Get Mystery Box with random crypto!

በ2014 በጀት ዓመት የኮቪድ ክትባትን ጨምሮ የመድኃኒቶችን ደህንነት ቁጥጥርና ክትትል በማድረ | EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

በ2014 በጀት ዓመት የኮቪድ ክትባትን ጨምሮ የመድኃኒቶችን ደህንነት ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ፣የምግብ ላብራቶሪን በአዲስ መልክ በማደራጀት የተለያዩ ምርመራዎችን እንዲጀምር ከማድረግ አኳያ፣በምግብ ምርት ላይ ቁጥጥር በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎችን ከመውሰድ አንጻር ፣በአዲስ አበባ ደረጃ ከትንባሆ ጭስ ነጻ የማድረግ ፕሮጀክት በማስጀመር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ህብረተሰቡን በማሳተፍ እንዲሁም በሁሉም የከተማ አስተዳደር ባለቤትነት ተወስዶ መሰራት መጀመሩ፣ህገወጥ በምግብና በጤና ግብዓት ምርቶች ላይ ቁጥጥር በማድረግ አጥፊዎችን በህግ ተጠያቂ ከማድረግ አኳያ ፣በኮሙኒኬሽን ስራ፣ የተቋሙ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ፣የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር የተሰሩ ስራዎች እና ሌሎች የላቀ አፈጻጸም የተገኘባቸው ስራዎች መሆናቸው በመግለጽ ተመክሮችው ተቀምረው ሊሰፉ እንደሚገባቸው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ አስታውቀዋል፡፡