Get Mystery Box with random crypto!

TVT institute

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiantechuniversity — TVT institute T
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiantechuniversity — TVT institute
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopiantechuniversity
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.76K

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-30 09:56:20
980 views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 09:56:20 ጭስ አልባ ከሰልን እውን ያደረገው የፈጠራ ሥራ

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ በዓመት 0.21 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የከሰል ምርት በባህላዊ መንገድ ይመረታል፡፡ የምርቱ 70 በመቶ የሚሆነን ደግሞ የሚቀርበው ለከተማ ገበያ ነው፡፡ ይህም ለደን መራቆት እና ለአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

ጉዳቱን የተገነዘበው አቶ ከድር ጀማል መፍተሄ ያለውን ደን ሳይጨፈጨፍ ተፈጥሮ ሳይራቆት ከሰል ማምረት የሚያስችል ፈጠራ ይዞ ከወደ አዳማ ብቅ ብሏል፡፡

ከድር ከብዙ ልፋት በኋላ ወደ ውጤት የቀየረውን የፈጠራ ሥራ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባዘጋጀው 3ኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ ቀርቦ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ከድር እንደሚናገረው ወደዚህ የፈጠራ ሥራ እንዲገባ ምክንያት የሆነው በየአካባቢው የሚመለከተው የደን ጭፍጨፋ መሆኑን ነው፡፡ ‘ክረምት በመጣ ቁጥር ዛፍ ለመትከል ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ አያለሁ ነገር ግን በዘላቂነት ጭፍጨፋውን የሚያስቆም ርምጃ ሲወሰድ አልመለከትም፡፡ በመሆኑም ይህንን ሊገታ/ሊቀንስ የሚችል ሥራ መሥራት እንዳለብኝ ወሰንኩ “ ይላል፡፡

ፈጠራው ለየት የሚያደርገው የከሰል ምርቱ ከወዳደቀ የሻንኮራ አገዳ፣ ከቦቆሎ አገዳ፣ ከተሰባበረ ሸክላ እና ከማንኛውም ተረፈ ምርት መዘጋጀት የሚችል መሆኑ ነው፡፡

የሚያመርተው ጭስ አልባ የከሰል ምርትም በሰው ላይ ምንም ጉዳት እንዳያደርስ ጭስ ያለው ቁሳቁስ እንኳን ቢሆን በፈጠራ ሥራው የማስወገድ ሥራ ይሰራል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ጭሱ ከተወገደ በኋላ ወደ ከሰልነት መቀየር የሚስችል ፈጠራ ነው ይላል የፈጠራው ባለቤት፡፡ በተጨማሪም በዚህ ሂደት የሚመረተው ከሰል በባህላዊ መንገድ ከሚመረተው ጥራቱ በእጅጉ የበለጠ በመሆኑ በጥቂት የከሰል መጠን ብዙ ነገር መሥራት የሚያስችል መሆኑን አስረግጦ ይናገራል፡፡

ከዚህ የፈጠራ ሥራ ባሻገር ሌሎችም ከአምስት ያላነሱ የፈጠራ ስራዎች መሥራቱን የሚናገረው ጀማል ሁሉንም ፈጠራ ሥራዎቹ ታዲያ ብክነት የሚያስወግዱ እና መልሶ መጠቀም ላይ ያተኮሩ መሆናቸውንም ይገልጻል፡፡

በእስካሁን ሂደት በአነስተኛ ማሽን አነስተኛ መጠን ያለው ምርት እያመረተ እንደነበርም ያስረዳል፡፡ አሁን ግን ይላል ጀማል ምስጋና ለአዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ይግባና የፈጠራ ሥራዬን ተሳቢ ያደረገ ትልቅ ማሽን ሰርተውልኛል፡፡ በዚህ ማሽን በመታገዝ ከእንግዲህ እስከ 60 ቀረጢት ድረስ መጠን ያለው ጭስ አልባ ከሰል በቀን ማምረት እንደሚያስችለው ያብራራል፡፡

እስካሁን በመንግስት የተደረገለትን ድጋፍ አመሰግኖ በቀጣይ በተለይ የቦታ ድጋፍ ቢደረግለት በሥራው ይበልጥ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ይገልጻል፡፡ ጀማል ከራሱ አልፎ ረዥም አስቦ ለሀገር የሚጠቅም ፈጠራ ይዞ መጥቷል፡፡
986 views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 23:04:44
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የ2015 ክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ።

ክህሎት ለተወዳዳሪነት በሚል መሪ ሀሳብ ከግንቦት 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የ2015 ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።

ውድድሩ ፍፃሜውን ሲያገኝ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመውጣት ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ከአንድ መቶ ሺህ እስከ 80 ሺህ ብር ድረስ የማበረታቻ ሽልማት፣ ዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስራ ሁለት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሦስት ነሀስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት አንደኛ በማግኘት የ2015 ክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዘጠኝ ወርቅ፣ ስአስር ብር እና ሰባት ነሀስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ሰባት ወርቅ፣ ስምንት ብር እና ሦስት ነሀስ በማግኘት ሦስተኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን አጠናቋል።
1.2K views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 09:33:18
አካል ጉዳተኝነቱ ውጤታማ ከመሆን ያላገደው የፈጠራ ባለቤት
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0SM8AV2SdfjVHrcUSHWGWk9XdtH6qp7TSPvvzieEyBfaJcQPUHVKGQApSVGeCC5nDl&id=100069116383994&mibextid=Nif5oz
1.5K views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 09:33:18
#Happeningnow
#አሁን
ክህሎት ለተወዳዳሪነት በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው ሦስትኛው ሀገር አቀፍ
የክህሎት ውድድር በተለያዩ ሙያዎች እንደቀጠለ ነው፡፡
ክህሎት ለተወዳዳሪነት!
ግንቦት 15/2015 ዓ.ም፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
1.4K views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 09:33:17
እጃቸውን፣ ልባቸውን እና አዕምሯቸውን አስተሳስረው የሚሰሩ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ ፈጠራ በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡ የእጅ ጥበብ ያላቸው፤ እጃቸውን፣ ልባቸውን፣ አዕምሯቸውን አስተሳስረው የሚሰሩ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡

ግብርናችን፣ ኢንዱስትሪያችንም ሆነ ኮንስትራክሽን ዘርፉ አልዘመነም፡፡ ብዙ ሴክተር በመፍጠር ሥራን ማቅለል የሚያስችል ሁኔታን መፍጠር የሚያስችል ሀገር ነው ያለን፡፡

ይህ ለማድረግ ግን ማንኛቸውን በአካባቢያችን ያሉ ፈተናዎች፣ ተግዳሮቶች እንዳያቆሙን በተባበረ፣ በተደመረና በተሳሰረ መልኩ ችግርን ብቻ በሚያወራ ሳይሆን መፍትሄ በሚያመጣ እሳቤ በመፍጠር ኢንዱስትሪያችንን እንድናዘምን አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡

እንበርታ፣ እንፍጠር፣ ፈተናንና ችግርን ለማለፍ መፍትሄ ላይ የምናተኩር እንሁን ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዚህ መንገድ የበለፀገች ሀገር ለመፍጠር ሁላችንም በየሙያችን የምንረባረብ እንሁን ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ግንቦት 14/2015 ዓ.ም፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
1.1K views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 09:33:17 ፈጠራ ወደ ከፍታ በሚያስፈነጥሩ ብዙ ችግሮች የተከበበ ነው ፤ መፍትሔ ተኮር ከሆንን ወደ መልካም አጋጣሚ ልንለውጠው እንችላለን።

ክቡር ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

3ተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር፣ “ክህሎት ለተወዳዳሪነት” በሚል መሪ  ሀሳብ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አቢይ አህመድ(ዶ/ር)፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ  ሀገራችን ብዙ ችግሮች እንዳሉበባቸውና አንዱ ዘርፍ የሌላው ግብዓት ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ የተሳሰሩ ባለመሆናቸውና በሚፈለገው ጥራት ስለማይመረቱ ከውጭ እንደሚገቡ በማስታወስ የክህሎት ውድድሩ ይህንን ለማስቀረት እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለማግኘት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈጠራ ወደ ከፍታ በሚያስፈነጥሩ ብዙ ችግሮች የተከበበ ነው ፤ መፍትሔ ተኮር ከሆንን ወደ መልካም አጋጣሚ ልንለውጠው እንችላለን።

የፋይናንስ፣ የቢሮክራሲ እና የመስሪያ ቦታ ችግርን የፈጠራ ሰዎች ከሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። ሆኖም መፍትሔ ተኮር መሆንን ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።

ውጤት ላይ ማትኮር ማለት በቀለለ ነገር አስቸጋሪ ነገርን ማለፍ መቻል ነው፤ ለዚህም የፈጠራን አስቸጋሪነት በመረዳት ፈተናዎች እንዳያቆሙን በተባበረ እና በተደመረ አቅም ኢንዱስትሪያችንን እናልማ ያሉት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተና እና ችግርን ለማለፍ እንበርታ፣ እንፍጠር ፣ እንጠንክር ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተቋቋመ አንድ ዓመት ተኩል ቢሆነውም ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ማሳየቱን እና በውድድሩ መክፈቻ ሥነ ስርዓት የፈጠራ ሥራቸውን ይዘው የቀረቡት የፈጠራ ባለሙያዎች ለችግር ያስቀመጡትን መፍትሔ በውድድር መማማሪያ እና ያለንን ብቃት ማሳያ ነው ብለዋል።


የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው
ባስተላለፉት መልዕክት የክህሎት ልማት ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት የሚረጋገጥበት አዲስ ምዕራፍ ነው፡፡

በክህሎት የበቁ፣ ምርትና ምርታማነትን በማረጋገጥ የአገራችን ብልፅግና  ዕውን እንዲሆን የራሳቸውን አስተዋፅኦ የሚበረክቱ፣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናዎችን በመጠቀም ለማፍራት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተተገበሩ ነው ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ‹‹ከሥልጠና በላይ›› በሚል መርህ የክህሎት ልማት ልህቀትን ለማረጋገጥ በሚተገብራቸው  የሪፎርም ሥራዎች መካከል ገበያ መርና የመልማት ፀጋን በመጠቀም የስልጠና ማዕከላትን በዞን ማደራጀት አንዱ ስትራቴጂ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትሯ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን የማምረቻ ማዕከላት በማድረግ ተግባራዊ ውጤትን የሚያረጋግጡበት ሥርዓት በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የክህሎት ልማት የዕድገት ምንጭ መሆኑን በማስገንዘብ ለዘርፉ በቂ ትኩረት እንዲሰጠው ለማስቻል ብዙ ርቀትን መጓዝ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን መስራት ይጠይቃል ያሉት ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት በአገር ዓቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ መሰል ውድድሮች የዘርፉን ገፅታ በመገንባትና ወጣቶች ዘርፉን ምርጫቸው እንዲያደርጉ በማነሳሳት ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወትም አመልክተዋል፡፡

ከኮሌጆች ጀምሮ በተካሄዱ ውድድሮች ሦስት ምዕራፎችን አልፈው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመወዳደር የበቁ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ተወዳዳሪዎችን ያካተተው 3ኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የቴክኖሎጂ ሽግግርን ዕውን ለማድረግ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው ብለዋል፡፡

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በየሁለት ዓመቱ በሚካሄደው የክህሎት ውድድር ላይ ለመሳተፍና የዓለም ዓቀፉ የክህሎት ማህበረሰብ (skill society) አባል  ለመሆን ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርባና ተገቢውን መስፈርት አሟልታ ምላሽ እየተጠባበቀች እንደምትገኝም ተናግረዋል፡፡

የክህሎት ልማት ዘርፍ ተጠናክሮ እንዲወጣ አደረጃጀቱን በመከለስና የነበረውን የፖሊሲ ማነቆ በመፍታት ረገድ የኢፌድሪ መንግስት ላሳየው ቁርጠኝነትም ክብርት ሚኒስትሯ ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡

ግንቦት 14/2015 ዓ.ም፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡
1.0K views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 09:33:17
1.1K views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 17:39:06
1.0K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 10:55:32
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2015 የትምህርት ዘመን በተቋሙ ዋና ግቢ ለመማር ያመለከታችሁና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ጥር 23 እና 24/2015 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃልን።

በቅጣት ለመመዝገብ ጥር 25/2015 ዓ.ም። (ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል።)
946 viewsedited  07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ