Get Mystery Box with random crypto!

በተለያዩ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው ለአጭር ግዜ የሰበዓዊ አገልግሎት ስራ ለሚሰሩ ግለሰ | የፓስፖርት አገልግሎት (passport service)

በተለያዩ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው ለአጭር ግዜ የሰበዓዊ አገልግሎት ስራ ለሚሰሩ ግለሰቦች የሚሰጠው የቪዛ ጊዜ ተራዘመ።

ከዚህ ቀደም ለ1 ወር ይሰጥ የነበረ የNGO ቪዛ ከትላንት ጀምሮ ለ3 (ሦስት) ወር እንደሚሰጥ የኢሚግሬሽን እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አሳውቋል።

ለተጨማሪ ግዜ ቪዛቸው እንዲራዘም ለሚጠይቁ ድርጅቶች ለኤጀንሲው ጥያቄ ሲያቀርቡ የሚራዘም ይሆናል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም የሰብዓዊ አገልግሎት ስራ የሚሰሩ ግለሰቦች የ1ወር የቪዛ ጊዜ ይዘው ገብተው ስራቸውን ካልጨረሱና የይራዘምልን ጥያቄ ባቀረቡ ወቅት ይራዘምላቸው ነበር።