Get Mystery Box with random crypto!

#Daily_Tips Kicking Away the Ladder! አሁን ላይ በኢኮኖሚ ብልጽግና ላይ ደ | Ethiopian Business Daily

#Daily_Tips
Kicking Away the Ladder!

አሁን ላይ በኢኮኖሚ ብልጽግና ላይ ደርሰዋል ተብለው የሚገለጹ ሀገራት በማደግ ላይ ባሉበት ወቅት የተቋማትን ነጻነት የሚጠብቁ አልነበሩም! ምክንያቱም በፍጥነት ለማደግ ተቋማትን ከገበያ ጣልቃ ገብነት ለመጠበቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት በማደግ ላይ ያሉ ድሃ ሀገራት ለማደግ በሚሞኩሩበት ወቅት የተቋማትን ነጻነት ማረጋገጥ አለባችሁ በሚል ጫና ከፈጣን እድገታቸው ለመገደብ ዘወትር ይጥራሉ፡፡

የዛሬ 20 ዓመት በHa-Joon Chang የተጻፈው እና ያደጉ ሀገራት እነሱ ባደጉበት መንገድ ታዳጊ ሀገራት እንዲሄዱ አይፈቅዱም! ያደጉበትን መንገድ ለመከተል የሚፈልጉትን በተለያየ ዘዴ ያከላክላሉ Kicking Away the Ladder "መንሰላሉን ገፍቶ መጣል" ወይም ያደጉበትን ትክክለኛ ሚስጥር ይደብቃሉ ይላል፡፡

አሜሪካ ለማደግ በሄደችባቸው ወቅቶች በገበያ ጣልቃ በመግባት የግሉን ሴክተር ትደግፍ ነበር፤ ጠበቅ ያሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ትጠቀም ነበር፤ ክልከላዎችን ታደርግ ነበር፤ ወዘተ ነገር ግን አሁን ላይ በማደግ ላይ ያሉ ድሃ ሀገራት ከዓለም ባንክ፤ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት እና ከሌሎች ተቋማት ብድር እና እርዳታ ለማግኘት ማሟላት አለባቸው በሚል ያዘጋጀቸውን (Washington Consensus) ማለትም ነጻ ገበያ መፍጠር፤ የገበያ ጣልቃ ገብነትን መቀነስ፤ ሰብአዊ መብት ማክበር፤ ክልከላዎችን ማንሳት፤ ወዘተ ይከበር የሚለው ህጓን ድሮም አሁንም በተገቢ መልኩ በራሷ ሀገር የማይተገበሩትን ታዳጊ ሀገራት ላይ አሳሪ በማድረግ አውጥታለች ይላል፡፡

የሰዎችን ጉልበት ብዝበዛ፤ የተፈጥሮ ሃብቶችን በገፍ መጠቀም፤ የአየር ብክለት፤ የውሃ ብክለት፤ መርዛማ ኬሚካል መጠቀም፤ ደን መጨፍጨፍ፤ ወዘተ ለማደግ ሲሞክሩ አንደልባቸው የተጠቀሙት መንገድ ነበር! ነገር ግን አሁን ላይ ለማደግ የሚሞክሩ ሀገራት እነዚህን ተግባራት እንዲያደርጉ በተለያየ ዘዴ አይፈቅዱም፡፡

በኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት እንግሊዝም፤ ጀርመንም፤ አሜሪካም በባሪያ ንግድ የተወሰዱ ሰዎችን እና ህጻናትን ሳይቀር ለምርት ሲጠቀሙ ነበር! ነገር ግን እነሱ ለማደግ ሲሉ ያለፉበትን ይህን አካሄድ አሁን ላይ ለየትኛው ሀገር የሰብሃዊ መብት ጠባቂ ነን በሚል ምክንያት ይህ እንዲሆን አይፈቅዱም!

በ19ኛው ክፍለዘመን የአውሮፓ ሀገራት በተለይ እንግሊዛዊ የሌሎች ሀገራት ዜጎች የፈጠራ መብት እንደራሱ አድርጎ የመጠቀም በህግ መብት ነበራቸው፤ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ምርጫ ለሴቶች በአውሮፓ ሀገራት አይፈቀድም ነበር እንዲሁም ህፃናትን ከጉልበት ስራ የሚጠብቅ ህግ አልነበራቸውም (በወቅቱ በአሜሪካ 50% የሚሆነው የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ሰራተኛ እድሜው ከ16ዓመት በታች ነበር!፤ ወዘተ።

ግን በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ የቻይና ምርቶች የህጻናትን እና እስረኞችን ጉልበት ተጠቅማ ነው የምታመርተው (ሰብዓዊ መብት ረገጠች) ስለዚህ በተመረጡ ቁሶች ላይ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል የሚል ዛቻ በተደጋጋሚ ታነሳለች (የኢኮኖሚ ተፎካካሪነትን ለመቀነስ ነው!)፡፡

ያደጉ ሀገራት ለሃይል ግብዓት ዩራኒየምን አበልጽገው ከኒዩክሌር ሃይል ይጠቀማሉ (መሳሪያም አድርገው ይታጠቃሉ)! ነገር ግን ታዳጊ ሀገራት የሃይል ምርጫቸውን ኒዩክሌር ለማድረግ ቢያስቡ ጫናው ከባድ ነው (ኢራን እና ሰሜን ኮርያ ተመሳሳይ ጫና ውስጥ ናቸው)፡፡ በምድር ላይ የመጀመሪያውንም ሆነ የመጨረሻውን አቶሚክ ቦምብ ጃፓን ላይ የሞከረችው ሀገር አሜሪካ ብቻ ነች፡፡

በዚህ ወቅት ለማደግ እየሞከሩ ያሉ ድሃ ሀገራት አሁን ላይ ያደጉ ሀገራት ለማደግ ይሞክሩ በነበረበት ወቅት ከነበራቸው የተሻለ ተቋማዊ አደረጃጀት አላቸው! ነገር ግን የበለፀጉ ሀገራት ለማደግ ሲሉ ማንኛውንም ጤናማ ያልሆነ አካሄድ ሞክረዋል (በወቅቱ ቁጥጥር ያደርግባቸው የነበረ አካል አልነበረም) ድሃ ሀገራት በዚህ ፍትሃዊነት በጎደለው ቁጥጥር በበዛበት ጊዜ እንደምንም ብሎ ማደግን እንዴት ያሳኩታል?

Via - The Ethiopian Economist View
@Ethiopianbusinessdaily