Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት  ባለሥልጣን ዋና የዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ አንጋፋውን  የኢት | EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት  ባለሥልጣን ዋና የዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ አንጋፋውን  የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአዲስ መልክ  በማደራጀት አዳዲስ የሚዲያ መሳሪያዎችን በመግጠም የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚሠራውን ስራ በመጎብኘት  የባለሥልጣን መስሪያቤቱ የጤና ግብዓት ቁጥጥር መረጃዎች ወጥነት ባለው መልኩ ለህብረተሠቡ በማድረስ የቁጥጥሩ ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ በቅነጅት ለህብረሰቡ መረጃ እንዲደርሰው ለማድረግ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የበላይ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ በቀጣይ በጋራ በመሆን የምግብ ደህንነት፣በመድኃኒት ደህንነት ፣ጥራትና ፈዋሽነት፤በህክምና መሳሪያዎች ጥራትና ውጤታማነት ጉድለት እንዲሁም ሌሎች ቁጥጥር በሚደረግባቸው ምርቶች በህብረሰባችን ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ቀጣይነት ያለው መረጃ ለማድስ ውይይት በማድረግ በጋራ በመስራት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የቁጥጥሩ ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሰራ ተገለጸ።