Get Mystery Box with random crypto!

ጉግል ያበለፀገውን አነጋጋሪ ቻትቦት ተጠቃሚዎች እንዲሞክሩት ግብዣ አቀረበ፡፡ #LaMDA (Lang | Ethiopian Artificial Intelligence Institute

ጉግል ያበለፀገውን አነጋጋሪ ቻትቦት ተጠቃሚዎች እንዲሞክሩት ግብዣ አቀረበ፡፡

#LaMDA (Language Model for Dialogue Applications) የተባለውን የውይይት መለዋወጫ ሮቦት (ቻትቦት) ፍላጎቱ ያላቸው ተጠቃሚዎች እንዲሞክሩት እድል ማመቻቸቱን ጉግል አስታወቀ፡፡

በዚህም ቻትቦቱ በይፋ ጥቅም ላይ ከመዋሉ አስቀድሞ በአሜሪካ ብቻ የሚገኙ ውስን ተጠቃሚዎች እንዲሞክሩት ኩባንያው የምዝገባ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በዚህ መልኩ የውይይት መለዋወጫ ሮቦቱን ጥቅም ላይ ከሚያውሉ ግለሰቦች የሚሰበሰበውን ግብረ መልስ በመጠቀም መተግበሪያውን ለማሻሻል እና አስፈላጊ እርምቶችን ለማድረግ ማቀዱን ኩባንያው ገልጿል፡፡

LaMDA የሰዎች ንግግር እና ታሪኮች ላይ መሠረት አድርጎ የሰለጠነ በመሆኑ ለሚጠየቀው ጥያቄ ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎችን ማቅረብ እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡

ይህም የቻትቦቱን ምላሾች ሳቢ፣ ዓውድ ተኮርና እውቀትን መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

በቅርቡ ከኩባንያው የተሰናበተ ብሌክ ሌሞይን የተባለ ባለሞያ ይህ የውይይት መለዋወጫ ሮቦት ልክ እንደ ሰው ስሜቶችን የተላበሰ እንደሆነ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ሆኖም ጉግል እና በርካታ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምሁራን አስተያየቱን ውድቅ በማድረግ ቴክኖሎጂው በባለሞያው በተገለጸው የሰው ልጅ ባሕርያትን የመላበስ ደረጃ እንዳልደረሰ አመላክተዋል፡፡