure — Ethiopian Entrepreneurs ኢንተርፕርነር E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopreneure — Ethiopian Entrepreneurs ኢንተርፕርነር
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopreneure
ምድቦች: ንግድ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.62K
የሰርጥ መግለጫ

Contact @mayirameteb

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-26 09:28:20 በኮርያ መንግስት ድጋፍ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማበልፀጊያ ማዕከል ሊቋቋም ነው።
============================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የኮርያ አለም አቀፍ ኮኦፐሬሽን ኤጀንሲ በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታና ድጋፍ ዙሪያ መክረዋል።

ማዕከሉ በኮርያ መንግስት ድጋፍ በ6 መቶ ሺ ዶላር ወጪ በአይ ሲ ቲ ፓርክ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን የሚያበለፅጉበትና ወደ ንግድ የሚለውጡበት ነው።

በኮርያ አለም አቀፍ ኮኦፐሬሽን ኤጀንሲ ድጋፍ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እስከ 2025 የሚቆይ የ10 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተተገበረ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) በዚህ ፕሮጀክት እየተደገፉ ያሉና ተወዳድረው ለተመረጡ 10 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እስከ 5ሺ ዶላር የሚደርስ የመነሻ ገንዘብ ተሰጥቷቸው በቅርቡ ይመረቃሉ ብለዋል።

የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራ ያላቸው ዜጎች በቀላሉ ብድር የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የኮርያ መንግስት እያደረገው ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኮይካ የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ሺንያንግ ሊ የኮርያ መንግስት በኢትዮጵያ የፈጠራ ስራ እንዲዳብር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የዲዛይን ስራው የተጠናቀቀው ማዕከሉ በአይ ሲ ቲ ፓርክ ውስጥ የሚቋቋም ሲሆን የውስጥ እድሳት ስራ፣ የፈጠራ የንድፍ ስራ መሳሪያዎች፣ ባለሙያዎች እና አስፈላጊ መሳሪያዎች ይሟሉለታል ተብሏል።

ከልማት ባንክ እና ከተባበሩት መንግስታት ልማት ድርጅት ጋር በጋራ በተዘጋጀው የጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች የብድር ዋስትና ላይ የመከሩ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የኢኖቬሽን ልማት ፕሮጀክት ማዕቀፍ ላይ ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
2.8K views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 13:32:47
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ!

ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

አሁን ላይ 4ተኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት በምዝገባ ላይ እንገኛለን።

የሥልጠናው ፕሮግራም የሚያካትተው ፦

• የተከታታይ 9 ቀን የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሥልጠና

• 3 ወር የንግድ ማበልጸግ እና ማማከር አገልግሎት (Business Development and Consultation, including coaching and pitching)

• 8 ወር የተለያየ የማማከር ድጋፍ, ክትትል እና ሜንቶርሺፕ

• ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን፤

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ
https://forms.office.com/r/TtnFJdedji
3.1K views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 08:06:29 የንግድ ምልክት ምዝገባና
ጥበቃ አዋጅ
2.3K views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 20:54:26 የተጠቃለሉ የንግድ ሕጎች
2.6K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 20:19:07
WALK AWAY...
2.9K viewsedited  17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 21:37:57
https://t.me/ethiopreneure

http://www.schoolofcloud.com
3.7K viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 09:02:58
Funding Opportunity!!
Here is a great grant opportunity to scale up your business from GIZ (German Official International Development Corporation). WIDU.africa is currently offering a grant of €2500 (141,177birr) to support small-scale businesses and innovative business ideas for ethiopian local Entrepreneurs and Ethiopian Diaspora who lives in Germany, France, Switzerland, Austria, Norway, Netherlands and Sweden.

This session will give a brief information and explanation on how to apply for grant to our project and what are the criterias and regulations.
Gud luck .

Share this information!

https://t.me/ethiopreneure
2.6K viewsedited  06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-27 10:19:20
Biginner Mistake as an Entrepreneur
2.1K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 13:32:36 #ቼክ

ቼክ ማለት ገንዘብን ተክቶ የሚያገለግል ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ነው፡፡ ቼክ ሊፈርም የሚችለው በአንድ ባንክ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ያለው ሰው ነው፡፡ድርጅት ከሆነ ደግሞ ፈራሚው በድርጅቱ ቼክ ላይ የመፈረም ስልጣን የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

ቼክ ከመቀበላችሁ በፊት በቼኩ ላይ -የሚከፈለው የገንዘብ መጠን በአሀዝና በፊደል መፃፉን - የሚከፈለው ሰው ስም እና የባንኩ ቅርንጫፍ መፃፉን -ቼኩን የሰጠው ሰው ፊርማ መኖሩን -ቼኩ የተፃፈበት ቀን እና ቦታ መኖሩ ማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ መሆኑን የንግድ ህግ አንቀፅ 827 ይደነግጋል።

ቼኩ ለማን እንደሚከፈል ስም ካልተጠቀሰበት ማንኛውም ቼኩን ይዞ የቀረበ ሰው ይከፈለዋል። ቼኩ በስሙ የተፃፈለት ሰው ወይም በትዕዛዝ የሚል ካለበት ደግሞ በቀላሉ ከጀርባው በመፈረም ለሌላ ሰው ሊያስተላልፈው ይችላል ።ያም ሰው በጀርባው ፈርሞ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላል፡፡ -የገንዘብ መጠኑ ያልተጠቀሰበትን ቼክ ፈርሞ መስጠት አደገኛ ነው ፡፡ ቼኩ የተፃፈለት ወይም የተላለፈለት ሰው የፈለገውን ገንዘብ ሊሞላበት ይችላል፡፡

ቼኩ የሚከፈለው ለባንኩ ለክፍያ በቀረበ ቀን ነው። - ሆኖም ቼኩ በን/ሕ/ቁ 857 መሠረት የወጣበት ቀን ከግምት ሳይስገባ ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ለባንኩ ለክፍያ መቅረብ አለበት፡፡ -ቼኩን የሚፈርመው ሰው የክፍያውን ቀን ቼኩን ከፃፈበት ወይም ቼኩን ካወጣበት ቀን ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ሊያደርገው ይችላል። ለምሳሌ ዛሬ ቼኩን ሲፅፍ የተፃፈበት ቀን ወደኃላ 7 ወር አድርጎ ቀኑን ቢፅፈው ለክፍያ መቅረብ ያለበት 6 ወር ጊዜ ስላለፈ ባንኩ መክፈልም ሆነ ያልከፈለበትን ምክንያት ለመግለፅ ሳይገደድ ቼኩ ለክፍያ መቅረብ ባለበት ጊዜ ባለመቅረቡ ብቻ ይመልሰዋል፡፡

ዛሬ የሚሰጥ ቼክ ወደፊት የዛሬ 4 ወር አድርጎ ቀኑ ከተፃፈበት ለክፍያ መቅረብ የሚችለው ከአራት ወራት በኃላ ካለው ቀን ጀምሮ ባለው 6 ወራት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ቼክ ተቀባዬች የሚሰጣቸውን ቼክ ገንዘቡን መቀበል ከሚችሉበት ቀን አንፃር በጥንቃቄ የተፃፈበት ቀን ማየት ያስፈልጋል ::

-ቼክ የሰጠው ሰው ቼኩ ለባንኩ ለክፍያ ከመቅረቡ በፊት ባንኩን እንዳትከፍል ብሎ መከልከል ይችላል። ባንኩም የክፍያ መከልከያ ትእዛዝ ከደረሰው መክፈል የለበትም።

ቼኩን ለባንክ አቅርበህ በቼኩ ላይ የተጠቀሰውን ያህል በቂ ገንዘብ ከሌለ በሂሳቡ ውስጥ ያለውን ያህል መቀበል ይቻላል። ለቀረው ገንዘብ ደግሞ ባንኩ ‘‘በቂ ስንቅ ለውም’’ የሚል የፅሁፍ ማስረጃ ቼኩን ይዞ ለቀረበው ሰው ይሰጠዋል። -በተለምዶ ‘‘ደረቅ ቼክ’’ የሚባለው ለክፍያ ሲቀርብ በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ከሌለው ሲሆን ባንኩ በሚሰጠው ማስረጃ መሰረት ቼክ ሰጪውን ወይም አውጭውን በወንጀል ያስጠይቃል። ሆን ተብሎ ከተፈፀመ ቼክ አውጪው በወንጀል ህግ አቀፅ 693 መሰረት በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ከሆነ ደግሞ ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስርና በመቀጮ ይቀጣል።

ደረቅ ቼኩ የተሰጠው በቸልተኝነት ከሆነ ደግሞ ሰጭው በመቀጮ ወይም ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስር ይቀጣል ፡፡ -ሳይከፈል የቀረውን የቼኩን ገንዘብ ና ወጭውን ቼኩ የተፃፈለት ወይም ተፈርሞ የተላለፈለት ሰው በፍትሀ ብሔር ከሶ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል፡፡ -በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ደረቅ ቼክ የሚሰጡ ሰዎች በጥፋታቸው በጥቁር መዝገብ ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ከገንዘብ መቀጮ አንስቶ በቼክ ሂሳብ የማንቀሳቀስ መብታቸውን እስከማሳጣት ቅጣት ይጣልባቸዋል፡፡

https://t.me/ethiopreneure
2.4K viewsedited  10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ