Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Orthodoxs Daily

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxs — Ethiopian Orthodoxs Daily E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxs — Ethiopian Orthodoxs Daily
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianorthodoxs
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.31K
የሰርጥ መግለጫ

በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ የሚታሰብ ቅዱሳን፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ምንባባት ፤ ብሂለ አበው እና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ፅሁፎች ያገኙበታል::Share https://t.me/ethiopianorthodoxs //like page on facebook fb.me/ethiopianorthodxs ለሀሳብ አስተያየትዎ
@Yakob520

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 16:11:35
ለመንፈሳዊ ትምህርት ፈላጊዎች
መንፈሳዊ ትምህርት ባሉበት ሆነው በኦን ላይን (Online) መማር እንደሚችሉ ያውቃሉ!
ካላወቁ እንንገሮ! የአንቀጸ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ት/ክፍል ምዝገባ እያደረገ ይገኛል፡፡
በቀዳማይ ክፍል ትምህርቶች
  ትምህርተ ሃይማኖት
  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
  የቤ/ክ ታሪክ
  ክርስቲያና ስነ ምግባር
ትምህርቶች ለተማሪዎች የሚሰጥ ይሆናል!
ለምዝገባ ፡- 
  በሚከተለው የጎግል ፎርም ይጠቀሙ https://forms.gle/VJPVJ2VRMj7Tpddt7 
  በሰ/ት/ቤቱ የንዋያተ ቅዱሳት መገልገያ እቃዎች መሸጫ ሱቅ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
  በሰ/ት/ቤቱ ቤተ መጻሕፍት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
  በሰ/ት/ቤቱ የትምህርት ንዑስ ክፍል ቢሮ ከሰኞ እስከ እሁድ
ለበለጠ መረጃ ፡- +251913831400 / +251911112851 / +251969184235
 በቴሌ ግራም https://t.me/anqesbirhanss
አዘጋጅ ፡-  የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ክ አንቀጸ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
366 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:33:45 ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ::

እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና::

እንሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፈው ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሰራ በስምህ መባ ለሚሰጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህ ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ::

አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ::

ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ጥቂት ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርግና አረፈ::

በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት::

ይህንን በማሰብ ከዋዜማው ጀምሮ ታላቅ በዓል እናደርጋለን በተክለ ሃይማኖት ስም በተሰራች ቤተ ክርስቲያን በገዳማት ተሰባስበን እግዚአብሔርን እናመልካለን::

እግዚአብሔር ሆይ በፃድቁ ስም ተሰባስበን ስናመሰግንህ በፃድቁ ስም መልካም ስንሰራ ቃል ኪዳንህን አታስቀርብን ና ባርከን ፈውሰን አሜን እንላለን::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ተክለ ሃይማኖት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን::
@ethiopianorthodoxs
615 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:33:39 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አራት በዚህች ታላቅ ዕለት የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ አባታችን ተክለ ሃይማኖት አረፈ::

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀርያ ነው::

እሊህም ቅዱሱን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው::

እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖረ::

በዚህም ነገር እያሉ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስከ ገዛ ድረስ::

የየሀገሩ መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል:: ከማረከውም ደምግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶቹ ያደርጋቸዋል::

በዚያ ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ::

አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባሕሩ ውስጥ ተሸሸገ::

ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት በአያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ::

በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ:: ለሠርጉም እንዲሰበሰቡ ወደ መኳንቶቹ ሁሉ ላከ::

እግዚእ ኀርያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረሚ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች::

ያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞረሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት::

ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ አያት አድንቆ በልቡ ይቺ ሴት ምንድ ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ::

የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዚእ ኀርያ እንደሆነች አገኛት:: እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው::

ከዚህም በኃላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው::

የዜናው መሰማት በዓለም ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው::

ከጥቂት ቀኖች በኋላ ይህ ቅዱስ ተፀንሶ በታኅሣሥ ወር በሃያ አራት ተወለደ::

በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ በቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው:: ለክርስትና ጥምቀት ባስገቡት ጊዜ ፍስሐ ጽዮን ብለው ሰየሙት::

ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመንፈስ ቅዱስ ጸና::

ከዚህም በኋላ ዲቁና ይሾም ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት ::

በዚያ ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ አባ ቢንያሚ ነበር:: ወደ ጳጳሱ ባደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት::

የዲቁና ሹመትን ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ ጎልማሳም በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሔደ::

ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ በሚያምር ጎልማሳ አምሳሎ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው::

ወዳጄ አትፍራ እንግዲህስ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን::

እንደ ኤርሚያስና አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኅፀን መርጬ አክብሬሃለውና::

እንሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኵሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ::

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድሆችና ለምስኪኖች በተነ:: ዓለሙንም ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደተከፈተ ትቶ ምርጒዙን ይዞ በሌሊት ወጣ::

ከዚህም በኋላ ወደ ጳጳስ ሒዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ::

ዐሥራ ሁለት ሽህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ:: ለጣዖት የሚሰዉበትን ሁሉ ሻረ:: በውስጡ የሚኖሩ አጋንንትን እስኪሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ::

ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሒዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ::

ከሀዲ ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው:: በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው::

እርሱ ግን በደኅና ይመላለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሰቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትን ጦርም ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው::

ከዚህ በኋላ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ::

የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው:: ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው:: በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁል ጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር::

ዜናውንም ሰምተው ወደርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኅነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ በማመንም ያጸናቸዋል::

ከዚህም በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ:: በገድል ተጸምዶ ወደ ሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደ ባሪያ ሲያገለግል ኖረ::

በአንድነት የሚኖሩ መነኮሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር::

በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በኋላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደ ሚኖረው ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሔደ:: ከእርሱም የምንኩስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ::

ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ::

ከዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሀም በአንድነት ኖሩ::

ከዚያም ግራርያ ወደሚባል አገር ሒዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ:: በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበር ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው::

ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኮሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስ በእርሳቸውም አይተዋወቁም::

እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው: በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ስለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እንደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም::

ከዚህ በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በኋላም በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው በዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስቲሰበር ሰባት ዓመት ቆመ::

በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ ውኃም ሳይጠጣው ኖረ::

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ::

መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ
522 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:16:31 (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 21)
----------
18፤ በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ።

19፤ በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና። ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።

20፤ ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው። በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች? ብለው ተደነቁ።

21፤ ኢየሱስም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ። ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤

22፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው።
https://t.me/ethiopianorthodoxs
694 views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:10:31
1.3K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:23:32 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅ ዱስ ስም የተወደዳቹ የዚህ ጹሑፍ ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ ሰባኤውን በሰላም አስፈጽሞ ለዚህ ታላቅ ቀን ያደረሰን አምላክ ይክበር ይመስገን።

የዛሬን መልዕክት ከብዙ በጥቂቱ በሦስት ክፍል ከፍዬ አቅርቢዋለሁና በረከቷ ረድኤቷ ይድረሰን አሜን!

ነሐሴ 16 በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ::

ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር::

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው::

ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር 16 ቀን ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ::

የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው::

የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው::

እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት::

ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ::

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ::

ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፅዋት ሁሉ አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት::

አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት::

በኪሮቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጅዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች::

2...ወንጌላዌ ዮሐንስ ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ወረደ።

ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽመው ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው::

እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንዳሳረጓት ነገራቸው::

ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ::

ከዚህ በኋላ እያዘኑ ሳለ እንሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላቹ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ::

እንሆ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳቸው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ::

ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴ ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሳየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን::

በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉኑም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዶ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት::

እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እየአንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው::

የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዔ ካህን ሆነ::

እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ::

ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሁኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ::

3.....ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋ ውንና ደሙን አቀበላቸው::

ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት::

በዚህች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው::

መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚህች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ::

የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርጉ ሁሉ በዚህች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውቱ ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው::

እመቤታችንም ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው።

ልጄ ሆይ እንሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸው ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ድንቆች ሥራዋችን አዩ::

እመቤታችንም ይህንን ስትናገር በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ::

የተወደዳቹ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለ እኛ ወደተወደደ ልጅዋ ሁል ጊዜ ትማልዳለችና::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን::
@ethiopianorthodoxs
1.3K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:58:19 የነሐሴ ፩፫ ቅዳሴ ምንባብ ቡሄ
(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 9)
----------
28፤ ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።

29፤ ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

30፤ እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤

31፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።

32፤ ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

33፤ ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።

34፤ ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።

35፤ ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

36፤ ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።

37፤ በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።
@ethiopianorthodoxs
1.8K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 20:57:51
1.4K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 08:14:17
1.7K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 09:16:32
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም
1.6K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ